እሳት ላይ ሕዝብን ጥዶ እያመሱ የሚደረግ የትግል ሽሚያ ይቁም!!! የእርስ በእርስ መነካከሱ አንድም የወያኔን እድሜ ማስረዘም ሲልም የሕዝብን ስቃይ ከማባባስ አያልፍም:: ‪

#‎Ethiopia‬ : እሳት ላይ ሕዝብን ጥዶ እያመሱ የሚደረግ የትግል ሽሚያ ይቁም!!!የእርስ በእርስ መነካከሱ አንድም የወያኔን እድሜ ማስረዘም ሲልም የሕዝብን ስቃይ ከማባባስ አያልፍም:: ‪

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኢትዮጵያ ያለው የወያኔ አገዛዝ በሕዝቦች ላይ የሚያደርሰው በደል እጅግ ብዙና ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም እስከዛሬ በሃገሪቱ ከነበሩት አምባገነን አጼዎች እና ወታደራዊ አምባገነኖች በተሻለ መልኩ ወያነ በኢትዮጵያውያን ላይ ከባድ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል::በአሁኑ ወቅት አስፈላጊው እና ዋነናው ጉዳይ ይህንን አደገኛ የማፍያ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመው ወንጀል ከነአገዛዙ ለማስወገድ የሚደረጉ ትግሎችን ማቀናጀት ነው:: የተቀናጀ የተደራጀ ትግል ፋይዳው ስኬት ብቻ ነው ይህ ስከት ደሞ በተግባር እንዲተረጎም በጋራ ጭቆናን በመታገል ማስወገድ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል::ጭቆናን እናስወግዳለን ብለው ከተነሱ ሃገር ወዳድ ዜጎች ጀምሮ እስከ እናት ጡት ነካሾች ድረስ ስለ ነጻነት እና መብት እየጮኽ ይገኛሉ::እከሌ አገር ወዳድ ነው እከለ በኢትዮጵያ ሃብት ተምሮ ዛረ ላይ ተቀምጦ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እና ባንድራ ይፈልጋል የሚል መከፋፈል ውስጥ ባንገባም ሁለቱም አካላት ግን በየፊናቸው ላይስማሙ ትስማምተው ፖለቲካዉን እያጦዙት ሲገኙ ሕዝቡ በመሃል እየተጎዳ በአምባገነኦች እየተረገጠ ቀጥሏል::

ከስድብ ፖለቲካ እና ከኩርኩም ሲልም ከሆያሆየ እና ከነፈሰበት መንፈስ ብሎም በሰዎች ማምለክ ላይ መመስረት ያልወጣው ፖለቲካችን በትግል ሽሚያ ላይ የሚያነጣጥረው ፖለቲካችን ለሕዝብ የፈየደው አንዳችም ጥቅም የለም::ሕዝቦች ብሶት ፈንቅሏቸው ለተቃውሞ በወጡ ጊዜ ሁሉ ባልዋሉበት ኩበት ለመልቀም የሚንጠራሩ ፖለቲከኞች የህዝብ ልጆች በተሰዉ ሰአት ሁሉ ካድሬዎችን በስማርፎት እና በዶላር በመደለል ከፎቶ እና ቭድዮ ውጪ ምንም ያልፈየዱ በሚዲያ ስም የተደበኩ ግልሰቦች እየተነሱ የሕዝብን ትግል የኛ ነው ቢሉ መስሚያችን ጥጥ ነው::ከዚሁ ሁሉ ግን በግራ እና ቀኝ ጽንፍ ቆሞ ከመነካከስ በቃላት ጦርነት ከመወራወር በሃገራዊ አጀንዳ ላይ የተሞረኮዘ ስራ ቢሰራ ትልቅ እመርታ ይኖረዋል::የሕዝብን ብሶት ሕዝብን ለመለያየት ከመጠቀም አሊያም ለድርጅት የፖለቲካ አጀንዳ ለማዋል ከመንጠራራት ተጠራርቶ እና ተመካክሮ በሰለጠነ ፖለቲካ በትልቅነት እና ቀና መንፈስ ስል ሕዝብ ለሕዝብ የነጻነት ጎህ መፈንጠቅ ችላ ሊባል አይገባም::ካልሆነ የሕዝብን ሰቆቃና የወያኔ ስልጣን ከማስረዘም አይታይም::

የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን ችግር እንዲሁም ትግል የድርጅት አሊያም የሚዲያ ማድመቂያ እንዲሆን ማናችንም አንፈልግም::የምንታገለው እኮ እንዲህ አይነቱ እኩይ ተግባር እንዲቀር እው;;በአሁኑ ወቅት ማንም ሕዝብ በራሱ አነሳሽነት እና በገነፈለው ቁጣ ስም አጀንዳውን እንዲያስፈጽም ለማንም አንፈቅድለትም::በየቦታው የተነሱ የሕዝብ ተቃውሞዎች በነማን እንዴት እና ለምን እንደተነሱ ጠንቅቀን እናውቃለን::ቅጥረኛ ካድረእዎችን በደላልነት አስቀምጦ የሚለፍፍም ይሁም ባልዋለበት ኩበት የሚለቅም ያልሰለጠነ ፖለቲካ አንፈልግም::ይህ ከወያነ ድድብና አይለይም::ሊታስብበት ይገባል::የእርስ በእርስ መነካከሱ አንድም የወያኔን እድሜ ማስረዘም ሲልም የሕዝብን ስቃይ ከማባባስ አያልፍም::እሳት ላይ ሕዝብን ጥዶ እያመሱ የሚደረግ የትግል ሽሚያ ይቁም!!!‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

6 Comments on “እሳት ላይ ሕዝብን ጥዶ እያመሱ የሚደረግ የትግል ሽሚያ ይቁም!!! የእርስ በእርስ መነካከሱ አንድም የወያኔን እድሜ ማስረዘም ሲልም የሕዝብን ስቃይ ከማባባስ አያልፍም:: ‪”

  1. እሳት ላይ ሕዝብን ጥዶ እያመሱ የሚደረግ የትግል ሽሚያ ይቁም!!! የእርስ በእርስ መነካከሱ አንድም የወያኔን
    እድሜ ማስረዘም ሲልም የሕዝብን ስቃይ ከማባባስ አያልፍም:: ምኒልክ ሳልሳዊ ፦

    እጅግ በጣም ጥሩ ታዝበሓል! ብሶት የወለደውን ሕዝባዊ ትግል በተቃዋሚ ስም ቀምተው የራሳቸውን
    ከወያኔው ያልተለየ አጀንዳ ለማስፈፀም የሚሮጡት እጅግ በጣም ብዙ ናቸው እንዲያውም ከዚያ ባለፈ
    መንገድ ማፊያውን ቡድን እንደራደረው የሚል አስገራሚ ቲያትር እየሰሩ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው
    ተቃዋሚ መሰል ወያኔወች ምንም አይነት አጀንዳ ሳይኖራቸው በሚዲያ ላይ በተመሰረተ ፕሮፖጋንዳ ብቻ
    ተቃዋሚ በመምሰል ትግሉን የሚጎዳ ተለጣፊነትን እንደስልት አድርገው ይዘውታል። መቸ ይኸ ብቻ
    ተቃዋሚ መሰል ግሩፖች ዛሬ ከአንዱ ጋር ነገ ደግሞ ከሌላው ጋር እየተለጠፉ ጠንካራ አገር ወዳድ
    ተቃዋሚ ድርጅቶችንና ግለሰቦችልን በሚጠቀሙበት ሚዲያ በማግለል፤ በማዋክብና ተስፋ በማስቆረጥ
    አዳክመው ለሓገሪቱና ለሕዝባችን ተቆርቋሪ በማሳጣት የሀገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ እያጨለሙት ነው
    ይህንኑ እኩይ ድርጊታቸውን ያለምንም ማፈር በአደባባይ እየነገሩን ነው። ታዲያ በዚህ አስተዛዛቢ ወቅት
    እንደ አንተ ያለው ቅን መካሪ ወግን ለሕዝባችንና ላገራችን እጅግ ይጠቅማልና በርታ እላለሁ።

  2. tikikil new

    beteley ke shabya ena le OLF gar teselfew

    ke setan garim behon abren serten

    4 kilo engebalen yemelutin and belulin

    tiglun yadakemut enesu aymesluhim Minilik ??????? KKK

  3. Yenie melkt: be andit ethiopia/
    ethiopiawinet amnachuh,
    Tere-tgrai woyanie tagay
    yehonachum tebabren woyanien
    medemses alebn.
    Yetgl sltachn:
    le Tere-woyanie tglachn miTeqm
    kehone diablosawi bihonm
    leTelatachn woyanie,
    ethiopian/hzbuan miTeqm
    yehonena leneTanet miyabeqan
    slt hulu meTeqem alebn.
    LeTelatachn letgrai woyanie
    yemayamch, lerasachn mimech
    yetgl slt meTeqem alebn.
    Bemeselachuh mkniyatawi
    leneTant bemiTeqm slt woyanien
    kerkruna ywdem.

  4. I can understand the intention of this piece but totally inclined. The sources of the differences in their entirety are such tilted comments.It is boldly clear who the writer is trying to favor and critisize.How can one dare say that this is a a balanced comment? This is a sort of accusition, however I feel that the relation would largely benefits from genuine comments. As to me the criticized body are comparatively better based on facts on the ground!

  5. This the perfect
    Political analysis that is based on the fact on ground.
    You remember when the protest first
    began all claimed as if they lead it.
    As soon as its hijacked by the Radical Jihhadist
    Jawar and Brehnu
    ( G7 ) Calls the protesters to intensity and continue to Protest
    Woyane starts the counter attacks and
    turned out a bloody
    chaos. To most of us the Oromo people
    the above mentioned
    two individuals should be held accountable for the
    death of inocent young students from all ethnicities .

  6. Thanks Minilik Salsawi the best analysis I have never read in any
    website . The problem is there are
    power thirsted groups who are ready
    to hijack any protests to there advantage like G7 & the radical Jihhadist lead by Jawar Mohammed Mencha.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*