ማንን እንመን ለወሣኙ የነፃነት ትግል ? በሎሚተራተራ
መቼም ዘንድሮ የማንስማው፤ የማናየው ጉደ የለምና ከሃያ አመት በኋላም መሪነን ተብዬዎች ሕዝብን አቅጣጫ ማሥያዝ አቅቷቸው በጥርጣሬና በግራ መጋባት እንደገና ወደ ኋላ እንድናፈገፍግና የተቀጣጠለው የነፃነት ትግል እንዲዳፈን ጥረት ማድረግ በርግጥ ተገቢ ነው?። ሕዝብም እምነት በማጣትና በጥርጣሬ ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሆነ ግን እንድትረዱ ያስፈልጋል።
ለምን ሕዝብ በመሪዎቸ ላይ እምነት አጣ ? ቢባለ እንደሚከተለው ነው።
እንጂነር ሃይሉ ሻዎልና Dር ብርሃኑ ነጋ የግንቦቱን 97 (2005) ምርጫ ውጤታማ ማድረግ ሲችሉ ከመሰሎቻቸው ጋራ ባለመግባባትና ወሣኝ አቆም መውሰድ ባለማቻል ምክነያት ሕዝብ የወያኔን ጉሮሮ አንቆ ሊያወርደው ከደረስ በኋላ አከሸፉት፤ አስከሽፉት። “ወያኔ አጭበርብሮቸው ወይስ አስፈራርቷቸው ምን እንደሚባል ሕዝብ ይፍረደው”። ግን የፖሎቲካ መሪ ናቸው ይህን እንዳትረሱ? ።
ትግሉ ግን አሁንም በሕዝብ እጅ ላይ እንደወደቀ መሪነን ተብዬዎቸ ጠንቅቀው ሊረዱ ያስፈልጋል።
በመጨረሻም ኢንጀነር ሃይሉ ሻዎል ማጎንበሱን መረጡ ። እነ Dር ብረሃኑም ወደ አሜሪካ ማራቶን አደርገው ተሳትፈው በማያውቁበት ሽልማትም ባላገኙበት በማራቶን አሜሪካ ገቡ። ምስኪኖ ብርቱካንም ቆራጥነቷን በጀግንነት ካሣየች በኋላ አይዞሸ የተባለችበት የትግል አጋሮቾን አቋም ስታይ እንደ መከላከያ መሣሪያ እንደተጠቀሙባት ስለገባት ከእስር በኋላ አዎ ሚስጥሩ ገብቶኛል መጀመሪያውንም ስህተት ነው የስራሁት ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ስህተት አልሰራም በሚል ፈርማ ከ እስርም ከትግሉም ጨዋታ ወጣች።
ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላም የሃገር ጉዳይ በመሪ አጣሁ ባይነት እንደማይቀር የገባው ሕዝብ ትግሉን ቀጠለ።
ይህ በዚህ እንዳለ የቱኒዝና የ ግብጹ ትግል እንቅስቃሴ የ ሕዝብን የተዳፈነ እሣት ቀስቅሦት የነፃነት ትግሉ ችቦ መቀጣጠል በጀመረ ማግሥት እነ Dር ብርሃኑ እትዮጵያዊ አይደለንም፤ ካሉትና እራሣቸውን (OLF) እና (ONLF) ብለው ከጠሩት ጋራ ድርድር አድርገን ተስማምተናል። በጋራም ወያኔን ለመጣል አብረን መስራት እንችላለን። በሚል ሃሳብ “በ ኢሳት ቴሌቪዥን” ኢንተርቪው አደርጉ። ሳይውል ሳያድርም ስልፍ ከ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጋራ ቀይ ባንዲራ ይዘው ወጡ።
እረንጎዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራችን በሌላ ቀይ ባንዲራ ታጅቦ መፈክሩ ቀለጠ ። የተለያዩ የምዕራባዊ አገሮችም ይሄ ባንዲራ የማነው ? ይሄኛውስ ? እያሉ በግራ መጋባት እየሣቁ አለፉ። ጥቂት የዋህ ኢትዮጵያዊያኖች አንድ እርምጃ ተራምደናል አሉ። በርካታዎች ግራ በመጋባት እራሳቸውን ነቅንቀው አዘኑ። በቅርቡ ወረሃዊውን ድጎማዬን ለማድረግ ወደአገርቤት ደውዬ ኖሮ በቅጡም ስላምታ ሳንለዋወጥ ውርጅብኙ ቀጠለና ፤ምነው አረንጎዴውና ቢጫው ቀዩ ባንዲራችን መሃል በተደነቀረው ኮከብ ተበሣጭተን ሣናባራ ምንድነው እየተደረገ ያለው በሚል ንዴታቸው ገነፈለ። ቀጠሉናም ስሞኑን በየ ቦታው የዳይስፖራውን የፖሎቲካ የስልፍ ትዕይንት ጉዳይ ነው በእሳት በምትሉት የ ቲቪ እስቴሽናችሁ እያየን የምንስቀው ሲለኝ ወንድሜ በብስጭት፤ ተወኝ እባክህ ብዬ ብዙም ሳላወራው ስልኩን ዘጋሁ።
እንደገና ወድኋላ ትግሉ እንዲሄድ የሚደረገበት ምክነያት ግን ምን ሊሆን እንደሚችል ፍርጥ አርጎ ማንም ሊናገር አልቻለም። ኢትዮጵያዊነት ለድርድር መቅረብ የለበትም ብሎ የሚከራከረው “ናሺናሊስት” ( ግትር አክራሪ አማራ) እየተባለ የሚፈረጅበት ምክነያት ግን በጣም የሚያሣዝን ነው። ገሚሱ ትክክል ነው ይላል። ገሚሱ ጥፋት ነው የተሰራው ይላል። ኢትዮጵያዊነት ለድርድር የሚቀርብበት ምክነያት ለምን ይሆን? ብሎ መጠየቅ ግን ተገቢ ነው ባይ ነኝ። በታሪክ ታፍራና ተከብራ በ አባቷቻችን ደምና አጥንት የቆየችን አገር ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ከሚል አካል ጋራ አብሮ መቆሙ በርግጥ አስፈላጊ ነው? ። ወይስ መቅደም ያለበት አዎ እትዮጵያዊነታችንን ተቀብለናል ሌላው ችግራችን ግን ኢትዮጵያን ከ ወራሪው ወያኔ መንጋጋ ካለቀቅን በኋላ በጋራ ልናስተካክል እንችላለን በሚል ተግባብቶ የ ኢትዮጵያን ባንዲራ ይዞ አብሮ መቆም ?።
ይሄን እነ Dር ብርሃኑ ይመልሱት። እንደ እኔ እምነት ከ ወንድሞቻችን ጋራ ለምን ድርድር ተደርገ አይደለም ጥያቄው። ሆኖም ወያኔም ኢትዮጵያን እየጠላ ባንዲራችንንም ጨርቅ ነው እያለ አይደለም እንዴ?። ሕዝብንም እያፈነና እያስረ መከራ ስለሚያሣየን መስለኝ ትግላችን ፤ ታዲያ የነ (OLF) ጉዳይ በምን ሂሣብ ስሌት ነው እትዮጵያዊ አይደለንም ብለው ባደባባይ እየነገሩን አብረው መሰለፋቸው? መሪዎች ተብዬዎችስ የወያኔ መጠቀሚያ ሊያደርጉን ? ወይስ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው በሚል ቸልተኝነትና አፍራሽነት ከነፃነት በኋላ ሌላ ልንወጣ ወደማንችልበት አዘቅት ውስጥ ሊከቱን ? ወይስ በርግጥ ሊያስማሙን ? ምን ይመስላችኋል? ።
አቶ ሌንጮስ ኢትዮጵያዊነትን አምኖ ከህዝብ ጋር በመቆም ችግር አለኝ ቢባልም እንኳን ከነፃነት በኋላ በ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በጋራ መፍትሄ ማምጣቱ አይበጅም ይላሉ? በስተርጅና እንዲህ ያለ የ አፍራሽ ተልዕኮ ማራመድ ተገቢ ነው? ማንስ ይቀበለኝል ብለው ነው? እርሦ እራሦት ይመልሱ።
በመጨረሻም የ ኢትዮጵያ ሕዝብ ከየት እንደመጣ የት እንዳለና ወዴትም መሄድ እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። አሁንም ማን ይምራኝ ከማ ጋር ልቁም የሚለውን የሚወስን እሱ እራሱ ነው። የተጀመረውንም የነፃነት ትግል እራሱ አቀጣጥሎ እራሱ መሪ ፈጥሮ በድል ይወጣዋል። መሪ ነን ያላችሁ በሕዝብ መነጽር ውስጥ ነው ያላችሁትና እራሳችሁን አስተካክላችሁ ሳይመሽ በጠዋቱ ከሕዝብ ጋር መቆም ትችሉ ዘንድ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ
እላለሁ።
የተጀመረው የነፃነት ትግል በሕዝብ የበላይነት የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፊት አስቀድሞ በድል አድራጊነት ይወጣዋል!።
በቸር ይግጠመን
ሎሚተራተራ !