የአልሸባብ ጥቃት እየተጠናከረ መምጣት

አልሸባብ ሞቃዲሾን እያመሳት ነው። ትላንት የፈጸመው ጥቃት ለዚያች ሀገር እየተደረገ ያለውን ዓለም አቀፍ ጥረት መና እንዳያስቀረው በእርግጥ እየተሰጋ ነው።

በትናትናው ዕለት ሞቃዲሾ በሚገኘው የሽግግሩ መንግስት ቤተመንግስት አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሆቴል በአልሸባብ በተቀነባበረ የቦምብ ጥቃት6 የምክርቤት አባላትን ጨምሮ 32 ሰዎች ሲገደሉ በዛሬው ዕለትም ውጊያው እንደቀጠለ ከስፍራው ከሚወጡ ዘገባዎች ለመረዳት ተችሏል። አንድ ጋዜጠኛ በዛሬው ውጊያ ከተገደሉት 6 ሰዎች ውስጥ እንደሚገኝበት ተነግሯል። የአልሸባብ የሰሞኑ ማየል ሶማሊያን ወደየት ይወስዳት ይሆን? ኢትዮዽያ ዳግም ወደሶማሊያ ሳትገባ አትቀርም የሚለው የፖለቲካው ተንታኞች ግምት አሁን ላይ በሰፊው እየተሰማ ነው። አርያም ተክሌ የአለም አቀፉን የግጭት ቡድን የሶማሊያ ተንታኝን ያነጋገረችበ ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል። ያዳምጡ፤