የመጀመሪያው ታላቅ የሙዚቃ ደራሲ ቤትሆቨን
የሙዚቃ ደራሲው ሉድቪሽ ፋን ቤትሆቭን እንደቀደሞው ሁሉ አሁንም ሰፊውን ህዝብ ይመስጣል ።
ቤትሆቨን ቻይና ውስጥ እንደ አንድ የፖፕ ሙዚቀኛ ያህል ክብር አለው ። በመላው ዓለም የቤትሆቨን የሙዚቃ አድናቂዎች ማህበር ይገኛል ። በኢንተርኔትም ቢሆን ስለ ቤትሆቨን ብዙ ይባላል ። የቤትሆቭን ሙዚቃ አሁንም ሰዎችን የሙዚቃ ምርኮኛ ያደረገበት ምስጢሩ ምንድን ነው ቤትሆቨንስ በአሁኑ ዘመን እስከ ምን ድረስ ተፈላጊ ነው ? ከትውልድ ከተማው ጋር ምን ያህል ጥብቅ ትስስር አለው ? የዶይቼቤለዋ አናስታስያ ቡትስኮ እዚህ ቦን ውስጥ በየዓመቱ በመስከረም ወር ስለሚከበረው የቤትሆቭን ሙዚቃዊ በዓል ያጠናቀረችው ዘዘባ መልስ አለው ።