61 ኛዉ አለም አቀፍ የሲኒማ መድረክ- በርሊናለ

የጀርመን መዲና በርሊን ዛሪ ስድሳ አንደኛዉን አለም አቀፍ የፊልም ትዕይንት ማስተናገድ ይጀምራል። ለአስር ቀናት የሚዘልቀዉ ይህ የፊልም ትዕይንት በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ የፊልም ስራ አዋቂዎችን የፖለቲካ ሰዎችን እና ታዋቂ የህብረተሰብ አባላትን በመጋበዝ በተለያየ አለም አገሮች የተሰሩ ፊልሞችን በማወዳደር ሽልማት ይሰጣል!