ኣፈናና ዛቻ ያልበገራቸው የወሎ ወጣቶች ተጠናክረዋል።ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

ኣፈናና ዛቻ ያልበገራቸው የወሎ ወጣቶች ተጠናክረዋል። በደሴና ዙሪያዋ ያሉ ወጣቶችን የማፈኑ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል። የደሴ ዙሪያ ወጣቶች በተጠናከረ መልኩ ለሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ዝግጅት የተጠናከረ ሲሆን ኣስፈላጊ የሆኑ ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

ዛሬ ጠዋት ኮምቦልቻ ከተማ የታፈኑ ወጣቶች
1. ዘሪሁን ገሠሠ
2. ጀማል ኡመር
3. ተማም እና ሌሎችም ሥማቸው ያልታወቀ ወጣቶች በገፍ ታፍሠው ተወሥደዋል:: ዘሪሁን ገሠሠ የኮንቦልቻ ነዋሪ ሲሆን የወያኔ መንግሥት በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚያደርሠውን ግፍ በተደጋጋሚ በማጋለጥ ይታወቃል! በዚህ የተነሣ ከዚህ በፊት ታፍኖ ከሁለት ወራት እሥር በኋላ የተለቀቀ ነበር። ዘሪሁን ገሠሠ በደሴና በኮምቦልቻ ከተሞች የሚደረገውን ሠልፍ ያሥተባብራል በሚል ከፍተኛ ማሥፈራራትና ዛቻ ሲደርሥበት እንደቆየ ይታወቃል!

የዘሪሁን ገሠሠ የፍርድ ቤት ማዘዣ ይህን ይመሥላል። የተጠረጠረበት ወንጀል ግን ግልጽ አይደለም!! ያው እንደተለመደው ፍርድ ቤት ቀርቦ ወንጀል ይጋገርለታል ማለት ነው።የደሴ ዙሪያ ወጣቶች በተጠናከረ መልኩ ለሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ዝግጅት የተጠናከረ ሲሆን ኣስፈላጊ የሆኑ ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

Gashaw Mersha's photo.
Gashaw Mersha's photo.

ወያኔ በወሎ ከተሞች የሚደረገውን ሠልፍ ለማደናቀፍ የዘመቻ እሥር ከጀመረ ሠነባብቷል። አሁን ከመሸ በደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ ሐርቡ ከተማ ውሥጥ ብዛት ያላቸው ወጣቶች እየታፈሡ ነው። በዚህ ሠዓት አብደላ ሙሃመድ የተባለን ወጣት ከቤቱ ይዘውት ሂደዋል!!የደሴ ዙሪያ ወጣቶች በተጠናከረ መልኩ ለሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ዝግጅት የተጠናከረ ሲሆን ኣስፈላጊ የሆኑ ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ። እንግዲህ ሁላችንም ታሥረን እሥክናልቅ ድረሥ ትግሉ ይቀጥላል!

13 Comments on “ኣፈናና ዛቻ ያልበገራቸው የወሎ ወጣቶች ተጠናክረዋል።ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።”

  1. Ye Jawar lejoch ina ye Dimtsachin Yisema frefari lakamiwoch silalu xenqeqe yasflgal
    Shek Nurun yegdlu
    nachw.

  2. በተለያየ አጋጣሚዎችና ስፍራዎች፡ ሰላማዊ ሰልፈኛው፡ ፖለቲካዊ ተንታኙ፡ የዜና ሰዎች…ወዘተ፣ ወልቃዪት አማራ ነው የሚል መግለጫዎችና መፈክሮች እየተሰሙና እየታዩ ነው። ይሄ ደግሞ፡ በወያኔ ወጥመድ ውስጥ እንደመጠመድ ነው። ወያኔ ተቃውሞ ቢገጥመውም፡ ይሄን ዘረኛ አስተሳሰብ በማስረጹ በኩል የተሳካለት ይመስለኛል።
    ወልቃይት አማራ አይደለም፡ ጎንደር ነው – ጎንደር ኢትዮጵያዊ -አለቀ።

    ኤንደነ ፕሮፌሰር መስፍን ያሉ ኢትዮጵያዊያን በዚህ አገላለጽ ይስማማሉእሚ። ወያኔ ቢጥላም፡ እሱ ያመጣውን ዘረኛ ፖሊሲ እሚቀበሉ፡ ላሁኑ ተቃዋሚዎች፡ ለነገ የወያኔ ፖሊሲ አራማጆች እንዳሉ ማወቁና ለተራዘመ ትግል መዘጋጀቱ ሳይሻል አይቀርም።

  3. Please read the article on ethiomedia.com about the wolkait and tegedey what the tplf is planned to do. God bless Ethiopia and it’s people

  4. Birhanu Nega ahunim tiglun lemakolashet

    tenestowal gobez neka bel!

    jegnaw ye Gonder Hizb banesaw filmeya ,,

    Birhanu ke Oromo tegabtenal belo kk

    be tiglachin wuha lechelis new

    ye Oromo ena ye Amara andinet asdegtot ahun ke

    Merara ena ke yelikal gar tegabu kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk

  5. bayhon tiglun enakomalen enji

    Birhanu nega be Amaraw tigil

    be Amaraw dem teremamdo

    aymtsdekibinim !

    HAGERETU YE AWRE MEFENCHA TIHONALECH ENJI antema atkelidibinem !

  6. ኧረ ስድቡ ብታቆሙ ምናለ!? እኔ በአቡነ አረጋዊ ገዝቼአችኍለሁ ።አትሳደቡ ።

  7. ebacachihu yesemayawi party abalat ena lieloch ehadegin saywokilu mircha tewodadrew yeneberu sewochachin be semen wollo zon be habru woreda(wurgesa,mersa,woldiya enam wuchalen chemiro beteleyayu akebabiwoch )esirat eyetefetsemebachew new,enam lemimeleketew akal asawukachihu endifetu adrigulin…lelaw degmo erak wodale bota esirbet new yetewosedut,migbim lemadres minim addres magignet alchalnim…M negn ke wollo

  8. ትግሉ ቅርባችን ያሉትን የወያኔ ተላላኪዎች ማጥራት አለበት።ፍርፋሪ ለቃቃሚው መስመሩን ከህዝብ ጋር ማድረግ የግድ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*