በግብፅ ባለስልጣናቱ እገዳ ተጣለባቸው
ማንተጋፍቶት ስለሺ
የግብፅ ጦር በቀድሞ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሞባረክ 20 ታማኞች ላይ የጉዞ እገዳ አስቀመጠ። የጎዞ እገዳውን ያስተላለፈው የግብፅ ጦር ሲሆን፤ ባለስልጣናቱ ሀገር ለቀው እንዳይሸሹ በሚል ያስተላለፈው ውሳኔ እንደሆነም ተጠቅሷል።
ባለስልጣናቱ መጓዝ ከፈለጉም ከጦሩ ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ተጠቁሟል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሞባረክ የት እንዳሉ በውል ለማወቅ አልተቻለም። አንዳንዶች ሻርም አል ሼክ ወደተሰኘችው ሌላኛዋ የግብፅ ከተማ ተዛውረዋል ሲሉ ይደመጣሉ። የአረብ ብዙኋን መገናኛ ደግሞ ሙባረክ ከሀገር ወጥተው ወደ አውሮፓ፣ አለያም ከባህረ-ሰላጤው ሀገራት ወደ አንዱ ሳያቀኑ አልቀሩም ይላሉ።