የመኢአድ ዋና መሪዎች፤ እርስበርስ “የእገዳ” ውሳኔ አስተላለፉ

– በፊናቸው ጠቅላላ ጉባኤ እናካሂዳለን ብለዋል
– አንዱ ሌላውን “ከሃላፊነት አግጃለሁ” ሲሉ ወስነዋል

የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት፤ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪን የከሰሰ ሲሆን፤ ፍ/ቤት አቶ አበባውን ለጊዜው በማገድ፣ የክስ መልስ እንዲያዘጋጁ የአንድ ወር ቀጠሮ ሰጠ፡፡
ለአመታት ከተለያዩ ውዝግቦች እፎይታ ያላገኘው መኢአድ፣ ዘንድሮም የፓርቲው ፕሬዚዳንትና የምክትላቸው በተቀናቃኝ ጐራ የተሰለፉበት የተካረረ ውዝግብ ገጥሞታል፡፡
መኢአድ፤ መጋቢት 24 ቀን ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ወስኗል ቢባልም፤ የፓርቲው  ም/ሬዚዳንት ተቃውመዋል፡፡ አቶ አበባው ከአመራር እንዲታገዱ ስለተወሰነ ጉባኤውን የመጥራት ስልጣን የላቸውም ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ አንድሪያስ ኤሮ፤ እኛ በስድስት ወር ጠቅላላ ጉባኤ እናካሂዳለን ብለዋል፡፡
በአቶ እንድሪያስ ኤሮ አስተባባሪነት፤ ከ50 በመቶ በላይ የፓርቲው ላዕላይ ም/ቤት አባላት ተሰብስበው፤ አቶ አበባው መሃሪን ከፕሬዚዳንትነት አግደዋል፡፡ ክስም አቅርበዋል፡፡
አቶ አበባው በበኩላቸው ሌላ ስብሰባ በማካሄድ፤ የአቶ እንድሪያስን ቡድን አግጃለሁ ብለዋል፡፡ በፊናቸው ክስ እንደሚያቀርቡ በመጥቀስ፡፡

Addis Admass

5 Comments on “የመኢአድ ዋና መሪዎች፤ እርስበርስ “የእገዳ” ውሳኔ አስተላለፉ”

  1. ማፈሪያዎች። ተሰበሰቡ አልተሰበሰቡ ምን ሊፈይዱ ነው? ህዝቡን ዝም ብለው ባያወናብዱት ጥሩ ነው። ከወያኔ ትግሬዎች በላይ በሌለ ዴሞክራሲ ትርፍራፊ ለመልቀም የሚያደርጉት ማወናበድ ነው። ህዝቡ ሌላ አማራጭ ይፈልጋል። በሌለ ሰላም የሰላማዊ ትግል ይብቃ!!!!!!

  2. ሰኑዬ: – እከሌ ይምራኝ እከሊት ትምራኝ አይደለም ጥያቄው። ጥያቄው ማንም ሆነ ማንም በህዝብ ድምፅ የተመረጠ ያስተዳድር ነው ። ኦነግም ሆነ ኦብነግ፤ ወያኔም ሆነ ኢህአዴግ ፣ ብቻ የህዝብ ድምፅ ይከበር ። ሰላም ሁኝልኝ!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*