የስኳር ፕሮጀክቶቹ ጡዘት እና የአርባምንጭ አከባቢ ግጭት የወለደው አዲስ ግርግር
የስኳር ፕሮጀክቶቹ ጡዘት እና የአርባምንጭ አከባቢ ግጭት የወለደው አዲስ ግርግር
#Ethiopia #EPRDF #TPLF #ANDM #ብኣዴን #MinilikSalsawi #SugerFactory
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የውሸት ካምፓኒው የሕወሓት አገዛዝ የደህንነት እና ወታደራዊ ተቋማት ባለስልጣናት አከባቢ ከበድ ያሉ ምስጢራዊ መረጃዎችን ለመያዝ ቢሞከርም በፍጹም እያፈተለከ መቸገራቸውን እና በሃገሪቱ ለሚነሱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አመጾች የኢሕኣዴግ አንዱ ቅርንጫፍ የሆነው የብኣዴን ካድሬዎችን ድምጻቸውን አጥፍተው ሊያጠፉን ነው በሚል በከባድ አትኩሮት ውስጥ እንዲዋልል ያደረጉት ሲሆን ብኣዴን የሕወሓትን የበላይነት እየተቅለሰለሰ ሊነጥቅ ነው የሚሉ ሕወሓታውያን እየበዙ መምጣታቸውን ከመጠቆሙም አልፎ ሕወሓት እንዲከስም በአገዛዙ ውስጥ የአማራው ሚና እየጨመረ ነው በማለት መነጫነጭ ጀምረዋል::
በሕወሓት አገዛዝ ሚዲያዎች የኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል የሚወጡ የተዛቡ እና የውሸት ምስሎች እና ዘገባዎች ከሕወሓት የደህንነት ቢሮ ተዘጋጅተው እንደሚላኩና በብኣዴን ሰዎችም ይህ ያልበሰለ ውሸት በደንብ ስለተደረሰበት የሕወሓትን ቅጥፈን በማጋለጥ ረገድ በመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የሚሰሩ የብኣዴን ልጆች ላይ ከንፈር ሲነከስ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ካለፍርሃት እያመጣቸው የሚገኙ ሕዝባዊ ጉዳዮች ለፌዴራል መንግስቱ የሕወሓት አገዛዝ ከፍተኛ ጋሬጣ እና ስጋት እንደፈጠሩ በደህንነት ተቋማት በኩል ሕወሓቶች እየጮሑ እንደሚገኙ ተሰምቷል::ባለፈው ሳምንት በአርባምንጭ የተነሳውና የቴፒ ወጣቶች የትግል አካል ሊሆን ይችላል ተብሎ የታሰበው የግንቦት ሰባት ፓርቲ ሃላፊነቱ የኔ ነው ያለበት በሌሎች ዘንድ ሕዝባዊ አመጽ እንደሆነ የሚነገርለት የሕወሓት ዘረኛ ካድረዎች የኤርትራን መንግስት የወነጀሉበት ሕወሓት-ሰራሽ ይህ ግጭት ከቀናት በኋላ እዛም እዛም ሲጠቋቆምበት የነበረውን ጣቶቹ ወደ ብኣዴን ካድሬዎች ማዞሩ በሕወሓት እና ብኣዴን ውስጥ የቀድሞው አካል የሆነና ከበፊቱ ሾኬ በተሻለ መልኩ አዲስ ያለመተማመን መንፈስ እየሰረጸ እንደሆን ያሳያል::ጥቂት ሆዳም የሆኑ የፓርቲ አመራሮችን ቀብረን የብኣዴንን ሕልውና እናረጋግጣለን የሚሉ የብኣዴን ካድሬዎች ምንም እንደማያውቁ በመምሰል እየተቅለሰለሱ ሊፈጁን ነው በትግራይ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ሊታወጅ ነው ምናምን እያሉ የሚቀባጥሩ የሕወሓት ካድሬዎች እና ተባባሪዎቻቸው እያፏጩ ይገኛሉ::
ከፖለቲካው ግርግር ጎን ለጎን ይህን ሰሞን ከስኳር ፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ የብኣዴን ሰዎች ደህንነቱን እና መከላከያውን መቆጣጠር ቢያቅታቸው ባለስልጣኖቻችንን እየወነጀሉ ነው ሲሉ አሁንም የሕወሓት ሰዎች አማረው ያለቅሳሉ::በፍጹም የማይሳካ እና ለዘረፋ ብቻ ተብሎ የተቋቋመው የስኳር ፕሮጀችት አንዱም ሳይሰራ ሃገሪቷን ለከፍተኛ እዳ እንዳጋለጣትና የጥቂት ሕወሓት ባለስልጣናትን ኪስ እንዳደለበ እየታወቀ የሕወሓት አናት የሆኑ በሰሩት ከባድ ጸረ ሃገር ወንጀል ራሳቸውን ለመደበቅ ካድሬዎቻቸውን በማሰማራት የብኣዴን ሰዎችን ለመብላት አሰፍስፈው ይገኛሉ::በከፍተኛ ሙስና የሚዘፈቁት ሕወሓቶች መሆናቸው እየታወቀ የሚታሰሩ እና የሚንገላቱ ግን የብኣዴን አማሮች እንደሆኑ ካሁን ቀደም የታዩ ተሞክሮዎች ምስክሮች ናቸው::አሁንም በተዘዋዋሪ ይህን ለመድገም ሕወሓቶች እየተሯሯጡ ነው::
ሕወሓት በስልጣን ላይ እንዲቆይ የሚሹ ተቃዋሚ መሰል አሾክሻኪዎች ሳይቀር ለለውጥ የሚደረገውን የፖለቲካ እና የኢኮኒሚ ትግል አፈር ለማስገባት ከሌቦች እና ከገዳዮች ጎን ቆመው ሲያፏጩ ማየት ያሳፍራል::የመከላከያ ኢንዱስትሪ(ሜቲክ)እና አመራሮች የሕወሓት ጄኔራሎች ቅርጥፍ አድርገው ለበሉት ገንዘብ የብኣዴን አባላት እንዲቀሉ እየተፈረደባቸው ይገኛል:: አርባምንጭ ላይ ለፈነዳው አመጽ በየጊዜው በስብሰባዎች የሚቀርቡ ጸረ ሕወሓት ሰዎች ሪፖርት የብኣዴን እጅ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል በሚል በሕወሓት መራሹ የደህንነት ተቋም ሪፖርት እየተዘጋጀለት ነው::የአርባምንጭ አመጽ እና የስኳር ፕሮጀክቶቹ ጡዘት የወለደው አዲስ ግርግር ወዴት እያመራ ይሆን ??? #ምንሊክሳልሳዊ

The start of the end….
Sile babur sayawku babur megenbat, sile sikuar factory sayawku factory megenbat alu prof…..
MeToz = mefendeq, menar, medrar, mekrer, maTadef, gura melqeq ?
TPLF is a collection of thieves . We don’t expect good things from woyana. Thieves are always thieves. The only solution is all Ethiopians should stand together to remove this cancer mafia group from our motherland Ethiopia .
ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሀል ይባል የለም እንዴ
ለኢትዮጵያ ውድቀት የማተኛ ማን አለ ? ሁሉም በተቻው የሃገር ባህል፣ወግ፣ሃይማኖት ለመሸርሸር በጡት ነካሾች አሰተባባሪነት ከውጭ ተላላኪዎች ዋና ተግባራቸው አድረገው እነሆ ዛሬ ቃና መጣላችሁ ተዝናኑ ወጣቱ ትምህርት ቤት መሄዳቸውን አቁመው እናቶች ወጥ ለመስራት ድስት ጥደው ማቃጠል ይባስ ብሎ ለእሳት አደጋ እየተጋለጡ ናቸው፡፡ ይህችን ሃገር ማን ይታደጋት ?
ሳተናው አሊ
RIP Ethiopia.RIP Ethiopia.RIP ethiopia.Ripppppppppppppppppppppppp
Be amara atinegidu amara min bota alewina weynen yishereshral bene
Berket Simon new ymeshreshrew tewu ebakachihu wishet atawiru.
Ayikerm
Who is Amara in ANDM?
BEREKET? ADISU LEGESE? YOSEF HILAWE? TEFERA walwa ?????
Bulls hit article
የስኳር ፕሮጀክት ቀውስ አላችሁት ቀውስ መሰላችሁ እንደ የተወሰኑ ሰዎችን ኪስ ማበልጸግ እና ቀጣይ ስራቸው ደግሞ የሃገር ውድመት ማለት ይቀላል!
የተንዳሆ የስኳር ፕሮጀክት አጀማመሩ እቅድ አልነበረውም በወያኔ አስተሳብ ለመሆኑ ወያኔ ኢትዮጵያን/ኢትዮጵያዊያን/ ማጥፋት እንጅ እቅድ ብሎ ነገር የሚገባው ፍጡራኖች አይደሉም፡፡
የተንዳሆ ፕሮጀክት በአለፈው መንግስት ማለት በደርግ ዘመን ማለትነው የተዘጋጀው ለጥጥ እርሸ እንጅ ለስኳር እርሻ አልነበረም ምክንያቱም ጥጥ እንደ ስኳር ብዙ ውሃ አይፈጅምና ያለውን የውሃ ሃብት መጠን ለምን አይነት ሰብል ስንት ውሃ ያስፈልጋል የሚለውን ሙያዊ አስተያየት በጥንቃቄ መስራት ታስቦ የተዘጋጀ ነበር አሁን ግን እቅድ የሚያቅደው ማን ነው እንደት የሚለውን የሚያዮበት ጭንቅላት ይባስ ብሎ እኮ በኢትዮጵያ ላይ የሸፈቱ፣ያደሙን፣የከፋፈሉን፣የነጠቁን ናቸው!
በኢትዮጵያ የስኳር ፕሮጅከቶች ሃላፊነት የማን ነው? ከሌለ ግን አሁንም ሃገሪቱ በዜጎች እጅ አለመሆኗን ይታወቅ!
ስለዚህ የስኳር ፕሮጀክት ውድቀት ወያኔ፣ሽፈራው ጃርሶ፣አስፋው ድንጋሞ በድብቅ ያሉ ዜጎች ለጥፋቱ ለውድቀቱ ተባባሪዎች ቤቱ ይቁጠረው!
የስኳር ጉዳይ ጠያቂም ተጠያቂም የለውም!
በስሜት ብቻ መጎዝ!
ሃገሪቱ ባለቤት የላትም!
በአጠቃላይ ፕሮጀክቶች ሁሉ የውሽት መፍለቂያ በረት ናቸው!
ሃገርንና ሰው ገዳዮች ናቸው!
እኛ ብቻ እንኑር ይላሉ ጎጠኛቹ ሁሉ!
አሰፋ