የመኢአድ ዋና መሪዎች፤ እርስበርስ “የእገዳ” ውሳኔ አስተላለፉ
– በፊናቸው ጠቅላላ ጉባኤ እናካሂዳለን ብለዋል
– አንዱ ሌላውን “ከሃላፊነት አግጃለሁ” ሲሉ ወስነዋል
የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት፤ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪን የከሰሰ ሲሆን፤ ፍ/ቤት አቶ አበባውን ለጊዜው በማገድ፣ የክስ መልስ እንዲያዘጋጁ የአንድ ወር ቀጠሮ ሰጠ፡፡
ለአመታት ከተለያዩ ውዝግቦች እፎይታ ያላገኘው መኢአድ፣ ዘንድሮም የፓርቲው ፕሬዚዳንትና የምክትላቸው በተቀናቃኝ ጐራ የተሰለፉበት የተካረረ ውዝግብ ገጥሞታል፡፡
መኢአድ፤ መጋቢት 24 ቀን ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ወስኗል ቢባልም፤ የፓርቲው ም/ሬዚዳንት ተቃውመዋል፡፡ አቶ አበባው ከአመራር እንዲታገዱ ስለተወሰነ ጉባኤውን የመጥራት ስልጣን የላቸውም ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ አንድሪያስ ኤሮ፤ እኛ በስድስት ወር ጠቅላላ ጉባኤ እናካሂዳለን ብለዋል፡፡
በአቶ እንድሪያስ ኤሮ አስተባባሪነት፤ ከ50 በመቶ በላይ የፓርቲው ላዕላይ ም/ቤት አባላት ተሰብስበው፤ አቶ አበባው መሃሪን ከፕሬዚዳንትነት አግደዋል፡፡ ክስም አቅርበዋል፡፡
አቶ አበባው በበኩላቸው ሌላ ስብሰባ በማካሄድ፤ የአቶ እንድሪያስን ቡድን አግጃለሁ ብለዋል፡፡ በፊናቸው ክስ እንደሚያቀርቡ በመጥቀስ፡፡
Addis Admass
Be shimglna gbuna Teqlala gubaye yftaw.
Mejemeriyam Teqlala gubaye neber meTrat migeba yeneber.
ማፈሪያዎች። ተሰበሰቡ አልተሰበሰቡ ምን ሊፈይዱ ነው? ህዝቡን ዝም ብለው ባያወናብዱት ጥሩ ነው። ከወያኔ ትግሬዎች በላይ በሌለ ዴሞክራሲ ትርፍራፊ ለመልቀም የሚያደርጉት ማወናበድ ነው። ህዝቡ ሌላ አማራጭ ይፈልጋል። በሌለ ሰላም የሰላማዊ ትግል ይብቃ!!!!!!
Tola
mechem OLF yemran endematil ergetegna negn ! kkk
Gin awo mafereyawoch nachew !
ሰኑዬ: – እከሌ ይምራኝ እከሊት ትምራኝ አይደለም ጥያቄው። ጥያቄው ማንም ሆነ ማንም በህዝብ ድምፅ የተመረጠ ያስተዳድር ነው ። ኦነግም ሆነ ኦብነግ፤ ወያኔም ሆነ ኢህአዴግ ፣ ብቻ የህዝብ ድምፅ ይከበር ። ሰላም ሁኝልኝ!!!
Tola tikikil new
ke tegentay OLFwegen neh beye neber kk