መፍረስ ያለበት የፍትሕ ሚኒስቴር ሳይሆን ሕወሓት የሚባለው ገዳይ ድርጅት ነው::
መፍረስ ያለበት የፍትሕ ሚኒስቴር ሳይሆን ሕወሓት የሚባለው ገዳይ ድርጅት ነው::
ምንሊክ ሳልሳዊ – ከነሰው በላዎቹ ከነአዘናጊዎቹ ከነገዳዮቹ መንደር የሚመጡ የጊዜ መግዣ እና ማጭበርበሪያ ዘገባዎች አሁንም አልቆሙም:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ካለምንም የፖለቲካ ድርጅት ይሁን አስተባባሪ ተቋም መሪነት በራሱ ስለመብቱ እና ነጻነቱ አደባባይ በመውጣት እየተገደለ እየቆሰለ በመፋለም ላይ ይገኛል::በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው ስር ነቀል ለውጥ ነው:: የፍትሕ ሚኒስትር መፍረስ የሃሰት ክስ ፋብሪካ አቅቢ ሕግ መቋቋም አሊያም የጸረ ሙስና ኮሚሽን ስልጣን ተገፎ ኮሚሽኑ ውደ ትምህርት ቤትነት መለወጥ አይደለም::ሕዝቡ የሚፈልገው ገዳይ ማፊያ የሆነው ሕወሓት እንዲፈርስለት ብቻና ብቻ ነው::
ፍትህ ተቀብሯል::ለዘላቂ ልማት እንሰራለን በሚል ስርኣት ውስጥ የመሰረታዊ የዲሞክራሲ መብቶች በጊዜያዊነት መኖር እና እንደመነገጃ መጠቀም ህዝብን አገለግላለሁ ሳይሆን አጭበረብራለሁ እንደማለት ይቆጠራል:: የወያኔ ስርኣት ባለስልጣናት በፍርሃት ተውጠው በጠበንጃ ሃይል በሚኖሩባት በዚች ኢትዮጵያችን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አሁንም እጅግ መልስ የሚያሻቸው ጉዳዮች ናቸው::ዜጎች በሃገራቸው እንዳይኮሩ በመኖር ደህንነታቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ እየተደረገ ስለሆነ ይህ ደሞ ወያኔ የያዘውን ስልጣን ላለመነጠቅ የሚሰራው ፖለቲካዊ ደባ ውጤት መሆኑ እሙን ነው::
ህዝብ ባለው ስርኣት ላይ እምነት የለውም:;በሃገራችን የተንሰራፋው አገዛዝ በከፍተኛ ደረጃ በፍርሃት በመዋጡ የፍትህ ተቋማቱን ሁሉ በቁጥጥር ስር አውሎ ዜጎችን የሚያጠቃበት የፖለቲካ ዱላ አድርጎታል:: ከባዶ ተነስተው ቢሊየነር የሆኑ ባለስልጣናትን እና ዘመዶቻቸውን ይቆጣጠራል ያጋንጣል የተባለው የጸረ ሙስና ኮሚሽን ከጠያቂነት ወደ አስተማሪነት እንዲሸጋገር ተፈርዶበታል::የሃሰት ክስ የሚፈበርከው አቃቢ ሕግ በሕወሓት ተጠፍጥፎ ስለተሰራ ተቃዋሚዎችን በመፈረጅ እና በመወንጀል ያስራል ያንገላታል ማለት ነው::ህጎች በተግባር ህዝብን አለማገልገላቸው እና በባለስልጣናት የመደፍጠጣቸው ውጤት ነው::ፍትህ እና መልካም አስተዳደር እንዴት ሊረጋገጡ ይችላሉ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እየተጓዝን ነው ጥያቄያችን ስለዚህ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል::መፍረስ ያለበት የፍትሕ ሚኒስቴር ሳይሆን ሕወሓት የሚባለው ገዳይ ድርጅት ነው:: #MinilikSalsawi