የትግል ጥሪ ለመላዉ የኢትዮዺያ ህዝብ! ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ የአለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን

የትግል ጥሪ ለመላዉ የኢትዮዺያ ህዝብ!

ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ የአለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን

በነገዉ ቅዳሜ ሀምሌ 30, 2008 በመላዉ ኦሮሚያ በተጠራዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ህዝባችን በብሔር ፣ በዘር ፣ በቀለም ፣ በሀይማኖትና በፆታ ሳይከፋፈል የዜግነት መብቱን፣ ነፃነቱንና እኩልነቱን ለማረጋገጥ እንዲወጣ ጥሪ እናደርጋለን::

1. በዚህ ሰልፍ ህዝባችን የመቃወም ህጋዊ መብቱን በሰላማዊ መንገድ እንዲገልፅ ምንም አይነት ንብረት የማውደምም ሆነ ሌላ ግጭት እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንድያደርግ እናሳስባለን:ድጋፍ ቡድን:

2. መንግስት የሕዝቡን የመቃወም ህገ መንግስታዊ እንድያከብር እና ከለመደዉ የሀይል ተግባር እንዲቆጠብ እናሳስባለን:: ይህ ሰልፍ ለቀጣዩ ያገራችን ዕጣፈንታ፣ ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን የሚያመጣዉን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለዉጥ በማሰብ ህዝባችን በዚህ ወሳኝ ሰአት በፍቅር፣ በአንድነትና በጋራ በመቆም አምባገነናዊ ሰርአትን እንድንቃወም ጥሪያችንን እናቀርባለን::

ፍትሕ ፣ ሰላም፣ እኩልነት ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ!

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ የአለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን

ሚኒያፖሊስ፣ ምኒሶታ

ሐምሌ 29, 2008 ዓም