ብርቱካን ይቅርታ ከጠየቀች የመፈታት ዕድል አላት – መለስ ዜናዊ

የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በአካዳሚክ ማህረሰቡ ለአምባገነኑ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር የወይዘሪት ብርቱካንን እስር በተየመለከተና ሌሎች ተያያዥ የሰባዊ መብት ጥበቃ ለቀረበለት ጥያቄ የቀድሞውን እስርና የይቅርታ ሂደት ከተንተነ በኋላ በዳግም የይቅርታ ጥያቄ ካቀረበች የመፈታት እድሏ ከፍተኛ እንደሆነ ገለጸ።

በስብሰባው ላይ የተገኙ የውስጥ ምንጮች እንደገለጹት የተደረገው ስብሰባ በጣም ቀዝቃዛ እንደነበርና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንትም እንዳልተግኚ ለማወቅ ተችሏል።

ባጠቃላይ የስብሰባው ግዜ 45 ደቂቃ ብቻ የፈጀ ሲሆን 25ቱን ደቂቃ ስለአፍሪካ የወደፊት የልማት አቅጣጫ በመደስኮር ያለቀ ሲሆን ቀሪው 20 ደቂቃ በጥያቄና መልስ ተጠናቋል። ከጥያቄዎችም ጥቂቶች ውስጥ እትዮጵያ ክጎረቤት አገሮች ጋር በጋራ አብሮ በሰላም የመኖርን በተመለከተ፡የ2010 ምርጫ እንዲህም እስከመቼ በስልጣን ላይ እንደሚቆይ የመሳሰሉት ነበሩ። በጣም ከሚገርመው ስለ ኡጋንዳና ስለኬንያ እንዲህም ጂቡቲ የልማትና ትብብርን በተመልከተ በመግለጽ ሲያልፈው ነገርግን የህይወት መሰዋትንት የተከፈልበትን የሱማሊያ ጉዳይ ሳይዳሠው ቀርቷል።የ2010 ዓ/ም የምርጫ ውጤት በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ 99.6 ፐርሰንት እሱ በግሉ እንዳላገኘና 51 በመቶ በላይ ያገኙት የፓርላማ አባላቶች ናቸው ያሽነፉት በማለት የተምታታ ምላሽ ስጥቷል።በጣም የሚገርመው ጥያቄ የቀረበለት መቼ ነው የስልጣን ዘመንህ የሚያበቃው ሲባል እንደተለመደው ከዚህ ተርም በኋላ በስልጣን ላይ ለመቆየት ፍላጎት እንደሌለው ገልጾል።

በአጠቃላይ የአቶ መለስን የኒዎርክ ጉዞ የደበዘዘ እንዲሆንና በተቃውሞ እንዲጠናቀቅ የረዳው በዛሬው ዕለት ከአዳራሹ ውጭ የታየው ደማቅ የተቃውምሞ ሰልፍና እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ጥሪ ማድረግ አግባብ እንዳልነበር የተለያዩ በውጭ ሀገር ያሉ ምሁራኖች ጫና ተጽኖ እንዳሳደረ ለመገመት ተችሏል።በተቃውውሞ ሰልፉ አካባቢ ቁጥራቸው ጥቂት የሆኑ የስራአቱ አቀንቃኞች ተገኝተዋል። ውሎው ባጠቃላይ የትግሉን ዕንቅስቃሴ ወደነበረብት የሚመልስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነው ሲሉ አብዛኛዎቹ ሰልፈኞች ስናገሩ ተደምጥጠዋል።በመጨረሻም ሥር አቱ እስኪወድቅ ድረስ በይትኛውም ቦታ በመገኘት እንደሚያጋልጡ ቃል በመግባት ከዋሽንግተን ዲሲ፡ከቭቨርጂኒያ፡ከቦስተንና ከኬነቲኬት የመጡት ሰልፈኞች በሰላም ወደመጡበት ግዛቶች ተመልሰዋል።