ሰበር ዜና: – አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) (የእምነት ክህደት ቃል ) ከነገ ጀምሮ ዲሲ ፍርድ ቤት ይሰጣሉ።
(አዲስ መረጃ ተካቷል ) ሚያዚያ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. (April 11, 2016)

ይህንን ጉዳይ እየተከታተልን አዳዲስ መረጃዎችን እናቀርባለን ባልነው መሰረት አሁን የደረሰን አዲስ መረጃ እንደሚያመለከተው የከሳሽ ወገን ጠበቃ ጥያቄዬን ጨርሻለሁ ብሎ እስኪያበቃ ድረስ የእምነት ክህደት ቃል በተከታታይ ብዙ ቀናት ሊቆይ የሚችል እንደሚሆን መረጃው ያሳያል።(አቡነ ፋኑኤል ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የከሳሽ ጠበቃ ያለ ሰዓት ገደብ የሚፈልገው ጥያቄ እንዲጠይቅ የታዘዙበት የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ):: ቀደም ብሎ የዘገብነውን ቀጥሎ ማየት ይቻላል።
ስለፍርድ ቤቱ ቀጠሮ የሚቀጥለውን ይመልከቱ። http://www.mereja.com/amharic/490212
ስትንሽ ስለ አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) አዋናባጅነት ከዜና ማህደራችን- ቀጥሎ ይመልከቱ። http://www.mereja.com/amharic/491127
እባካቹ እናስተውል።ወርቅ በእሳት ክርስትያን በመከራ ገዜ ይፈተናል።ሰው ባያየን እግዛብሄር ያያል።ለመሆኑ ለውጥ ከየት ይጀምራል? ለውጥ ክራስ ይጀምራል። በሌላው ላይ እጅ ከመቀሰር መጀመሪያ እራስን መመርመር እንዴት መልካም ነበር።ሰው እንደመሆንናችን መጠን ከሁላችንም ስህተት አይጠፋም።እውነት ትመነምን እንደሆን እንጂ አትበጠስም።እውነት እንነጋገር የሆድ የሆዳችንን እናውጋ ካልን ዛሬ እኛ ሰልጥነናል ውይስ ሰይጥነናል ነው የምንባለው። በአፋችን የምናውራ ስለ አንድነት፣ስለህብረትና ስለፍቅር ነው። በተግባር ደግሞ አንዱ ያንደኛውን ገድጓድ ይምሳል።ቤተመቅደሱ ይእግዛብሄር ማደሪያነቱ ቀርቶ ለልጆቻችን የምናወርስው ቋሚ ንብረት የሚመስለን ጥቂቶች አይደለንም።ዛሬ ብንጣላ ነገ መስማማታችን አይቀርምና ክፋ ቃል ከአፋችን አይውጣ።እግዛብሄር ያለው ሁሉ በቀኑ ሊፈፅም ግድ ነው።እርስ በራስ ከመጠላለፍ ይልቅ እግዛብሄር ፍቅርን እንዲሰጠን አጥብቀን እንፅልይ።ለሁላችንም እግዛብሄር ምማስተዋልን ይስጠን። አሜን።