“የሰሜን ሱዳን ወታደሮች በተራቸው ኢትዮጵያን ጥሰው ገብተው እያፈኑ መውሰድ ጀምረዋል” ቪኦኤ

“የሰሜን ሱዳን ወታደሮች በተራቸው ኢትዮጵያን ጥሰው ገብተው እያፈኑ መውሰድ ጀምረዋል” ቪኦኤ
++++++++++++++++
ከጥቂት ወራት በፊት : የ ኤርትራ ወታደሮች ወርቅ ለማውጣት ይቆፍሩ የነበሩ በርካታ ወጣቶችን ታፍነው መወሰዳቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ገልጾ ነበር:: ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ ዩኒፎርም የለበሱ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን ገድለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕጻናትን አፍሰው መውሰዳቸውን አሁንም የኢትዮጵያ መንግስት ገልጿል:: አሁን ደግሞ የሰሜን ሱዳን ወታደሮች ቤንሻንጉል ድረስ ገብተው በርካታ ኢትዮጵያውያንን አፍነው ወስደው ሱዳን እንዳሰሯቸው እና ሌሎቹም የት እንደገቡ እንደማይታወቅ ባለሀብቶች እየገለጹ ነው::
ቀጥሎስ ተረኛው ማን ይሆን? የጅቡቲ ወይስ የኬንያ ወታደሮች?

አልኑር በሽር ሲባል በቆየ በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል በጉባ ወረዳ በኦሜድላ ቀበሌ ባለ እርሻ ልማት ላይ የሚሠሩ 22 ሠራተኞች በሱዳን ወታደሮች ተጠልፈው መወሰዳቸውን የእርሻ ልማቱ ባለቤት ነኝ ያሉት አቶ ይርሳው የሺወንድም ተናግረዋል።

5 Comments on ““የሰሜን ሱዳን ወታደሮች በተራቸው ኢትዮጵያን ጥሰው ገብተው እያፈኑ መውሰድ ጀምረዋል” ቪኦኤ”

  1. አሁን ሁሉም ንገር እዚህ ላይ ያብቃ ወሬ ይብቃ ተገደለ ታሰረ የሚለው ወሬ ማነው የሚፈራው እኛም ጠመንጃ ይዘን እንፋለም ተነስ አይንህ እያየ ከቤትህ እያወጡ እንደበግ እስከሚያርዱህ አትጠብቅ

  2. ክላይ የጻፍከው ጥሩ ብለሀል ባርነት የጠላህ ህዝብ ባለህበት እገር እነዚህን ወንጀለኞች ተፋለም ይህ እርምጃ ዛሬ ካልሆነ ጊዜው ይመሽብሀል። እነዚህ ዘረኞች የህዝብ ክብር ስለ ሌላቸው አንተም እነሱን የማክበር ግዴታ የለብህም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*