የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ትምህርት አቋረጡ

የቅድስት ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ከብዙ ክርክርና ድርድር በኋላ ያነሷቸው ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው ትምህርት አቁመው መሰንበታቸው ተጠቆመ። ሰኞ ህዳር 13ቀን 2003ዓ.ም. ደግሞ ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውም ተገልጧል። ተማሪዎቹ ችግራቸውን ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ሴቶች ጉዳይ ፅህፈት ቤት በሰላማዊ ሰልፍ እንዳቀረቡም ታውቋል። ታደሰ እንግዳው በቦታው ተገኝቶ የሚከተለውን አጠናቅሯል።

ሙሉ ዘገባውን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ