ዜጎችና መሪ በአንዱዓለም በቀለ(ስዊዘርላንድ)

ቺሊ
አልፎም አይረሳ ኖሮም ለታሪክ ነው፥
የአምላክ ጥበቡ ሁሌም እንግዳ ነዉ፥
ብቻ የሚገርመዉ ሁሌ ሚያሳዝነዉ፥
የሰዉ ልጅ ከዚህም አለመማሩ ነዉ።
በዛች በላቲኗ በዛች ትንሽ ሃገር፥
ድንገት በደረሰ አይነተኛ ችግር፥
ዓለም ጉድ ተሰኘ ታየ በዙ ነገር፥
ታየ ድንገት መጥፋት ታየ ዳግም መኖር፥
በሰባ ቀናቶች ታየ ብዙ ነገር፥
የሰዉ ጥንካሬ የአምላክ ተአምር፥
የባንዲራን ትርጉም የሃገርን ፍቅር፥
የመሪነት ሚና የዜጎችን ክብር።
እንዲህ ነው ሃላፊ እንደዚህ ነው መሪ፥
ሃገር የሚያስጠራ ዜጎቹን አክባሪ።
ዜጋዉ ሲጎዳበት እንቅልፉን የሚያጣ፥
ከገባበት ገደል ቆፍሮ ሚያወጣ፥
ሲደሰቱ ስቆ ሲያዝኑ አብሮ አዝኖ፥
በረሃ የሚያደር የሆኑትን ሆኖ፥
እንደዚህ ነዉ ጎበዝ የወገኑ ፋኖ።
ግብዝ ዜጎች ገድሎ እሬሳ ሲከምር፥
ሌላዉ አንድ ሊያድን ሲጨነቅ ሲዳክር፥
ስንቱን ጉድ ታቀፈች አቤት እቺ ምድር!
ምናለ እነመለስ ከነዚህ ቢማሩ፥
በቀራቸዉ እድሜ ቁም ነገር ቢሰሩ፥
ከልፈታቸዉ በፊት አንድ ቅን ቢኖሩ!
በዚህ በጎ ስራ ምናለ ቢቀኑ፥
ከኮሪያ ገዝተዉ ዶክተር ከሚሆኑ፥
ለተንኮል ለልጥፋት እንዲህ ከሚፈጥኑ፥
በህዝብ ተወደዉ መሃይም በሆኑ፥
ወይም ቺሊ ሄደዉ ፍቅርን ባጠኑ።
አንዱዓለም በቀለ(ስዊዘርላንድ)
[email protected]