አወዛጋቢው የዛራትሲን መጽሐፍ

(DW) — ትናንት እዚህ ጀርመን ገበያ ላይ የዋለው የጀርመን ቡንደስ ባንክ የቦርድ አባል የቲሎ ዛራትሲን መጽሐፍ ጀርመን ውስጥ አሁንም የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ እንደቀጠለ ነው።

ጀርመን ራሷን ለውደቅት እየዳረገች ነው” የሚል ሀሳብ የያዘው የዚህ መፀሀፍ ደራሲ የእስልምና ባሕል ጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞች ከህብረተሰቡ ጋር ተዋህደው እንዳይኖሩ እንቅፋት ሆኗል ሲሉ ተችተዋል ። ጀርመን ከሚኖሩ የውጭ ዜጎች በተለይ ሙስሊሞች ከህብረተሰቡ ጋር ባለመዋሀዳቸው ምክንያት ሀገሪቱን ከመጥቀም ይልቅ ሸክም እንደሆኑባት በመፀሀፋቸው ያካተቱት ሀሳብ ሙስሊሙን ህብረተሰብ በእጅጉ አስቆጥቷል ። ከጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል አንስቶ የጀርመን ፖለቲከኞችም የዛራትሲንን ሀሳብ ተቃውመው አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው።

ያዳምጡ