ተንጋለው ቢተፉ : ተመልሶ ባፉ – ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::

ተንጋለው ቢተፉ : ተመልሶ ባፉ – ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – ከሶማሊያ ከኬንያ እና ከደቡብ ሱዳን እያስኮበለሉ ልዩ ሃይል እና የፌዴራል ፖሊስ አድርጎ በመቅጠር ኢትዮጵያዊ ዜግነት መስጠት ምን የሚሉት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ እየተደረገ ያለ ጥላቻ ነው ??? ከደህንነት ቢሮ የሚወጡ ጥቆማዎች አስደንጋጭ ናቸው::ወያኔ ጊዜ መግዣ ፋታ ማግኛ ማዘናጊያ ማደናበሪያ ያላቸውን የፕሮፓጋንዳ ስራዎች እየሰራ ነው:;የወያኔን አካሄድ ጠንቅቀን ማወቅ አለብን ዝም ብሎ ፖለቲከኛ ነኝ አያሉ ማራገብ አክቲቭስት ነኝ እያሉ መብጠልጠል/ማጦልጦል ጥቅም የለውም::ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::ካልሆነ ጊዜ ገዝቶ እያዘናጋ የለውጥ ሃይሉን አመድ ለማድረግ ቆርጧል::

ሁሉም ነገር ስህተት ነው ብለው ራሳቸው አምነዋል ከተባለ እነዚህ ሰዎች ስልጣን የማለቁበት ምክንያት ምንድነው? የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን.. የኦሮሞ ወገኖኔ ላይ የወሰዱት ድድብና የተሞላበት ግድያና ድብደባና እስር … የትራፊክ ሕግ … የጤና መድህን ዋስትና … ሁሉ ፖሊሲያቸው ስህተት ነው እያሉ እየተናገሩ ነው::በአገራችን ላይ አስተዳዳሪ ነን ብለው እስከተቀመጡ ድረስ ሃገርና እና ሕዝብን የሚመሩበት ፖሊሲ ስህተት እና ፉርሽ ከሆነ ምን እየጠበቅን ነው::ሕዝብ ላይ እየደነፉ ሕዝብ ላይ እያሾፉ ሕዝብን እየዋሹ ከዚህም አልፈው እየገደሉ እያሰሩ እያሳደዱ ይህ ስራችን ስህተት ነው እያሉ ደጋግመው እያደረጉት እኛ ግን ምን እየሰራን ነው?እነሱ ሰው ለመጨፍጨፍ በአንድነት ሲዘምቱ ደግመው ለለመዋሸው በአንድነት ሲደሰኩሩ እኛ ስለ ነጻነታችን ምን እየሰራን ነው?ድር ቢያብር አንበሳ ያስር አንድ እንጨት ብቻውን አይነድም::

ኢሕአዴግ ተሃድሶ አያስፈልገውም በስብሷል መፍረስ አለበት::እኛ አይደለንም ራሳቸው አመራሮቹ ድርጅታቸው እንደበሰበሰ ከሟቹ ጀምሮ ተናግረውታል::አሁን ያለው አመራር ሰው ያልተረዳለት ነገር ቢኖር ራሱን የሚክበው በባዶ ነው:: ሕዝብን እያስገደለ የሚገኘው ያልተማሩ በፕሮፓጋንዳ የተሞሉ ያልሰለጠኑ ፖሊሶችን ከአንዱ ክልል ወደ አንዱ ክልል እየወሰድ ነው::ለመሆኑ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን ? 25 ሺህ የልዩ ሃይል ፖሊስ ሰራዊት ከሶማሊያ ከደቡብ ሱዳን እና ኦሮሚኛ ተናጋሪ ከሆኑ ኬንያውያን ተመልምለው ሰልጥነው ከፌዴራል እና ከክልል እንዲሁም ከአግኣዚ ሰራዊት ጋር ተደባልቀው ሕዝብ እየገደሉ ይገኛሉ አሁንም ስልጣንን ከሕወሓት ሚሊሻዎች ጋር በጋራ ይጠብቃሉ የተባሉ ከየቦታው እየተመለመሉ እየሰለጠኑ ይገኛሉ::ግን እስከመቼ??? ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

21 Comments on “ተንጋለው ቢተፉ : ተመልሶ ባፉ – ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::”

  1. Yonas ermias
    ye tgrai hzb woyanien slemidegf hzbawi meseret alew tlaleh.
    Le tgrewoch yebelaynet endeqome mnaqew new.
    Welqait-Tegedien bezer maTdat amarawn gelo, abaro tegrie masferu hzbawi yaregewal le nante.
    Be mela etiopia 6 million amara megdelu tgrai woyanien hzbawi argotal le nante tgriewochu.
    Oromon merietun eyeneTeqe letgriewochna lewci ziegoch mesTetu, yan hulu ye oromo teqwami megdelu lante hzbawinet new.
    Adis abeba hzbun ke bietu eyasleqeqe condominium eyesera letgriewoch masrekebum hzbawinet new lante mkiniyatum hzb malet tgrie new.
    Konso lay hzbun asro wode magoriya meworwer hzbawinet new le tgrai woyaniewochu.
    Baciru tgrai woyanie beslTan meqoyetun miqawemu maletm melaw ye etiopia hzbn bitgedlu hzbawinet new le nante.
    NeTanetn matawqu neTa awci hunachuh new.
    Yalawaqi sami nfT yleqelqal hunachuh new.
    Hzb eyefejachuh tesasten new yqrta tlalachuh.
    Ladersachuhut bedel kasaw slTan melqeq new.
    Yh sihon new yqrta mnaderglachuh.
    Qnjit siyashnfachuh hzb fejachuhna yqrta Teyeqachuh.
    Yabat eda yelebn qoshasha tgrai woyanien yqr eyaln lemeshekem anchlm.
    BeTam bzu millionoch etiopiyawiyan Trit adrgew be selam, bekulnet, be dimokrasi ymimeru slalun benesu metedader aleben.
    Mnm beweTan be wdaqi worari, zereña, cingaf, worada, denqoro, ebriteña, wonjeleña yetgrai woyanie malagegiya anhonm.
    Lielaw Telatachuh slehonu hzb aydelem

  2. ስልጣን አይልቅም አዎ አይልቅም የህዝብ ነው ሰልጣን እናንተ ውሸት ሰለፃፈችሁ ነው ወያኔ ሰልጣን የሚለቀው ከከከከከከ

  3. በምንም ተአምር በዛ ተባለ በዛተባለ የጀግኖች ጀግና ህወሕት ነው

  4. ” ከሶማሊያ ከኬንያ እና ከደቡብ ሱዳን እያስኮበለሉ ልዩ ሃይል እና የፌዴራል ፖሊስ አድርጎ በመቅጠር ኢትዮጵያዊ ዜግነት መስጠት ምን የሚሉት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ እየተደረገ ያለ ጥላቻ ነው ??? ”

    Mobutu also did the same in the final years and days of his power. Sure other dictators also have done similar things.

    Idme leAmerika !

    May God Damn USA, the cancer of humanity and the power behind TPLF.

  5. By the way, isayas does also the same thing. Demhit is not an eritrean force, but is responsible for the security of isayas because isayas doesn’t trust eritreans.

  6. ንጉሡ ሞቱማ says:

    March 11, 2016 at 6:09 am

    ዳግም አደዎ ዘመቻ አስቸኳይ ጥሪ!!!
    ነፃነት ወይም ባርነት!!!
    በቁመና መሞት ወይም በማእረግ ለኢትዮጵያ ብሩህ ቀን መሞት!!!
    ታህሣሥ 1 ቀን 2008 ዓ•ም•
    ••• መመረያ ቁጥር 4•••
    Are you ready for radical change for equal opportunity blessed land Ethiopia for all in the name of ” ADOWA victory again in coming soon!!!”
    ጥሪው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው፣ሰሜን፣ደቡብ፣ምስራቅ አና ምዕራብ ፣ ኢትዮጵያዊ ማለት ማነው? ቅን ና እውነተኛ፣ሃይማኖተኛ/ፈረሃ እግዚአብሔር ያለው፣ጥበብን በልቡ ያሳደረ፣ ጠንካራ በአስተሳሰብ ጤነኛ ደፈር፣ ሃገር ወዳድ ጀግና አትንኩኝ ባይ፣ ሲጠቃ አሻፈረኝ ባይ ትውልድ አከባሪ ነው።
    1• ኢሕአዴግ ስልጣን የማስረከብ የተሰጠው ጊዜ ገደብ አበቃ። የተላኩት ጠ/ሚ ሀ/ማርያም እንደ እስስት ፓርላማቸው ላይ በጭንቀት ሌላ አሰመሰልው አጥፈተናል ብለው ተናዘዙ። የኢትዮጵያ ህዝብ ከአሁን በኋላ ሞኝ ነው። ወደኋላ የለም የሞቱ ት ሰዎች ቁንጫ አይደለሙ፣ በኦሮሚያ፣ በጉንደር፣በጋንቤላ፣በሱማሌ፣በአፈር፣ በትግራይ ክልል ከአደዎ ምርጥ 1000 ወርቃማ ባለስልጣቢች ቤተሰብ በስተቀር። በ25 አመት ውስጥ ሰንት መአት ሰው ጨርሳቸሃፀረ??? ከዚህ በኋላ በቃችሁ ሆዳም እሐዲግየ???
    2• ጥሪያችን ለሁሉም ኢሐዲግ ስራዊት እና ፓሊስ ውስጥ ገብቷል፣ ተደራጅተዋል ፣ በተጠንቀቅ ከአሁን በኋላ በሕዝባችን ላይ የሚተኩስ ከላ ቀድመው እንዲመቱ ታዛዙን ሁሉ በአብዛኛው መመሪያው ደርሷል። ሁሉም ቀን እና ዶሮ ሲጮህ እየጠበቀ ነው።
    3• ጦርነቱ ለይቶ በ1000 አደዎች ላይ ብቻ ነው፣ አንጂ ከጭቁኑ ወገናችን የትግራይ ህዝብ ጋር አይደለም። ከዚያ በኋላ ዶ/ር ብርሐኑ የሽግግር መንግስቱን እና ጄነራል ከማል ጦሩን ይመራሉ።
    4• ሕዝባችን በየአቅጣጫው ለለውጥ ስለተነሳ ጨዎነት በተምላበት ሁኔታ፣ነመፈጋገፈ በለውጡ ማእበል ውስጥ እንዲሳተፍ እናሣስባለን።
    5• “ሮድ ማፕ” በሙሁራኖች አማካይነት በተከበሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ በኩል ለህዝባችን በቅርብ ቀን ይገለፃል።
    6• አገር ወዳድ በኢሐዲግ ውስጥ ያላችሁ ጦር ፣ ፓሊሶች የራሳችሁን ሂሊና ፍርድ ይዛቹ በለውጥ ውስጥ በሚስጣችሁ መመሪያ መሠረተ በኢትዮጵያ ውስጥ ማንኛውም ክፍተት ሳይፈጠር ከ ሽግግር መንግስቱ ጋር ተሠራላችሁ።
    7• የተደራጀ ሐይል በየአቅጣጫው ስላለ በጨዎነት እና በመረዳዳት ከእግዚአብሔር ጋር እንወጣዋለን። በፀሎት ወደ ፈጣሪ እንደ ሐይማኖታችሁ የምናለቅስበት ግዜ ነው። እነዚህን በ 17 አህያዎች ተቀምጠው ቤተመንግሥት በሱዳን አሰማት ስም የገቡትን ሴይጣኖችን በእግዚአብሔር ስም ይነቅላሉ። በኤፈርት በትግራይ ህዝብ ስም የዘረፈትን $50 ቢሎን ጋር ለፍርድ እናቀርባቨዎለን። ግን 50% ከ 1000 ውስጥ ተስፋ የቆረጡ የ ኤችአይቪ በሸተኞች ናቸው፣ ኢትዮጵያ የልጆቻቸው መኖሪያ እንኳን መሆኑን ረስተዎል???
    8• አቡነ መርቆሬዎስ አሁን ለሕዝባችን አንድነት መናገር የለቦት አጣብቅኘ ጊዜ ላይ ነን። አንድ ኢትዮጵያ ፣ አንድ ሲኖዶስ የኣባቶቻችን ሰርአትን ዶግማ እና ቆኖና ሳይቀየር ወደ አንድነት ማምጣት በእግዚአብሔር ስም ይጠበቅባቸዎል።

    ተራማጅ የኦሮሞ ታጋዬች ከ አምቦ ጫካ ጽሕፈት ቤት እና ይድረስ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ታጋዮች በየአሉበት፣ ለውድ መሪዎቻችን የሽግግሩ ዶ/ር ብርሐኑ ነጋ እና የጦሩ አሰረተባባረ ጀነራል ከማል ገልቹ።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!!
    ንጉሡ ሞቱማ አስተባባሪ CORE ከአምቦ። Strong Ethiopian is next to your door and Create connection for freedom!!!

    [Reply]

  7. Nigusu motuma ! kkkkkkkkkkkkkkkkk

    G7 eko kemote ketekebere koye

    shabya bilo netsa awchi kkkkk

    Birhanu belo yetor meri kkkkkkkkk

    atijajal jil k

  8. You yonas of woyane willy or nilly your masters woyanes will be destroyed and then you gona hang yourself

  9. አመድ ብቻ አድርጎ መተው የተቀበሩትን ስለሚበጠብጥ አመዱን እራሱ 30 ሜትር ቆፍሮ መቅበር። ነው

  10. ወያኔ ሞቶም አይታመንም ምክንያም በዚች ሃገር ላይ የተከለው ነቅርሳ ማጥፋት ይከብዳል (የጎሳ፣የጎጥ፣የሰው ባህሪ የለሌው አስተሳሰብ ተክለውት( ኢትዮጵያን ሲያቆስሉ ሲነክሱ ሲያስነክሱ ይኖራሉ ስለዚህ ወያኔን ማመን ቀብሮ ነውየሚለው አሁን አይሰራም!
    ሳ.አ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*