ቤተክርስቲያን ተጽእኖ ፈጣሪነቷን እያጣች መተማመን እየሰፋ በመምጣቱ በሲኖዶሱ ውስጥ ክፍተት ተፈጥሯል::

በፓትርያርኩ እንደራሴ አስፈላጊነት ከስምምነት ተደረሰ፤ “ወቅቱን የጠበቀ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፣ “ቅ/ሲኖዶሱ ተስማምቶ ካልወጣ ለሕዝብም ለሀገርም ጥሩ አይኾንም” ብለዋል

Ato kassa teklebirhan on holy synod gin2008በምልዓተ ጉባኤው ውሎ በተደረሰው መግባባት፤
  • የእንደራሴው መመዘኛ፣ ፓትርያርኩን የማገዝ ተግባሩና ሓላፊነት ደንቡ በቀጣዩ ጉባኤ ይታያል
  • በልዩ ጽ/ቤቱ፣ ለሥራ ዕንቅፋት የኾኑ ሰዎች ተነሥተው፣ እንዲስተካከልና እንዲረጋጋ ይደረጋል
  • የገዘፈ ችግር ያለበት የአ/አበባ ሀ/ስብከት፣ በረዳት ሊቀ ጳጳስ እየተመራ ሕጉ የሚሻሻል ይኾናል
  • ፓትርያርኩ፣ ስለወቅታዊ ኹኔታዎች ያላቸው አረዳድ ውስንነት ምደባውን አስፈላጊ አድርጎታል
  • ተግባር የሚሻው የልዩ ጸሐፊውና የጨለማ አማካሪዎች ግፍና አውዳሚነት አጽንዖት አግኝቷል፡፡
ሚኒስትሩ ስለአጀንዳዎቹና በውሏቸው እንደታዘቡት፡-
  • ከጥቅማጥቅም ጋር ሳይገናኙና ራስን ማዕከል ሳያደርጉ ጤናማ ውይይት ሊካሔድባቸው ይገባል
  • ጠንካራ ቅ/ሲኖዶስ፤ ጠንካራ አደረጃጀትና ፖሊሲ፤ አስፈጻሚና ፈጻሚ የሰው ኃይል ያስፈልጋል
  • እናንተ ናችሁ እኛን መደገፍ ያለባችሁ፤ ቤቱ ተኣማኒነቱና ተጽዕኖ ፈጣሪነቱን ማጣት የለበትም
  • በጨለማ የሚያማክሩት እነማን ናቸው? በእምነት፣ በምግባርና በዕውቀትስ ለቤቱ ይመጥናሉ?
  • አለመተማመን ይታያል፤ ይህ ፍጹም ክፍተት አምጥቷል፤ በጋራ መሥራት ይጠበቅባችኋል፡፡
የሚኒስትሩ እንደታዛቢ መጠራት፡-
  • ከቅ/ሲኖዶስ ልዕልና፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ከሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች አንፃር መነጋገርያ ኾኗል
  • የፓትርያርኩ ግትርነት ዋናው መንሥኤ ቢኾንም፣ ምልዓተ ጉባኤው በጥሪው መስማማቱ አስቆጥቷል
  • ጥሪው፥ “ኃይል አለኝ” ሲሉ የዛቱት ፓትርያርኩ፥ ለማስፈራሪያ በሚጠቅሱትና አዘውትረው ለርምጃ በሚማፀኑት አካል ፊት፣ ችግራቸውን የማስረዳትና ምልዓተ ጉባኤው በመጨረሻ የሚወስደውን አቋም ጠብቆ የግንቦት 2001 ዓ.ም. ዓይነቱ ግርግር ለመፍጠር የተዘጋጀውን የጨለማ ቡድን የማጋለጥ ዓላማ እንደነበረው ተጠቁሟል፤
  • በጥሪው፥ በእምነቶች የሰላምና የመግባባት ጉዳዮች እንዲሠራ ተልእኮ የተሰጠው ሚኒስቴር ሚኒስትሩ፣ በሃይማኖታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ያላቸው ቅርበት ከግምት መግባቱ የተጠቀሰ ሲኾን፤  በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ፥ የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ተግባር ከፓትርያርኩ ሥልጣንና ተግባር ጋር እየተነፃፀረ በብፁዕ ዋና ጸሐፊው ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፤
  • “ለምን ተጠራን አንልም፤ እምነታችን ነው፤ ቤታችን ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፣ ቤተ ክርስቲያን ለሀገር ያደረገችውን አስተዋፅኦ በመዘርዘር፤ ተኣማኒነቷንና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን እንዳታጣ፣ “ወቅቱን የጠበቁ ናቸው” ባሏቸው አጀንዳዎች ላይ በመተማመን ጤናማ ውይይት ማካሔድ እንደሚያስፈልግ ሐሳብ ሰጥተዋል፤
  • “ቤተ ክርስቲያኒቷ ከላይ እስከ ታች መጠናከር እንዳለባት ይገባኛል፤” ያሉት ሚኒስትሩ፣ አጀንዳዎቹም የተቀረፁት ከዚኽ አንፃር እንደሚመስላቸው ጠቅሰው፣ የእንደራሴ ምደባው ደንብና አፈጻጸሙ አስቀድሞ ተጠንቶና ከዋናው ሕግ ጋር ተጣጥሞ ለቀጣዩ ምልዓተ ጉባኤ ቢቀርብ፤
  • የአ/አበባ ሀገረ ስብከት የከበደና የገዘፈ ችግር እንዳለበትና መንግሥትም በቅርበት እንደሚያውቀው፤ ችግሩ፥ ለጊዜው፣ ባለው ሕግ ሰንሰለቱ ተጠብቆ እንዲፈታና በቀጣይም ከተጠሪነት አኳያ[የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የሚለው] በማገናዘብ ቢታይ፤
  • በልዩ ጽ/ቤቱ ለሥራ ዕንቅፋት የኾኑ ሰዎች እንዲነሡ ቀድሞም ከፓትርያርኩ ጋር ተነጋግረውበት እንደነበርና በአጀንዳ መካተቱ ትክክል እንደኾነ፤ መወሰንና በጎ ተጽዕኖ መፍጠር በሚችል የአስተዳደር ሰው ቢደራጅና ቢጠናከር የሚሉ ሐሳቦችን ሰጥተዋል፤ ቅዱስ ሲኖዶስ በእነዚኽ ጉዳዮች ላይ ተስማምቶና ወስኖ ካልወጣ፣ “ለሕዝቡም ለሀገርም ጥሩ አይኾንም” ሲሉም መክረዋል፡፡
  • Source Hara Tewahdo

4 Comments on “ቤተክርስቲያን ተጽእኖ ፈጣሪነቷን እያጣች መተማመን እየሰፋ በመምጣቱ በሲኖዶሱ ውስጥ ክፍተት ተፈጥሯል::”

  1. የዳግም አደዎ ዘመቻ
    ቁጥር 15 አሰቸኳይ የተሰጠ መግለጫ
    +-+++++++++++++++++++
    ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዋች) ኢትዮጵያን ሳያቋት በደመ ነፍስ 25 አመት በድርቅና ገዙ እንዲሁም ባንዲራችንን የጋኔን ምልክት አጣብቀወባት የብሔር እኩልነት ነው ብለውን እንደ አህያ እንድናስብ አረጉን። ኢትዮጵያ ከአለም በፊት 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበሯትን እነዚህ የሰው ባህሪይ የሌላቸው ጋኔኖች ኢትዮጵያ ሰው የላትም አሉን። ህዝባችን ሆይ አገራችን በየአቅጣጫው በረሀብ መከራ፣በስደት፣ተዋርደናል፣ታርደናል፣ ተገለናል። ሰለዚህ እስከ መቼ ይህንን ሰቆቃ እየሰማን፣ እየደማን፣ እየተገደልን፣ እየተገለልን፣ ባህር እየወስደን፣ መሪር ሐዘን መቼ ነው በኦሮሚያ፣ በአማራ፣በትግራይ ፣ በሱማሌ፣በደቡብ፣ በጋምቤላ የሚቆመው ? በመጀመሪያ ለሀያሉ አምላክ ሁሉም እንደእምነቱ ከልብ አምርረን ማልቀስ ያለንበት ወቅት ላይ ነን!!! አሁን በችግር ላይ ችግር የኢትዮጵያ ማዳን ጥሪ ጋር ሳንወድ በግድ ተፈጠናል ምክንያቱም ስንት ኢትዮጵያዊያን የተቀበሩበት ነፍስ የትም ብንሄድ የግድ ዝም ማለት አንችልም። አሁን ፓለቲካን አለወድምን የሚለው ሁሉ ቦታ የለውም። አንዳንድ ፓለቲከኞች ወይም እንዲሁም የአገር ስሜት የሌላቸው በሐይማኖት ስም ወጠጤ ለኢሕአዴግ የምትሰሩ ፓስተሮች በትግሉ ካልተሳተፉችሁ በተራ ወሬ ሕዝባችንን መከፋፈል እንድታቆሙ እንጠይቃለን። ወንድም ፓሮስቴታዊያን ዱሮ፣ዱሮ የወንጌል አገልግሎት እንጂ በዘፈን ወይም ቦርጭ ለማስቀነስ የሚል አልነበረም። 1000 አደዎዎቹ በትግራይ ህዝብ ላይ የከፋ በስውር የማይታይ ከሐውዜን ጀምሮ እከሌ ጠላት ነው እያሉት ህዝብን ለቨድዬ ሲሉ አስፈጅተዎል። ዛሬ ጥላሽት እና ደም የተቀባውን የመጨረሻውን ግንቦት 20 ኢሕአዴጎቹ በጥቅም ጉዳይ ምክንያት ለ3 ተከፈለዋል መሣሪያ መያዝ ላይ ለጠባቂዎቻቸው በስውር ቅደም ብለዋል። ከ10ኘ ክፍል ተስፋ ቢስ አድርጎ ያባረራቸው 30 ሚሊዬን ወጣቶች አባ ገበሬ ማፈናቀል ሴራ ወ/ሮ ገነት ምላሽ ሰንቆ በተጠንቀቅ ላይ ነው።
    1ኛ፣ አብዛኛው ጦሩ፣ሰለዮች ለኢትዮጵያ ተሰልፈው እየስሩ ነው። የኤፈርት ንብረት፣ የኢሕአዴግ አባላት፣ የገራፈዎች መረጃ በሙሉ በእጃችን ገብቷል። እነሱ 5ለ1 እኛ ደግም በራሳቸው ሰላይ 5ለ3 ምላጭ ሆነንባቸው። ከጦሩ ደግም ከ10 ለ7 የኛ ነው።
    2ኛ ኢሕአዴግ ለሱዳኑ አልበሽር $42 ሚልዬን ጉቦ ማስረጃ በኋላ አልበሽር በፍርሀት ሣምንቱን ስልክ በ ስልክ ሆነዎል ከወያኔዎቹ ጋር። የኤርትራ መንግስት በአንፃሩ የ 1000 አደዋዎች ጋኔኖችን ቀድሞ አውቆ ከእናንተ ይልቅ 90 ሚሊዬን የኢትዮጵያዊ ፍቅር ይሻለኛል ብሎ አንቅሮ ተፈቸው።
    3ኛ የ12ኛ ክፍል ፈተናው ለጦር መሪዎች ወጥቶ በስካር መንፈስ ፍልኋዋ እና የምግብ አደራሸ ውስጥ ተገኘ ከዚያም በሂሳብ ተስራጨ።
    4ኛ የታሀድሶ አቀንቃኝ ፣ ስውር መተተኛ፣ የነበረው ኑብረ ኡድ ኤልያስ የዘረፈውን ንብረት ለመንግሥት ሊያካፈል ነው። አቡነ ማትያስም መንፈሳዊ ስልጣናቸውን ለመንግሥት አስረከቡ የፈለጋችሁትን እንደራሴ መርጣችሁ የፅዬንን ታቦት አሰርቁ ብለው የመጨረሻ ከንቱ የረከሰ ሩጫቸውን ጨረሱ።
    5ኛ ኢትዮጵያ የምትፈልገው በእኩል አይን የሚያስተዳድር መሪ ብቻ ነው። ሕዝባችን ለሽግግር ለውጥ ተዘጋጁ ተራማጅ መረዎቻችን ደ/ር ብርሀኑ ፣ ጄ/ር ከማል ሰር ገብታቹ በአስቸኳት ትግሉን ተቀላቀሉ። አቶ ኦባንግ በአስቸኳይ ለህዝባችን የቅድመ/በኋላ ሸግግር ሥርአት መረጃውን የስተላልፈሉን። ተራማጅ ኦ/ማ
    ንጉሡ ሞቱማ የአምቦ ኮር አዛዥ።

  2. በሃገራችን መቼ ነው ስርቆት የሚቀረው?
    1- ጤፍ ተሰረቀ
    2- ቡና ተረሰቀ
    3- ብር ከባንክ ተሰረቀ
    4- ወርቅ ተሰረቀ (200ኪግ ወርቅ ባሌስትራ ሆነ ተሰረቀ)
    5- ልጆች ተሰረቁ
    6- ኮንዶሚኒየም ተሰረቀ( አረጉ፣ጠፋ)
    7- ስኳር ተሰረቀ
    8- መኪና ተሰረቀ
    9- ድንበር ተሰረቀ
    10- ታቦት ተሰረቀ
    11- ፈተና ተሰረቀ
    12- ወደብ ተሰረቀ
    ይህች ሃገር የማትሰረቀው ምን ምን ይሆን? ይህ ሁሉ መሰረታዊ ምክንያት ምንድን ነው ትላላችሁ?

  3. አኔ አህመድ ሴይድ አደም እባላለሁ ምስጋና ለነብያችን ከኢትዮጵያ ምድር ተፈጥርያለሁ። አብዛኛው ሙስሊም ማህበረ ስብ ና ኦርቶዶክሶችን በፍቅር ነው የምንወዳቸው ድሮ በጥሩ ኦርቶዶክስ በፍቅር የምትሰበስብ አገር እና ሰዎች አንደ ንጉስ ነጋሺ አይነት ባይኖሩ ኖሮ እኛ እስላሞች የለንም ነበር። ሰለዚህ ቤተ ክርስትያኗ ውስጥ ተሽግሸጋቹ ገንዘብ ያሰከራቹ እንኳን ኦርቶዶክሱ ይቅርና ሙስሊሙም አይምራቹም። ኦርቶዶክስ ለ ኢትዮጵያ ሙሲሊሞች የጌጣችን ጌጥ ነች!!!!!!
    ችግር ፈጣሪዎች ገንዘብ አስክሯቸው ሐይማኖተዋቸው የማያቁት የስድብ ጅኒ ያለባቸው ኦርቶዶክስ እና ሙስሊሞችን እየበጠበጡ ያለት ግራ የተገቡ ገንዘብ አፍቃሪ ፔንጤዎች ብቻ ናቸው። ጨዋ ፔንጤዎች እናከብሯችዋለን። ተጠንቀቁ ከእኩይ ስራቹ። አላ ኢትዮጵያን ይባርካት!!!!!!!!!!!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*