የነዳጅ እጥረት በአዲስ አበባ

አብዛኛዎቹ የአዲስ አበባ ነዳጅ ማደያዎች ዛሬ ለደንበኞቻቸው የተለመደውን የነዳጅ ሽያጭ አገልግሎት ማስጠት ማቆማቸውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ታደሰ እንግዳው ዘግቧል ። ምክንያታቸውም ኢታኖል የተደባለቀበት ነዳጅ የለም የሚል ነው ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት በበኩሉ ምንም ዓይነት የነዳጅ ዕጥረት የለም ባይ ነው ። አሁን በከተማዋ የታየው የነዳጅ እጥረት የተከሰተው የነዳጅ ዘይት ኩባንያዎች ዋጋ ይጨምራል በሚል ነዳጁን ይዘውት ሊሆን እንደሚችል የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።
ያዳምጡ [podcast]http://dw-world-od.streamfarm.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/36A3F0D1_3.mp3[/podcast]
ታደሰ ዕንግዳው ፣ ሂሩት መለሰ አርያም ተክሌ