በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ: ፓትርያርኩ እስከ ነገ አቋማቸውን የሚያሳውቁበት የማሰላሰያ ጊዜ ተሰጣቸው

Abune Mathias perplexed

  • ከንግግራቸው በተፃራሪ በአማሳኞችና በተሐድሶ መናፍቃን ተጽዕኖ ውስጥ ወድቀዋል
  • የተጽዕኖው አስጊነት ምደባውን አስፈላጊ እንዳደረገው በምልዓተ ጉባኤው ታምኖበታል
  • ፓትርያርኩ፣ “ሌላ አለቃ ልታስቀምጡብኝ ነው ወይ?” በሚለው ተቃውሟቸው ውለዋል
  • በተቃውሞ ከጸኑ፣ ጉባኤው በአብላጫ ድምፅ ወስኖበት ሌላ ሰብሳቢ በመምረጥ ይቀጥላል

*           *           *

  • ቅ/ሲኖዶስ፣ የመጨረሻው መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ ሕግ አውጭ እና ወሳኝ አካል ነው
  • ሕጎችን ያወጣል፤ ያሻሽላል፤ ይሽራል፤ የአስተዳደር መዋቅርን ደረጃና ተጠሪነት ይወስናል
  • በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ የሚያሳልፈው ውሳኔም፣ የሕገ ቤተ ክርስቲያኒቱ አካል ይኾናል
  • ፓትርያርኩን በአመራር ለማገዝ ለሚሾመው እንደራሴ ምደባ፣ ዝርዝር ደንብ ይወጣል

*           *           *

  • ፓትርያርክ የሚባሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ የቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን አባት ናቸው
  • የፓትርያርክነት/ርእሰ ሊቃነ ጳጳስነት ሥልጣናቸው የአመራር እንጂ የክህነት ደረጃ አይደለም
  • ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው ያለአድልዎ የማስተዳደር እና የመምራት ሓላፊነት አለባቸው
  • ቤተ ክርስቲያንን ማስነቀፋቸውና ታማኝነት ማጣታቸው ከተረጋገጠ ከሥልጣናቸው ይወርዳሉ

*           *           *

በዛሬ፣ ግንቦት ፳፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከምደባው ጋር በተያያዘ ከምልዓተ ጉባኤው ውይይት የሚጠቀሱ፡-

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፡-
  • “በሕጉ እንደራሴ ይመደብ የሚል ሕግ የለም፤ ከሕጉ ውጭ ነው፤ ሕጉ ይከበር፤ እኔስ ምን አደረግኋችኹ? እየሠራኹ አይደለም ወይ? ከእኔ በላይ ሌላ አለቃ፣ ሌላ ባለሥልጣን ልታስቀምጡ ነው ወይ?”
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡-
  • “ምልዓተ ጉባኤው÷ ሕግ የማውጣት፣ የወጣውን የማሻሻልና የመሻር ከፍተኛ ሥልጣን አለው፤ ውሳኔውም እንደ ሕግ ይሠራል፤ የቅዱስነትዎም ተጠሪነት ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ ሓላፊነትዎ ከባድና ክፍተቱ ብዙ ቢኾንም የተሰጠዎትን ከመናገር በቀር ምንም አልሠሩም፤ ምክርዎም ከአማሳኞችና ከመናፍቃን ጋር ነው፤ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ እስከ ሀገረ ስብከትና አጥቢያ ድረስ ወርደው ሥራ አስኪያጅ፣ ጸሐፊ እና ሒሳብ ሹም ይመድባሉ፤ የምንሾመው የሚያግዝ እንደራሴ ነው፤ አንድ ብቻ ሳይኾን ብዙ ሊያስፈልግ ይችላል፤ ከዚኽ በፊትም በየዘመነ ፕትርክናው ሠርተንበታል፤”
  • እንደ ጉባኤው ሕግና ደንብ፣ አጀንዳው በድምፅ ብልጫ ሊወሰንበት ይገባል፤ ምልዓተ ጉባኤው 50 ለ1 ኾኖ መቀጠል የለበትም፤
  • ፕትርክናዎን ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ለቤተ ክርስቲያን ከሚያስቡ ጋር ሊሠሩበት እንጂ ከማይመለከታቸውና ከሚያበጣብጡን ጋር ሊመክሩበት አይገባም፤ ካልኾነ ሥልጣኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤
  • ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር መሥራትዎ ግድ ነው፤ ሕዝብ ይግባ፤ መንግሥት ይግባ ማለት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ሕገ መንግሥቱን አለማወቅ ነው፤ ማንም በማንም መግባት አይችልም፤ እኛም አንፈልግም፤
  • ቤተ ክርስቲያን በሕዝብ መካከል ኾና ኹሉንም በአንድነት የምትጠብቅ ችግር ፈቺና አስታራቂ ተቋም ናት፤ እነእገሌ ይግቡ፤ እነእገሌ ይምጡ የሚለው አስተሳሰብ የመከፋፈል አጀንዳ ያላቸው ሰዎች ከውጭ የሚረጩት ነው፤
  • ለረጅም ጊዜ በቤተ ክርስቲያንና በብፁዓን አባቶች ላይ ሲዘምቱ የቆዩ መናፍቃን፣ ስለአጀንዳው የሚያሰራጯቸው አሉባልታዎች፣ ፍጹም ሐሰትና ኾነ ተብሎ የጉባኤውን አቅጣጫ ለማስለወጥ የሚያናፍሷቸው ናቸው፡፡

3 Comments on “በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ: ፓትርያርኩ እስከ ነገ አቋማቸውን የሚያሳውቁበት የማሰላሰያ ጊዜ ተሰጣቸው”

  1. አንድ ቀን እንኳ መናቃንና ተሃድሶዎች ህግ እየጣሱ በቤተክርስቲያናችን ላይ እየፈጸሙ ስላለው ድርጊት ሲናገሩ ሰምቻቸው አላውቅም ይልቅስ ከነሱ ጋር በተለያዩ ጉባኤዎች ማለትም መንግስትም ሆነ መያዶች በሚያዘጋጁዋቸው ከመሳተፍ በስተቀር። አንድ ቀን ተናግረው ክሆነም አምልጦኛል። አንድ ቀን ቢደግሙ ግን ሳልሰማ አልቀርም ነበር። አንድ ቀን ብቻም ሳይሆን ደጋግመው መናገር አለባቸው። ስራቸውና ሃላፊነታቸው ምን ሆነና?!

    አለበለዚያ ግን ………

  2. Patrayaric tetrinetu me qdus sinodwosu newu patriyarku dgmo yhichin qdstna batakrstian chgran , bemftat yhim kemimelktachiwu yebate krsityan abatohi gar bemhon,endhum lmatan,twufitan sratan yemasketll halafinte yemigemrewu kegnbar kedemu meri (patriyark) newu negrgin yhichin qdst bate krsitiyan lemaqudem,lemtasi,lemserahir,abrewun dbelo lensewu keyamokun sewochi gar kemetebaber ylk yhichi batekrsityan lezihi endedereswchi,eyawokn ,beminafeaewu nfas kemenaqos ylk yelenbetn yemenfesawi,gdta mewotatvygebal.yhi sihon gin keqdusan abatochi,yebatekrsityan ljochi,mehon alebate .EGA eko bandane yealemawim sbseba endhihumbhugern yemimeleket guday tekesto patriyarku medrek sistaxhewu.kepoletikegochi baltwnamesw slepoletika yeworalu biyans kehizbu ylki patriyarku lemenfes kdus krb nachewu yemnefesawi. Gnbar kedem meri nachewu. Negr gin yeegIabhar talaknet gelso hageritan kemwbark ylk he may mell tax he win bamatm ngiggr ynagerlu yhi dgemo yewum yeorthodoz emnetaxhin merit ykrna lelawum amagi merit yemilewu aydel egam bemimerun patriyarik makerker yelebnm. Ylkunm komen lehad engi. Slzihi kdus sinodwosu yaskemetwu Susana try hone. Yalegi sgat wede hale enadatmelesu yemariam lgi eyeaus krstos yrdaxhi menfes kudus hulunm never ygletilachum besekot tgu. Entga..

  3. በአንድ ሃገር ስንት የሃይማኖት መሪ ነው የሚኖረው
    ምሳሌ፡
    1- በትግራይ ጳጳ አላቸው ለምን
    2- በአዲስ አበባ የሚኖረው ጳጳ አለ እንዴት ነው ነገሩ
    ይህ ሁኖ ግን የሚያሳዝነው ሕዝብ አብረህ አትኖረም እያሉ የሚሰብኩ አማኛች ናቸው ወይ
    እዩ ሃገሬ እየጠፋች ነው ያለችው ማን ያድናት ጎጠኞቹ ጠባብነታቸው አላማቸው ስለሆነ ኢትዮጵያን እያዋረዶት ነው!
    ተው መላ በል ወገኔ!

    አንድ ዘር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*