ሰበር ዜና፤እስካሁን ባለዉ መረጃ በኢሬቻ በዓል ላይ የተገደሉ ወገኖቻችን ቁጥር ከ300 በላይ ሆኗል ቁጥሩ ከዚህም በላይ እንደሚያሻቅብ ተፈርቷል
- በኢሬቻ የተገደሉ ወገኖቻችን ቁጥር እስከ አሁን ባለው መረጃ ከ300 በላይ ሆኗል
- የቆሰሉት እጅግ በርካቶች ናቸው
- ከሞቱት መካከል በዓሉን ከኦሮሞ ወንድሞቻቸዉ ጋር ለማክበር የተገኙ የአማራ ልጆች እንዳሉ ታዉቋል
- በዚህ ሰአት ኔትወርክ የተዘጋ ሲሆን ተቃዉሞዉ ወደሌሎች አካባቢዎችና አዲስ አበባና ሻሸመኔም ይዛመታል ተብሎ ተሰግቷል
- ከወደመከላከያ ፌደራል ፖሊስ አካባቢም አለመግባባት ተፈጥሯል እንዲሁም ደብረዘይት አየር ኃይል ዉስጥ የተኩስ ድምፅ ተሰምቷል::
