ሕወሃቶች ፎቅ ይሰራሉ ብአዴኖች ሎተሪ ይሸጣሉ !!!

ግርማ ካሳ  = ሕወሃቶች ፎቅ ይሰራሉ ብአዴኖች ሎተሪ ይሸጣሉ – ግርማ ካሳ

ከኢትዮጵያ በቅርብ ከመጣ ከአንድ ወዳጄ ጋር አወራን። ከጥቂት ወራት በፊት ብአዴን በባህር ዳር ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ፣ የተገኘ ። በስብሰባው ከፍተኛ ጭቅጭቅ እንደነበረ ነገረኝ። ከዚህ ወዳጄ ባገኙሁት መረጃ፣ በተለይም በፓርቲው መካከለኛና ታች ባሉ የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ በሕወሃት ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞ ተሰምቷል። “በኢሕአዴግ ዉስጥ የተጠቀሙት ህወሃቶች ናቸው እንጂ ሌላው አይደለም” የሚል ከፍተኛ ምሬትና ብሶት ቀርቧል። “በሁሉም ነገር፣ ሃላፊዎቹ ፣ ወሳኞች ቀዳሚዎቹ እነርሱ ናቸው ። ለምድንን ነው ይሄ የሚሆነው ?” የሚል ጥያቄ ቀርቧል። “እነርሱ ባለፎቅ እኛ ሎተሪ ሻጭ ነው የሆንነው “ ሲሉ ነበር።

እንደሚታወቀው ኦህዴድ አምጿል። የኦህዴድ አባላትና ካድሬዎች ናቸው፣ የመንግስትን መዋቅርን በመጠቀም ፣ ህዝቡን በማደራጀት ከነጃዋር ጋር በቅንጅት በመስራት፣ ላለፉት ሁለት ወራት ተቃዎሞ እንዲታይ ምክንያት የሆኑት።

ወደ ድሃዴን(የደቡብ ሕዝቦችች ደርጅት) ከመጣን አንደኛ እርስ በርስ ፣ ሕወሃት ለርሱ እንዲመቻቸው ብሎ፣ ከፋፍሏቸዋል። ለምስሌ በወላይታና በሲዳማ የደሕዴን አባላት መካከል ችግር አለ። ሁለተኛ በድሃዴን ተራው አባላት አካባቢም ፣ ባለው ሁኔታ ደስተኛ ባይሆኑም፣ ብዙም በኦህዴድና በብአዴን እንዳለው አይነት ማጉረምረም አይሰማባቸውም። ምናልባት የኛ ሰው ነው ጠቅላይ ሚኒስተር የሆነው ከሚልም ሊሆን ይችላል።

ለጊዜው ድሃዴንን ወደ ጎን በማድረግ፣ ብአዴን እና ኦህደድ ግንባር ቢፈጥሩ የሕወሃትን የበላይነት በማስቆም የስርዓት ለዉጥ ማምጣት የሚቻልበትን ትንሽ ድፍረት ከተገኘ ቀላል መንገድ ለማሳየት ልሞክር። ፓርላማው በ ቮት ኦፍ ኮንፊደንስ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማንሳት ይችላል። በፓርላማው ብአዴን እና ኦህዴድ በጋራ ከ547 መቀመጫዎች ከ313 እስከ 339 የሚሆነውንን ይቆጣጠራሉ።(ከ60% እስከ 71%) ሁለቱ ድርጅቶች የሚገናኙበትን እና አብረው ስትራቴጂያዝ ማድርግ የሚችሉበት መንገድ ቢፈለግ፣ ብዙ ሥራ መስራት የሚቻል መሰለኝ። ጥያቄው እንግዲህ እንዴት የሚለው ነው።

እነ ጃዋር ሞሀመድና አንዳንድ የኦሮሞ አክራሪዎች፣ እንዲሁም እንደ ተስፋዬ ገበረአብ ያሉ በሞጋሳ ኦሮሞ ሆነናል የሚሉ፣ ላለፉት 2 ወራትት የተጀመረው የኦሮሞ እንቅስቃሴ በኦሮሞዎች ትግል ብቻ ከድል እናደርሰዋለን የሚል እምነት ያላቸው ይመስላል። ይህ በጣም የተሳሳተና ጎጂ አመለካከት ነው። የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ጋር የተሳሰረ ነው። ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ እንዳሉት ኦሮሞ ግንድ ነው። ኦሮሞን ከሌላው ነጥሎ ማየት በራሱ ጸረ-ኦሮሞነት ነው። ይሄ አንዱ ነጥብ ነው።

አንድ ሰላማዊ ትግል ብዙ ህዝብ የሚኖርባቸዉን ትላልቅ ከተሞች ሳያካትት እንዴት ነው ለዉጥ ሊያመጣ የሚችለው ? አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጂማ፣ ሻሸመኔ በመሳሰሉት ከተሞች ሕዝቡን ማቀፍና ማንቀሳቀስ ካልተቻለ እንዴት ነው አገዛዙ ትንሽ ከአቋሙ ፈቀቅ እንዲል የሚገደደው ? የነጃዋር ፖለቲካ አሮጋንትና ለበለጠ ጥፋት፣ ለትልቅ ክስረት የሚዳርግ ፖለቲካ ነው። ኦሮሞ፣ አማራ መባባሉ ቀርቶ በጋራ ለመብት፣ ለፍትህ. ለመሬት ባለቤትነት ከመታገል ዉጭ ሌላ የተሻለ መፍትሄ አይኖርም።

ለዚህም ነው፣ የኦህዴድ እና የብአዴን አባላት እርስ በርስ እየተገናኙ ራሳቸውን አጠናክረው መዉጣት ያለባቸው። ሁለቱ አብረው ቢሆኑ አንደኛ ድሃዴንን ሊቀላቀላቸዉም ይችላል። ሁለተኛ ከዚህ በፊት ከሕወሃት ጋር በመሆናቸው የተቀየማቸው ሕዝብ ይታረቃቸዋል፤ ሶስተኛ ሙሉ ለሙሉ ሕገ መንግስቱ ይፈቅድላቸዋል።

በመጨረሻ አንድ ነገር ብዬ ላቆም። በርግጠኝነት ነው የምለው። በኢሕአዴግ ዉስጥ የበላይ ብአዴን ወይም ኦህዴድ ወይ ሌላ ደርጅት ቢሆን ኖሮ፣ ህወሃቶች አሁን ብአዴኖችና ኦህዴዶች እንዲያደርጉ የምንጠይቀዉን ከማድረግ በጭራሽ ወደኋላ የሚሉ አይደለም። የሚፈልጉትን ከማግኘት፣ አላማቸውን ከማሳካት አይቆጠቡም። ይሉኝታ ብሎ ነገር እነርሱ ጋር የለም። ላመኑበት ነገር ቆራጥ ናቸው። ብአዴን እና ኦህዴዶች በድፍረትና በቅርጠኝነት አኳያ፣ ህወሃት ያለው አንድ አሥረኛ እንኳን ቢኖራቸው ነገሩ አበቃለት ነበር።

ቀደም ሲል እንዳልኩት ኦህዴዶች “አምጸዋል” ።ዉስጥ ዉስጡን የተደራጁ ይመስላል። በቀላሉ ሕወሃት ገፍቶ ያስወግዳቸዋል ብዬ አላስብም። ብአዴኖች ዉስጥ ከላይ እንደጠቀስኩት ትልቅ ብሶት አለ። ብአዴኖችን reach out በማድረግ፣ ያላቸዉን አቅምና ጉልበት እንዲጠቀሙ ማነጋገር፣ ሎቢ ማድረግ፣ ማበረታትታት ያስፈለግል። በዚህ መልኩ ለዉጥ ከራሱ ከኢሕአዴግ ውስጥ ፣ ሰላማዊ፣ ሕገ መንግስታዊ በሆነ መልኩ ቢመጣ በጣም የተሻለ ነው የሚሆነው።

19 Comments on “ሕወሃቶች ፎቅ ይሰራሉ ብአዴኖች ሎተሪ ይሸጣሉ !!!”

  1. Wake up & smell the Coffee!

    since when Opdo & Amhara party work together? they hate each other to death, they don’t trust each other. Tigre Woyane work day & night to make sure that there is no trust in between them.
    remember on Oromo protest in Salale it was Amhara Liyu Police who was killing (Terrorising) the protester, there was some conflict in between Oromia Liu Polic & them too.

  2. Bado neger bihonm, lante sl, qdmiya ene adisu, bereket, tefera, dula, muktarn etc ke drjt masenabet woi slTan mensat, bewsT sraw manm aymeleketewmna.

  3. ህወሀቶች ፎቅ ይሰራሉ
    ኦህዴድ ነፍጠኞች ይሆናሉ
    ብአዴን ሎተሪ የሸጣሉ
    ደህዴን ሊሥትሮ ይሆናሉ

    አኗኗራችንን እንመልከትና እንፍረድ።

  4. ትግል እኮ ከፍት ነው ከማንም ፍቃድ አይጠይቅም።ዛሬም ነገም ወደ ትግሉ መግባት ይቻላል።ኦሮሞ እኔ እንደጀመርኩ እጨርሳዋለሁ ካለ እናንተ ደግሞ ገብታችሁ ለመታገል ስትገቡ እስቲ የሚከለክላችሁን ለሁሉም አሳያዩ።የኦሮሞ ትግል ቆሞ አይጠብቅም።ሌላው በተዘጋጀ ጊዜ ገብቶ መታገል ነው። በኦሮሞ ትግል ላይ ጥርጣሬ ተፈጥሮባችሁ ከሆነ ማነው መተማመን የሚሰጣችሁ።የትግሉ ጥንካሬ ነው።ሌላው የብስለት ችግርና ትግል ምን ማለት እንደሆነ ያለመረዳት ነው።ለወያኔ ሳናውቅ ትልቅ ነገር እየተሰራለት ነው።የትግል ጉልበት ሁለት ቦታ ሲከፈል ለወያኔ ትግሉን ለመምታት ይቀለዋል።የሁሉም መከራ ይራዘማል።ጅዋር ይህን አለ ብሎ ከትግሉ መቆም የማይመስል ነገር ለባልሺ አትንገሪ ነው የሚሆነው።ፋጥናችሁ ወደ ትግሉ ግቡ።
    ሁልጊዜ ሰላም ይሁን።
    አሜን።

  5. እንደነዚህ አይነት መጋዣ ሲያገፕ ወያኔ መሬት ላይ ሳይሆን ገና ፎቅ ጭንቅላታቸው ላይ ስርቶ አሸክሟቸው ይዞራል። ሽክም የማይስለቻቸው አህዮች!!!

  6. 1) tplf will never allow any communication between th DO’s

    2) Gun not law governs that country. Those with gun do whatever they want to do. What vote of confidence are you talking about?

    3) the only way out of this gugmanguges is through armed strugle and popular uprising. Dont distract the people from a winning path.

    4) as the going gets tough tplf will do everything possible to dismantle the country and walkaway with its loots. Let it be! I would rather live as a freeman in my piece than as a slave to tplf ethiopia.

  7. በደማችን በጌምድር የሚለውን የደብረታቦርና ወረዳወቿ ስምን እንመልሰዋለን።ጎንደር የሚለው መጠሪያ በሀይል በጌምድር የሚለውን ኩሩ መጠሪያችንን ሰሜን ጎንደሮች አጥፍተውታል።ለዚህ ደግሞ ጎንደሮች ዋጋቸውን ያገኙታል።እኛ በጌምድሮች ነን ጎንደሮች አይደለንም።

  8. ተማርን የምትሉ ልሂቃኖች ትግሉን መሥዋት ከሰሜን ይውደቅ ከደቡብ እያልን ሥንርበተበት ወያኔ 25 አመቱን ደፈነ ኢትዬጵያዊነት ሥሜት ተላበሱ አማራ ጀመረ ኦሮሞ የብሄር ዝቅተኝነት ተጠቂው ህወሀትን አትምሰሉ ባካችሁ ትውልዱ የብሄር ፖለቲካን አውግዟል የብሄር ፖለቲካንና ወያኔን መቅበር ነው የምንፈልገው።

  9. Lemsalie badn enyi:
    meriwochu adisu legese, bereket
    simon nachew.
    Wede rub (1/4 ña) abalatu amara
    ager tewoldew yadegu tgriewoch
    sihonu, lielaw 1/4ña degmo ke
    amara ena ke liela zer yetewoldu
    (ketgriena amara,
    keoromana amara,
    kewolaytana amara,
    keagewna amara, etc) yetewoldu
    nachew.
    Qeriw gmash demo amara
    nachew gn abzañawochu
    kehbrete-sebu yetenaqu,
    yetegelelu, sbnachew yewodeqe,
    bemeTfo srachew Tebasa
    yalebachew, achberbariwoch,
    wofefie qewsoch, etc nachew.
    Tqit haqeña amarawoch
    kemekakelachew binorum
    masTenqeqiya eyeteseTachew,
    eyeteqeTu, kedereja zq blew
    eyetemedebu betemelkachnet
    lesmu abal hunew mnm
    yemewesen slTan yelielachew,
    sle badn kfat mereja endayawqu
    yehonu nachew.
    slezih mnm yemiTebeq yelem ke
    zih ye tgrai woyanie qrnchaf badn.

  10. Ato Girma wera becha yehonek neger neh lelochin bemtkesbet neger antem tebochareqaleh keweyana gar weta geba setel neber anda be VIP ber eyetekebelu sitastenegdhu antem chirahin seteqola alneber enda

  11. የተሰቀለ ቋንጣና መንግሥት ግዜው ሲደርሥ ይወርዳል አጆሀ!!!

  12. ዚና አሊ = አሳብህ ጥሩነው በአንድነት መታገል ጠንካራ ያደርጋል ተነጣትሎ ግን መደከም እንደሆነ እኮ ኢትዮፒያኖች ዛሪ ሳይሆን ከጣሊያንም በፊት በለው በታሪካችን በግራኝም ዘመን ቢሆን አባቶቻቸው ያቆማትን አገር ለማንም አሳልፈው አልሰጡም የማንንም አገር አልነጠቁም ዛሪ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን እኮ አገር ያቆሙ አባቶች ጠላቶች ናቸው የኦሮሞን መሪት በቅኝ ግዛት ይዘው ነው ስለዚህ እነዚህ ጠላት የተባሉ የአጺዎች ዘሮች አምሃራዎች መመታት መጥፋት አለባቸው ከዛ ኦሮሞም ትግሪም አገሩን ያገኛል ተብሎ እኮነው ጫካ የወቱጥ እንጂ ኢትዮፒያውስጥ ያለፉ ስረአቶች ዲሞክራሲን ስላላመጡ ለውጥ ለህዝብ ዲሞክራሲ ለኩልነት ብለው አይደለም የአጺዎች ስረአት ከመሰረታቸው ጀምሮ በዘመናቸው ህዝብ ተቀብሎ አስተዳድረዋል ህዝብ ሳይፈልግ ሲቀር ስራቱን አፍርሳል ይህን ስረአት አምሃራው እራሱ አፍርሶታል ለምን ለውጥ ስለፈለገ ለውት ማለት ግን አገር አፍርሰን መሪት እንከፋፈላለን ማለት አይደለም:: ዲሞክራሲም አይደለም:: ፈረጆች እንደ ኢትዮፒያ በ አጺዎች ስረአት ተስተናግደዋል ሳይፈልጉ ሲቀሩ ለውጠዋል ዛሪ ዲሞክራሲ ተቀብለዋል አገራቸው ግን ያችኑ አባቶቻቸው ያቆማትን እንጂ አገር ለመከፋፈል ሳይሆን በአስተሳሰብ ልዩነቶች እየተማገቱ ለአንድ አገራቸው ይሰራሉ ኢትዮፒያውስት 25 አመት ዘር በማጥፋት አገር በመቀማት የዘር ክልል በሃይ በጫካ ህግ ተጭኖ ከተስማማን እንኖራለን ካልተስማማን አንኖርም ማለት ብቻ ሳይሆን ይሂ መሪት የኦሮሞ ነው በዚህ መሪት ላይ አምሃራ አያገባውም ….የሁሉም ነገር ተጠቃሚ ኦሮሞነው በማለት በዘር ማንነትህ አገርህን የምትነጠቅበት እና ባገርህ ላይ የምትባረርበት ዘምን ላይ ነው ያለነው ይህንን ነው እንግዲህ የኦሮሞ ልሂቃኖች አንዳንዲም ከወያኒጋ በጫካ ያጸደቁትን የዘር ካርታ አምሃራውን በግልጽ ኢትዮፒያ የምትባል አገር የምትፈለግ ከሆነ የአምሃራ ልሂቃን ያለፉ ስረአቶችን ለመመለስ መጣር የለበትም እያሉ ሲያስጠነቁም ነበር ከወያኒጋ እጅ ለ እጅ ተያይዘው ሲስሩ የነበረም ያሉም በተቃዋሚ በኩል ቆመናል የሚሉ ኦህዲድ (ኦነግ)አንድ አይነት ናቸው ጎበዝ አምሃራ እንደ ኦህዲድ ኦነግ ጫካ ወቶ ኢትዮፒያን አከፋፍሉኝ መሪት ይገባኛል አላለም የማንነት ጥያቂ በሚል ፉገራ ለራሲ የሚሆን መሪት አላለም የአምሃራ መሪት አልነበረም ወደፊትም አይኖርም አምሃራ መሪቱ ኢትዮፒያ ነች ስለዚህ ኢትዮፒያውስት ያሉ እንደ አምሃራ ማህበረሰቦች ኦሮሞም ልክ እንደ ጉራጊው እንደ አፋሩ ኢትዮፒያውስጥ ያሉ የ ኢትዮፒያኖች አገር ብሎነው የሚያስበው በርግጥ ነው ማህበርተሰቦች (ነገዶች) እንደየ ታሪካቸው ሰፍረዋል ያማለት ኦሮሞ ወይም ትግሪ ካሉት 81 ብሂረሰቦች ውጥ አምሃራ በወረራ አልያዛቸውም ኢትዮፒያም የምትባል አገር አልወረረችም ስለዚህ ብአዲን ማለት በወያኒ ህወሃት ባንዳ ተጠፍጥፎ ከጫካ ተሰርቶ በአምሃራ ላይ የተጫነ አምሃራን ለማሳደድ እና ከ ኢትዮፒያዊነት አውጥቶ ለማሳነስ ዘሩን በማጥፋት አገሩን ለመውረር የተደረገ ሲስተም ነው ማንም በውክልና ጫካ የላከው የለም ስለዚህ በ ኦህዲድ እና በአምሃራ መካከል ብዙ ልዩነቶች አሉ ኦህዲድ እና ህወሃት ግን ከጫካም ጀምሮ በአንድ አይነት አስተሳሰብ የሰሩ በተቃዋሚነትም ሁሉም ንድ አይነቶች ናቸው አምሃራና ኢትዮፒያኖች ግን አንድ ናቸው አገር ከሆነች የግዲታ በዘር መደራጀት የለብንም ስለዚህ ኦህዲድ ከህወሃት ጋር ያለውን መርምሮ 25 አመት ነጻነታቸውን እና አገራቸውን ከተቀሙ አምሃራም ጋር ሆነ ኢትዮፒያዊያን መቀላቀል ይችላል አለበለዚያ አገር እንዲሰጣችሁ ህወሃትን አገር ለማስለቀቅ አምሃራን አይሰራም አገር የተገኘው በውርስ ነው ማንም ሰጭና ነፋጊ ሊሆን አይገባውም ፈርጅ አገር ስትኖር አገርህ ነው ብሎ መኖሪያ ይሰትሃል ዚግነት ይሰጥሃል ያ እና ይህ የተለያዩ ናቸው ኦሮሞው ሲሰፍር አምሃራው ነበረ ጉራጊምነበረ ወላሞም ነበረ አፋርም ነበረ ስለዚህ አገሪቱ ኢትዮፒያ መሆናን እና የሁሉም አገር መሆናን ማመን ነው ኦርሞሞ መብቱን ለማስጠበቅ ኢትዮፒያዊነኝ ብሎ ማመን አለበት ካመነ የኦሮሞ ትግል የኦሮሞ ተቃውሞ አመጽ አያስፈልገውም እንደ አምሃራው እና እንደ ኢትዮፒያኖች 25 አመት የነጻነት ጥያቂ እየጠየቁነው ያንን መቀላቀል አለበት ከወያኒጋ ከሃሰተኛና ከባንዳጋ ከመቆም ለውነት ቆሞ እስከመጨረሻው ነጻነት ለህዝብ ማስረከብ ጥሩ ነው

  13. ገብሬ: -ልክ ነሽ ሱሉልታ የነበሩት ፓሊሶች ቀንድ ያላቸው የመቀሌ አማሮች ነበሩ። ለነገሩ የኢንሳ ፈታላ ነሽ መሰለኝ!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*