የውህደት ትምሕርት በጀርመን

« እነዚህ ደንቦች በርግጥ ለመረዳት ቀላል ናቸው ። እዚህ መኖር የሚፈልግ ጀርመንኛ መማር አለበት ። እዚህ የሚኖር ሰው ህጎቻችንንና እሴቶቻችንን ማክበር ይገባዋል ። ይህን የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በኛ ዘንድ ተቀባይነት አለው ። ይህን ማድረግ የማይፈልግ ማዕቀብ ይጠብቀዋል ። ያን ያህል ቀላል ነው ። »