በሶማሌ ተወላጆች የተረገጠውና የተቃጠለው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ኣላማ መነጋገሪያ ሆኗል። VIDEOS

በሶማሌ ተወላጆች የተረገጠውና የተቃጠለው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ኣላማ መነጋገሪያ ሆኗል።

በቅርቡ ኣሜሪካንን ጨምሮ በኣውሮፓ የሚኖሩና ኢትዮጵያውያን ሶማሌዎች ነን ያሉ የተወሰኑ ግለሰቦች የኢትዮጵያን ባንድራና የኦነግን ባንድራ ማቃጠላቸው ይታወሳል።እነዚህ ግለሰቦች ሕወሓትን ደግፈው የሕዝብን ትግል ንቀውና ኣሳንሰው በቅጥረኝነት ማንነታቸው ሳይታወቅ ኢትዮጵያዊ ቸዋነት የጎደለው ስራ መስራታቸው በኣለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቁጣና በቁጭን በመናገር ላይ ሲሆኑ ሃገር ቤት የሚገኙ የኢሕ አዴግ ኣባላት ለድርጅታቸው የተቃውሞ ደብዳቤ መጻፋቸው ተሰምቷል።

በውጪ ኣገር የሚኖሩ የኢትዮ ሶማሌ ተወላጅ ነን ያሉ ሕወሓትን ደግፈው በወጡት ሰልፍ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ኣላማ ማቃጠላቸው በኢሕ አዴግ ኣባላት ኣከባቢ ጥያቄ ማስነሳቱን ለድርጅቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል።

ጸረ ሰላም ሃይሎችንና ጽንፈኞችን ተቃውመው መውጣታቸው የሚደገፍ ቢሆንም የሃገሪቱን የረጅም ጊዜ መታወቂያ የኣፍሪካ የነጻነት ተያያዥ ሰንደቅ የሆነውን ባንድራ ማቃጠል የሰዎቹ ኢትዮጵያዊነት ከማጠራጠሩም በተጨማሪ ድርጅታችን የሃገሪቷን ገጽታ ግንባታ ላይ ነኝ እያለ የሚሄድበት መስመር በኣለም አቀፍ ደረጃ ታማኝነት ያጣል ሲሉ ለድርጅቱ የላኩት ደብዳቤ መግለጹን ለኢሕ አዴግ ጽ\ቤት ሰዎች ይናገራሉ።
[youtube http://www.youtube.com/watch?v=85sSPheE1UM&w=560&h=315]

[youtube http://www.youtube.com/watch?v=EdP9XQpMk5s&w=560&h=315]