መሪዎቻችን እነማን ናቸው? አርቲስቶቹ ወይስ ታጋዮቹ?

አቤ ቶኪቻው

ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው ለዛሬው የፍትህ ጋዜጣ ጨዋታችን በዋነኛነት ይዤ የመጣሁት ጉዳይ መሪዎቻችን እነማን እንደሆኑ የሚጠይቅ ነው። ያው እንደተለመደው ሌሎች ጨዋታዎችም ይኖሩናል። አውራ ርዕሱ ግን “መሪዎቻችን እነማን ናቸው… አርቲስቶቹ ወይስ ታጋዮቹ?” የሚለው ይሆናል። “ለፓርቲ አውራ እንዳለው ሁሉ ለጨዋታም አውራ አለው።” እንልና ገዢው ፓርቲን ገልመጥ እናደርጋለን…