ሞት ! እንዳትቀድመኝ! – ይፍሩ ኃይሉ

ሞት እኔ አልፈራህም አንተ ልማን ቀርተህ!
ግን ብትሰማ አድምጠኝ አለ የምጠይቅህ!

መጣደፍ፤ መቸኮል ትወዳለህና፤
ተንሽ አደብ ሰጥቶህ ሕ ሊና ግዛና፤
ቢቻልህ አትቸኩል፤ አትሩጥ ፤አትገስግስ፤
የልቤ እስኪሞላ ትንስ ጊዜ ታገስ።

ጊዜ ያበቀለው እሾህ ፤አሜኬ1ቅላ፤
የሕዝብ፤የሐገር ጠንቅ፤እንክርዳድ አተላ፤
የዘመኑን ኒሮ፤ ፋሽስት አረመኔ፤
አገርን የሚሸጥ ከፋፋይ ወያኔ፤
ከቀመጠበት ሲውርድ ተሽቀንጥሮ፤
በሕግ ተገዶ ከስልጣን ተባሮ፤
ከፍርድ ቤት ቀርቦ፡ “በል አስረዳ!” ሲባል፤
ግፉን በጠቅላላ የዋለውን በደል፤
ወንድ፤ሴት አላለ ወይ ወጣት ጎልማሳ፤
ለባልቴት፤ ለአዛዉንት ለማንም ሳይሳሳ፤
በጨካኙ ክንዱ በግፍ ላጨዳቸው፤
ደማቸው ደመ ከልብ እንዳይሆንባቸው፤
ዕዉነት መስክራበት ሲፈረድበት፤
“ዕድሜ ይፍታህ!” ወይ ሞት ሲበየንበት፤
እጅ እግሩን የፍጢኝ ታስሮ በገመድ፤
በተራው ሊማቅቅ ከርቸሌ ሲወርድ፤
ይህን ባይኔ ዓይቼ ልሙት በማግስቱ፤
እስከዚያ አደራህን እንዳትቸኩል ሞቱ።

ትራፊ ለቃሚን፤ አድርባይ ሆዳሙን፤
ሁሉን ቀባጣሪ፤ ለፍላፊ አዝማሪውን፤
ሰላይ፤ ፊርማቶሪ፤ ሠርጎ ገብ ተኩላውን፤

አርባ ሳዠልጠው ባኮርባች ጀርባውን
በሽመል፤ በዱላ ሳላገላብጠው፤
ምጥ እንዳያዛት ሴት ሳላንቆራጥጠው፤
ጊዜ ባለ ዉሉ ይህን ዕድል ስጠኝ፤
ግዳጄን ልፈጽም መብቴን አትንፈገኝ።

እንደተቆጣ ንብ ተነቃንቆ ቀፎው፤
ጊንጥ እባቡን ሆኜ ጠላቴን ሳንድፈው፤
በጥይት ሳልፈልጠው፤ ግንባሩን በመውዜር፤
እንብርቱን በሳንጃ፤ ሆዱን ሳልተረትር፤
ኩላሊቱን ሳልጠብስ፤ ሳንባውን ሳልመትር፤
የከሰለው ሆዴ፤አንጀቴ ሳይርስ፤
ያሰብኩት ሳሞላ፤ የልቤ ሳይደርስ፤
ሞት እንዳትቸኩል እዳታጣድፈኝ፤
ብዙ አልጠይቅህም ትንሽ ጊዜ ስጠኝ።

አሰብ ከሄደበት በግድ ተመልሶ፤
የጠፋው ስማችን ፤ ክብራችን ታድሶ፤
ኢትዮጵያን ሳናደርግ የወደብ ባለቤት፤
ይህን ባይኔ ሳላይ እዳትቀድመኝ ሞት።
አባይ ተገድቦ ኢትዮጵያን ሲያለማ፤
አርሲና፤ ሐረርጌ፤ ባሌና፤ ሲዳማ፤
ጎጃም፤አዳ፤ ብቾ፤ ቡልጋና፤ ሁመራ፤
በደንብ ለቶ አይቼው ሲትርፈን አዝመራ፤
እኛም በተራችን ለቸገረው ስንቸር፤
ኢትዮጵያ ለካንሳስ ስንዴ ስ ታበድር፤

የአፍሪካ ማፈሪያ መናጢ ድሃዎች፤
መባላችን ቀርቶ ሁል ጊዜ ለማኞች፤
መሰደድን ንቀን ስኖር ባገራችን፤
ሌሎች ስናስጠጋ እኛም በተራችን፤
ይህን ቀን ዓይቼ ልሙት በማግስቱ፤
ግድየለም ታገሰኝ አትቸኩል ሞቱ

አገር ሰላም ሆና አቧራው ሲረጋ፤
ሕዝብን የሚያገናኝ መንገድ ሳንዘረጋ
ሁስፒታል ተሰርቶ ክሊንክ ተስፋፍቶ’

ኮሌጅ፤ ዩኒቨርሲቲ በየትም ተሰርቶ፤
ይህን ሁሉ ዓይቼ ደስ ሳይለኝ!
አደራ እናትቸኩል ሞት እንዳትቀድመኝ!!

ትራፊ ለቃሚን፤ አድርባይ ሆዳሙን፤
ሁሉን ቀባጣሪ፤ ለፍላፊ አዝማሪውን፤
ሰላይ፤ ፊርማቶሪ፤ ሠርጎ ገብ ተኩላውን፤

አርባ ሳዠልጠው ባኮርባች ጀርባውን
በሽመል፤ በዱላ ሳላገላብጠው፤
ምጥ እንዳያዛት ሴት ሳላንቆራጥጠው፤
ጊዜ ባለ ዉሉ ይህን ዕድል ስጠኝ፤
ግዳጄን ልፈጽም መብቴን አትንፈገኝ።

እንደተቆጣ ንብ ተነቃንቆ ቀፎው፤
ጊንጥ እባቡን ሆኜ ጠላቴን ሳንድፈው፤
በጥይት ሳልፈልጠው፤ ግንባሩን በመውዜር፤
እንብርቱን በሳንጃ፤ ሆዱን ሳልተረትር፤
ኩላሊቱን ሳልጠብስ፤ ሳንባውን ሳልመትር፤
የከሰለው ሆዴ፤አንጀቴ ሳይርስ፤
ያሰብኩት ሳሞላ፤ የልቤ ሳይደርስ፤
ሞት እንዳትቸኩል እዳታጣድፈኝ፤
ብዙ አልጠይቅህም ትንሽ ጊዜ ስጠኝ።

አሰብ ከሄደበት በግድ ተመልሶ፤
የጠፋው ስማችን ፤ ክብራችን ታድሶ፤
ኢትዮጵያን ሳናደርግ የወደብ ባለቤት፤
ይህን ባይኔ ሳላይ እዳትቀድመኝ ሞት።
አባይ ተገድቦ ኢትዮጵያን ሲያለማ፤
አርሲና፤ ሐረርጌ፤ ባሌና፤ ሲዳማ፤
ጎጃም፤አዳ፤ ብቾ፤ ቡልጋና፤ ሁመራ፤
በደንብ ለቶ አይቼው ሲትርፈን አዝመራ፤
እኛም በተራችን ለቸገረው ስንቸር፤
ኢትዮጵያ ለካንሳስ ስንዴ ስ ታበድር፤

የአፍሪካ ማፈሪያ መናጢ ድሃዎች፤
መባላችን ቀርቶ ሁል ጊዜ ለማኞች፤
መሰደድን ንቀን ስኖር ባገራችን፤
ሌሎች ስናስጠጋ እኛም በተራችን፤
ይህን ቀን ዓይቼ ልሙት በማግስቱ፤
ግድየለም ታገሰኝ አትቸኩል ሞቱ

አገር ሰላም ሆና አቧራው ሲረጋ፤
ሕዝብን የሚያገናኝ መንገድ ሳንዘረጋ
ሁስፒታል ተሰርቶ ክሊንክ ተስፋፍቶ’

ኮሌጅ፤ ዩኒቨርሲቲ በየትም ተሰርቶ፤
ይህን ሁሉ ዓይቼ ደስ ሳይለኝ!
አደራ እናትቸኩል ሞት እንዳትቀድመኝ!!

ላንድነት፤ ለሰላም፤ ለሕብረት፤፡ለፍቅር፤
አንደበተ ጨዋ ተከብሮ የሚያስከብር፤
“ሐገሬ! ወገኔ!” የሚል መሪ ሲገኝ፤
ከዚያ እንደፈለገህ እንዳሻህ አድርገኝ።

ይፍሩ ኃይሉ
ነሓሴ 2002