የወያኔ የደህንነት ተቋም በመረጃ ድርቅ ተመታ:: ዳግም ግምገማ ሊገባ ነው::
የወያኔ የደህንነት ተቋም በመረጃ ድርቅ ተመታ:: ዳግም ግምገማ ሊገባ ነው::
#Ethiopia #EthiopianSecurity #EPRDF #OromoProtests #Miniliksalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ለደህንነት ተቋም ቢሮ ቅርብ የሆኑ ምንጮች የኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ተቃውሞ ከፈነዳ በኋላ ባሉት ጊዜያት በመላው ሃገሪቱ እንደ ውሃ ይፈስ የነበረው የመረጃ አገልግሎች በ75 በመቶ መቀነሱን እና ሕዝቡ ለሕወሓት የደህንነት ሃይሎች እና ለጸጉረ ልውጦች ያለው ማግለል እና መጠራጠር ችግር በመፍጠሩ እንዲሁም ከብኣዴን እና ኦሕዴድ የወጡ የደህንነት አባላት የሚያመጡት መረጃ ፍሬ አልባ እና ተራ በመሆኑ የደህንነት ቢሮው በመረጃ ድርቅ መመታቱን እና እንቅስቃሴው በሕዝብ ጫና መቀዝቀዙን የደህንነት ተቋሙ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::በሹሞች እና በተራ አባላት መካከል ዘርን መሰረት ያደረገ ቅርርቦሽ እንዲሁም በሕወሓት የደህንነት ሹሞች እና በሌሎች ብሄር የደህንነት አባላት መካከል ጥርጣሬ እየሰፋ መምጣት በዘር ላይ የተመረኮዘ ጥቅማ ጥቅም ክፍፍሎሽ የአማራ ደህንነት አባላትን ማግለል በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የደረሰው ግፍ የኦሕዴድ የደህንነትና ጸጥታ ሃላፊዎችን መወንጀል መጀመሩ የደህንነት ቢሮው መታመሱን እና በመረጃ ድርቅ መመታቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::
ከወራት በፊት የተደረገውን ግምገማ ተከትሎ አስራ ስምንት የትግራይ ተወላጆች ከአዲስ አበባ ተነስተው በአልታዘዝ ባይነት ወደ መቀሌ መቀየራቸው ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን ለሃገር የሚሰሩ አባላት ለሹሞች የግል ጉዳይ አልታዘዝ ስላሉ ብቻ ከደረጃቸው ዝቅ ብለው የማይሆን ቦታ ላይ መመደባቸው ጥያቄ ቢያስነሳም ሹሞቹ ለአሸባሪ ድርጅቶች ተባባሪ የሆኑ ሲሉ አባላቱን ወንጅለዋል::በሃገሪቱ በሕወሓት የበላይነት የተያዘው የደህንነት ተቋሙ ከሹሞቹ እና በጥቅማ ጥቅም በዝምድና በአብሮአደግነት እና እከክልኝ ልከክልህ በቡድን ከተያያዙ የደህንነት አባላት ውጪ በሃገር ጉዳይ በስራ የተሳሰረ መረቡ መላላቱን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::መረጃ አነፍናፊዎች እና የመንደር መረጃ አቀባዮች ራሳቸውን እያራቁ መሆኑ ታውቋል::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና የደህንነት ተቋሙ አሰልጣኞች የሆኑት አቶ ሰለሞን አስራት እና አቶ በትረ መንግስተአብ የስራ መልቀቂያ አቅርበው ወደ ሚኖሩበት አውሮፓ መመለሳቸውን የደህንነት ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን አዳዲስ የወታደራዊ እና የሲቭል ደህነት እና ስለላ አሰልጣኦችን ለመቅጠር የደህንነት ቢሮው ከአለም አቀፍ የሴኩሪቲ ደላሎች ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ታውቋል::የደህነት ተቋሙ በመረጃ ድርቅ መመታቱን ተከትሎ ዳግም ወደ ግምገማ ለመግባት ዝግጅት ላይ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረው ምናልባት በመጪው ወር አጠቃላይ ግምገማ እንደሚደረግ የገለጹት ምንጮች በተቋሙ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን/በጥርጣሬ መተያየት ለስራ ደንታቢስ መሆን ስርኣቱ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ መሆኑን በግልኣ ይጠቁማል ብለዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ
ተፈጥሮአዊ ድርቅ የመረጃ ድርቅ የመልካም አስተዳደር ድርቅ የመሪ ድርቅ የሀገር ፍቅር ስሜት ድርቅ የዉጪ ምንዛሪ ድርቅ የሚበላ ነገር ድርቅ ብቻ ድርቅ በድርቅ!! ሕያው አምላክ የሚበጀውን ያርግልን ።
weyane
lemin gin atlekum.
weyane will fall very soon
Woyanne never had its own intelligence . It was depending on its master the CIA. That is why fighting in Somalia for America.
ደህንነት ማለት ወገኑን ሃገሩን ለሆዱ የሚሸጥ የሚለውጥ የክህደት ማዕከል ማለት ነው! አዎን ዛሬ ሃገሪቱ በረሃብ በድርቅ ተመትታ ሰላዩቹና ሰፍስ ገዳዩቹ የጎሳ ስብስቦች ህዝብን ፣ወጣቱን ሽማግሌወን
እየገደሉ ነው! ብአድን አማራን እየገደለና እያገደለ እያፈናቀለ አማራ ኢትዮጵያዊ አይደለም በለው!
ሰ.አ
ደህንነት ማለት ወገኑን ሃገሩን ለሆዱ የሚሸጥ የሚለውጥ የክህደት ማዕከል ማለት ነው! አዎን ዛሬ ሃገሪቱ በረሃብ በድርቅ ተመትታ ሰላዩቹና ነፍስ ገዳዩቹ የጎሳ ስብስቦች ህዝብን ፣ወጣቱን ሽማግሌወን
እየገደሉ ነው! ብአድን አማራን እየገደለና እያገደለ እያፈናቀለ አማራ ኢትዮጵያዊ አይደለም በለው!
ሰ.አ
አንባብያን ሆይ፤
ሰለሞን አስራትም ሆነ በትረ መንግስተ ዓብ ከሄዳች ሁባት ጉርኖ ተለቅማች ሁ ያስገደላች ኋቸውን ግለሰቦች ታወጧታላች ሁ።ሰውነቷ እየደረቀ የመጣው £¥¢ ጉጅሌ ¢€£ ገና በቁሟ ትፈረካከሳለች።
**…አክታን አናድነውም…ጉጅሌንም አናድነውም****
አፋችን ደርሶ ብናቆየውም፤
አክታን ብንደብቀውም።
በውርደት እያየነውም፤
ጉጅሌን በፍፁም አናድነውም።
አክታም ቢሆን ይሄው ነው፣
ወደ ውስጥ እንኳ ብንምገውም፤
ሆዳችን ታዛዥ ነው ለተፈጥሮ :-
ያለ ሕሊና አናድነውም።
ከእኛው ተፈጥሯል ብንልም ያውም፤
እንደአክታ በምንም አባብለን አናድነውም።
አናድነውም ፍጹም ሓቁን ስናየው በተጨባጭ፤
ጉጅሌስ በሰላም ሥም ፣ አልሆነም እንዴ አሽቃባጭ?
ለሃያ ዓመት ይቅርና በእጥፉ ስሌት ለአርባ፤
“ቢደረፍለትም ጓንዴ በሰገባ፤
ሕድሪ ሰውዓትና ሎሚ ዝጠለሙ፤
ሐገርና ዝሸጡ ብደም ዝፈረሙ፤”
ሁሉም ያገኛሉ እንደ በደላቸው፤
አያ ጊዜ መጥቶ:-
ይብላኝ ወዮላቸው!!!
የሰው አክታም ሆነ ጉጅሌውም ያልፋል ፤
አያ ጊዜ መጥቶ በሕዝብ አፍ ይተፋል።
በግዴታ አክታ ቁልቁል መተፋቱ፤
ጉጅሌም አይቀርም በቀን መደፋቱ።
እናም በአፋችን ድብቅ አርገነውም፤
ፍፁም ከመትፋት በቀር ማንም አያድነውም።
ከላንቃ-ጥግ ቢኩረፈረፍ፣ትፋትን ሆዳችን አምጦ፤
እየተገመደ ቢዝለገለግ፣ካሳምባ ጥግ ተሸምጥጦ፤
ትንፋሽ በሽምቅ እየገፋው፤እብጥ ብሎ በጉንጫችን
ምላስ ለፍላፊው ሊተፋው፤ቢከላከል ከንፈራችን፤
እየገዘፈ በጭብጥ ባዕድነቱን ስንቀምሰው፤
ስንጠላው ለራሳችን እያጣጣምን ስንልሰው፤
ወደድነውም፣ጠላነውም፤
በውርደት እያየነውም፤
አክታን ብንወደውም
ጉጅሌን አናድነውም።
ከንፈራችን ሲያሞጠሙጥ ላንቃ በንዝረት ከጠረገ፤
የቀረልን ይመስለናል ፤ በአፍንጫችን ከተማገ።
አክታ ግን ከተማገ በትናጋ ታግዞ፤
አንድም አይቀር ተጎልጉሎ፤ይወጣታል ጓዙን ይዞ።
ባዕድ ሆኖ ሲኩረፈረፍ እስከትናጋችን ሞልቶ፤
ከሕሊናችን ሲሟገት በራስ ዳኝነት ተጠልቶ፤
ጥርስ ለማኘክ ቢሆንም-ቅሉ፣ሕሊና ያልወደደውን፤
ያክታን መኖር ልባችን ለመቼም የማይፈቅደውን፤
በምላስ እንደታዘለ በትንፋሽ እንኩርፍ ፈልቶ፤
በጭ-ጮ አሊያም ባዝቶ ሲከፋ ከደም ተጣብቶ፤
እብጥ እንዳለ ጉንጫችን፤ወደድነውም፣ጠላነውም፤
ቢከላከልም ከንፈራችን፤
አክታን አናድነውም።
አፋችን ደብቆት ቢቆይ:-ጥርሳችን ቢሸፍነውም፤
ጎልጉለን ከመትፋት በቀር በማጨቅ አናድነውም።
በኢኮኖሚ ግንባታ በዶላር በብር ቢሸሸግም፤
በግድብ ተስፋ ለመኖር የሕዝቡን ሥልጣን ቢፈልግም፤
ዘረኝነትን የሚዋጋ ኢትዮጵያዊነትን የሚያነግስ፤
ቆየ’ኮ ከተፈጠረ ግብረ-ጉጅሌን የሚያረክስ።
ልባቸው ባልተቸነፈ ሕሊናቸውን ባልሸጡ፤
ኢትዮጵያዊነትን አንግበው ነፃነትን በሚያምጡ፤
እየደሙ እየሞቱ በትግል ውስጥ እየፋሙ፤
ባልታሰበ አቅጣጫ ከጉጅሌው በሚቀድሙ፤
እሳት ባሕርን ሊያሻግሩን፤
በልብ አፍንጫቸው አሽትተው፤
የገዳዮችን ኅጢያት፤
በሞት ሸለቆ ሸኝተው፤
የመቅሰፍት ፍትፍት የበሉትን በዘረኝነት ደም ሰክረው፤
ያሳዩታል ለሕዝቡ በመቅሰፍት ድንጋይ ተወግረው።
የጉድፍ የእድፍ መጨረሻው፤
በቃ መቃብር በመሆኑ፤
ጉጅሌም እንደአክታ፤
በደም ታጅሏል አይኑ።
እናም…..
በውርደት እያየነውም፤
ጉጅሌንም አናድነውም።
አክታን ባንወደውም
ጉጅሌን ብንጠላውም:-
በፍፁም ከመትፋት በቀር፤
ለያይተን አናድነውም።
የኦሮሞ መሬት እየተሸጠ መቀሌ ላይ ግዙፍ ፋብሪካ ይገነባል!
ደቡብ ክልል ላይ የሃይል ማመንጫ ግድብ እየተሰራ ለትግራይ ፋብሪካዎች በነጻ ጥቅም ላይ ይዉላል!
የጋምቤላ መሬት እየተሸጠ ለትግራይ መንገድ ልማት ይዉላል!
የቤኒሻንጉል ወርቅ እየተሸጠ የህዉሃት ባለሃብቶችን የዉጭ ምንዛሬ እጥረት ይፈታል!
አማራዉ ከመሬቱ እየተፈናቀለ ለትግራይ ሰፋሪዎች ይታደላል!
አመናችሁም አላመናችሁም እየሆነ ያለዉ ይሄ ነዉ፡፡!
ምክር ጠፍቶ ምክር ተሳስቶ
ማረሻው አንድ ብር ምንሺር በመቶ
አለመታደል ሁኖ ወንድም ወንድሙን እየገደለ
ይኸው እየተገዳደል እዚህ ደረስን ምን ይሻላል?