ውሃ በፈረቃ ፥ የሙታንን መነሳት ተስፋ እናደርጋለን ( ሄኖክ የሺጥላ )

ውሃ በፈረቃ ፥ የሙታንን መነሳት ተስፋ እናደርጋለን ( ሄኖክ የሺጥላ )

ኣንድ ወዳጄ አዲሱን የአዲስ ኣበባ “ውሃ በፈረቃ” ዜና እንደሰማ ፥ « ድሮ በምን ነበር ?» ብሎ የጠየቃት ጥያቂ ፈገግ ኣድርጋኛለች።
የኣዲስ ኣበባ የመሬት ትሎች ዛሬ ዛሬ ከኣፈሩ ይልቅ ለመኖሪያነት ቧንቧውን ይመርጣሉ። ለምን ቢሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ውሃ ከሚመጣበት ቀን ይልቅ « መሬቱ ለ ኢንቨስትመንት ይፈለጋል እና ተነሱ» የሚለው የመንግስት ማስታወቂያ የሚሰማበት ይልቃልና።

ስለ ቧንቧ ካወራሁኝ ኣይቀር ፥ ኣዲስ ኣበባ ቤተሰቦቼ ጋ ደውዬ ስለዚህ የውሃ መጥፋት ጉዳይ ስንጨዋወት ፥ በዛ በኩል እንዲህ ኣሉኝ « ኣይ ውሃው መቼ እንደሚመጣ ስለማናውቅ ቧንቧውን ከፍተነው ነው የምንውለው የምናድረው ፥ እንደውም ኣንዳንዴ ኣሜሪካዊው ጠፈርተኛ ጨረቃ ላይ በወጣ ጊዜ ምድር ላይ ካሉ ወገኖቹ ጋ ለመገናኘት በሚያደርገው ጥረት ተፈጥሮ የነበረው የተቆራረጠ የራዲዮ ዌቭ ዛሬ የኛ ቧንቧ ላይ ይስተዋላል ፥ ይሄም ምክንያት ምናልባት ውሃው ከጨረቃ ይሆን ተቀድቶ የሚመጣው ብለን ኣንድናስብ ኣድርጎናል » ብለውኛል።

ኣንደውም ኣንድ ዘመዴ « ጉዳዩ የውሃ ጉዳይ ሆኖብኝ እንጂ ይሄንንም ቧንቧ እንደ ኢቲቪ ጥርቅም ኣድርጌ ዘግቼው ባረፍኩ ነበር !» ያለችኝን ባነሳስ!
ለነገሩ ኣባይ ተገድቦ እንዳለቀ ፈረቃው ይቀራል ልል ብዬ ፥ ለካስ ኣባይ ለመጠጥ የሚሆን ውሃ የለውም ለግድብ እንጂ! ብዬ ያባይን ነገር ለግብፆች ትቼ ወደ ኣዋሽ ገሰገስኩ ። ኣዋሽ ስደርስ ኣዋሽ ከነ ኣባ ሳሙኤል እና ገፈርሳ ጋ ኣምስት ለኣንድ ኣልጠፈነግም ብሎ ፥ ህገ መንግስቱም ኣይመለከተኝም ብሎ እንደ ዋቢ ሸበሌ ኣሸዋ ውስጥ መኖር እንደጀመረ ሰማሁ ።

በነገራችን ላይ በወንዞች የተከበበችው ሸገር ውሃ ሲጠማት ትግራይ እንዴት ኣድራ ይሆን ?
ማን ነበር
« ኣይጫንም እንጂ ውሃ በመኪና
መቀሌ ነበሩ ኣባይና ጣና » ያለው ።

እነሱ ምናቸው ሞኝ ነው በመኪና የሚጭኑልህ ሃይላንድ እያለ!

ኣዲስ ኣበቤዎች የክርስቶስን ፥ የውሃን እና የመብራትን መምጫ እስከ ዛሬ ኣያውቁትም ነበር ፥ ዋን ኢዝ ዳወን ናው ። መብራትም በፈረቃ ሆነ የሚለውን ዜና ስንሰማ ምናልባት ያኔ « የሙታንንም መነሳት ተስፋ እናደርጋለን !» ብለን ካንጀታችን እንፀልያለን ። ሲሆን ስላየን!

Henoke Yeshetlla's photo.

7 Comments on “ውሃ በፈረቃ ፥ የሙታንን መነሳት ተስፋ እናደርጋለን ( ሄኖክ የሺጥላ )”

  1. ወያኔ ሥልጣን በፈረቃ ቢጀምር ለውጥን እናመጣለን ግን ከወታደራዊ መንግሥት ሁሌም የዳቦ የውሀ የነዳጅ ሰልፎች አይቀሩም።

  2. 50% ያላነሰው ከተማ በመፍረሥ ላይ ነው ታድያ ይህ ህዝብ ይጠቀም የነበረውን ውሀ የት ገባ? ወይሥ ወያኔ በምርጫ የተሸነፈባቸው ክ.ከተማዎች ተለይተው የመብራት የውሀ የኔቶርክ ሥርጭቶችን ማጥፋት ምን ይሉታ ልማታዊ መንግሥት ወይሥ አሸባሪ?

  3. Zeyit ena skuar be wor and gizie ration/be qunena new.
    Wuha be ye 3 qen be bzu ketemawoch, andand bota minm yelem, mebrat beyeqenu 4-5 seat yberal.
    Ahun new giziew bertu, berttenal tgrai woyanien enaTfaw.

  4. ibakachu yemadbt worie atawru
    sewu yetna yet dersoal yegna tsehafiwoh
    ibakachu metsehaf anbebu discuss ideas .

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*