ሰበር ዜና፤እስካሁን ባለዉ መረጃ በኢሬቻ በዓል ላይ የተገደሉ ወገኖቻችን ቁጥር ከ300 በላይ ሆኗል ቁጥሩ ከዚህም በላይ እንደሚያሻቅብ ተፈርቷል Satenaw October 3, 2016 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic በኢሬቻ የተገደሉ ወገኖቻችን ቁጥር እስከ አሁን ባለው መረጃ ከ300 በላይ ሆኗል የቆሰሉት እጅግ በርካቶች ናቸው ከሞቱት መካከል በዓሉን ከኦሮሞ ወንድሞቻቸዉ ጋር ለማክበር የተገኙ የአማራ ልጆች እንዳሉ ታዉቋል በዚህ ሰአት ኔትወርክ የተዘጋ ሲሆን ተቃዉሞዉ ወደሌሎች አካባቢዎችና አዲስ አበባና ሻሸመኔም ይዛመታል ተብሎ ተሰግቷል ከወደመከላከያ ፌደራል ፖሊስ አካባቢም አለመግባባት ተፈጥሯል እንዲሁም ደብረዘይት አየር ኃይል ዉስጥ የተኩስ ድምፅ ተሰምቷል::