ያልታደለ ሕዝብ በማንኪያ ተሰጥቶት በአካፋ ይዛቃል

ኢትዮ እማማ)

ሰሞኑን ወያኔ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የደመወዝ ጭማሪ አድርጌያለው በማለት ለፍፏል።ከ600 ብር በታች ደመወዝ በወር የሚያገኙ የአንድ እርከን ጭማሪ ሲያደርግላቸው። በአንፃሩ ጎን ለጎን ከሚዘርፈው ሌላ ቁልፍ ቦታ ላስቀመጣቸውና የእኔ ለሚላቸው ካድሬዎቹ ደግሞ ከምስጊኑ ሕዝብ በ18 እጥፍ ጭማሪ አድርጎላቸዋል።

ለምሳሌ አንድ የበታች የመጨረሻ ሠራተኛ የሚባለው በፊት የሚያገኘው ደመወዝ 320 ብር ሲሆን ተጨመረለት በተባለው በአዲሱ የደመወዝ ስኬል መሠረት 444 ብር የከፈለዋል። ይህ ማለት የተጨመረለት 124 ብር ብቻ ነው።

በአንፃሩ አንድ የወያኔ ባለሰልጣን ጎን ለጎን ከሚዘርፈው ሌላ እንዲሁም ወደተላያዩ ክልሎችና ከሀገሩ ሲወጣ ከሚታሰብለት የቀን አበልና ፌስታ ውጪ በወር በፊት ከሚያገኘው ደመወዝ 7168 ብር ላይ ተጨመረለት የተባለው 2125 ብር ነው።ይህም ደመወዙን ወደ 9293 ብር ያሳድግለታል።

ከዚህ ሌላ ለካድሬዎቹና በየቀበሌው ላስቀመጣቸው የወያኔ አባላት ከ606 ብር እስከ 1427ብር በላይ ጭማሪ እንደተደረገላቸው ለማወቅ ተችሏል።ከዚህ አንፃር 124 ብር ብቻ የተጨመረለት ምስጊኑ ድሀ ሕዝብ እየተወደደ ባለው የኑሮ ውድነት እንዴት ብሎ ነው በ444 ብር ሕይወቱን ማቆየት የሚችለው?

ወያኔ በቅርቡ ባደረገው የውሸት የዋጋ ማስተካከያ ነጋዴው የሚሸጠውን ጨርሶ ባዶ መጋዘን በአሁኑ ወቅት ታቅፎ ባለበት ወቅት።በአንፃሩ በመሬት መቸብቸብና በንግድ ውስጥ የተሰማራው ወያኔ ትርፋማ እየሆነ ይገኛል።ኅብረተሰቡ ደግሞ ተመልሶ የሀገሪቱ ኑሮው ወደ ላይ በማሻቀቡ፤ በመኖርና ባለመኖር መካከል ወስጥ ነው ያለው።እናም ያልታደለው ምስጊኑ ሕዝብ ካለው አንጡራ ሀብት በማንኪያ ተሰጥቶት በአካፋ ይዛቅለታል። ለመሆኑ መቼ ይሆን “ከእኔ ይልቅ ለሕዝቤ!” ብሎ የሚያስብ መሪ ለዚች ምስጊንና ድሀ ለሆነች ሀገር አምላክ የሚሰጣት?