የእንግሊዛዊው ባለቅኔ ዊሊያም ሼክስፒር የራስ ቅል ከመቃብሩ መዘረፉ ተረጋገጠ
ከ400 አመታት በፊት ከዚህ አለም በሞት የተለየው እንግሊዛዊው ባለቅኔ ዊሊያም ሼክስፒር የራስ ቅል ከመቃብሩ ውስጥ ባልታወቁ ዘራፊዎች መሰረቁ በአርኪዎሎጂስቶች ጥናት መረጋገጡን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ፡፡እንግሊዛውያን ተመራማሪዎች በስታንፎርድ የቅዱስ ስላሴ ቤተክርስቲያን ውስጥ በሚገኘው የዊሊያም ሼክስፒር መቃብር ላይ ባደረጉት የራዳር ፍተሻ፣ የባለቅኔው የራስ ቅል መቃብሩ ውስጥ እንደሌለ ማረጋገጣቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ የመቃብሩ የላይኛው ክፍልም ከረጅም አመታት በፊት ተከፍቶ እንደነበር የሚያሳይ ምልክት መገኘቱን ገልጧል፡፡
በዚሁ ምልክት ላይ በተደረገ ምርመራ፣ የራስ ቅሉ የተዘረፈው በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሳይሆን እንደማይቀር መገመቱ የተነገረ ሲሆን፣ የራስ ቅሉ መጥፋት የታወቀው ባለቅኔው ከዚህ አለም በሞት የተለየበትን 400ኛ አመት በማስመልከት ዶክመንተሪ ፊልም በሚሰራበት ወቅት መሆኑንም አስረድቷል፡፡ሼክስፒር ከሚወዳት ባለቤቱ አና ሃትዌይ ጎን መቀበሩን ያስታወሰው ዘገባው፣ የመቃብር ስፍራው ለረጅም አመታት በበርካታ የባለቅኔው አድናቂዎች ሲጎበኝ የኖረ ትልቅ ስፍራ እንደነበርም አክሎ ገልጧል፡፡

የዓለም መርዝ እቫቮች እንኳንም ይኽንን የራስ ምትሃት አዘዘላችሁ።እንግሊዝ የቀበረው time bomb ይኸው ዓለምን ፍዳ ያሳያታል።
“ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው
ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው፥
ምን አሉ እንግሊዞች ሲገቡ አግራቸው፥
ለወሬ አይመቹም ተንኮለኞች ናቸው።”
እግዚአብሔር የበለጠ ራስ ምትሃት ይስጣችሁ።ዛሬ የዓለም እናቶች እና አባቶች የደም እንቫ የሚያለቅሱት እንግሊዝ በተከለው የከፋፍለኽ ግዛው ሰይጣናዊ ስራ ምክንያት ነው።እንባዋ መድረቂያ ያጣችው አገራችንም ይዚህ እርኩስ ዓላማ ዋነኛ ሰለባ ናት።
Divide and conquer (derived from the Latin saying Divide et impera) may refer to:
Ethiopian angetuwan yaskoretu englizoch nachew. Meles zenawi gin angetun defa inji chinkilat yelewim.