የሸንኮራ እርሻና የተፈናቃዮች አቤቱታ

የኢትዮጵያ መንግስት በቀጣይ አምስት ዓመታት ተጨማሪ የስኳር ፋብሪካዎችን በመገንባት ሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ቶን ስኳር ሐገር ዉስጥ ለማምረት እቅድ እንዳለዉ ተገልጧል። እቅዱ አሁን ያሉትን ሶስት ፋብሪካዎች ጨምሮ 12 የስኳር ፋብሪካዎችን መገንባት መሆኑን የወኪላችን የታደሰ እንግዳዉ ዘገባ ያስረዳል። አዳዲስ ለሚገነቡት ዘጠኝ የስኳር ፋብሪካዎች ሲባል፤ በተለያዩ የሐገሪቱ ክፍሎች ለሸንኮራ አገዳ ልማት በተመረጡ ቦታዎች ኗሪዉ ህዝብ ያለምንም ማካካሻ ተፈናቅለናል በሚል አቤቱታ እያሰማ ነዉ። የኢትዮጵያ የስኳር ኮርፖሬሽን በበኩሉ ያለማካካሻ ከመኖሪያ ቀየዉ የተፈናቀለ የለም ይላል። ታደሰ ዝርዝሩን አድርሶናል። ያዳምጡ