መንግስት የህዝበ ሙስሊሙን ኮሚቴዎችንና ቤተሰቦቻቸውን በቃሊቲ ማወከብ መቀጠሉ ታወቀ ።

መንግስት ኮሚቴዎቻችንና ቤተሰቦቻቸውን በቃሊቲ ማወከብ መቀጠሉ ታወቀ ።

ሬዲዮ ዳንዲ ሀቃ ጥር 11 /2008

የህዝበ ሙስሊሙን የመብትጥያቄ : ይዘው መፍትሄ ለማፈላለግ በመንቀሳቀሳቸው ብቻ በአምባገነኑ ስርአት እጅ ወድቀውና : በመንግስታዊው የካንጋሮ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው : ከሰባት አመት እስከ ሀያ ሁለት አመት ተፈርዶባቸው : በየማጎሪያ ጣቢያው ታጉረው በሚገኙ የህዝበ ሙስሊሙ መሪዎች ላይ : አንባገነኑ ስርዓት እያደረሰባቸው ያለው ግፍ አሁንም መቀጠሉ ታወቀ ።ፖሊሱን ስሙን ቢጠይቁትም ስሙን ሊናገር ማን እንዳዘዘው ቢጠይቁትም ያዘዘውን አካል መናገር አልፈለገም ።

ኮሚቴዎቻችንም የሰው መብት ለመጣስ ከመነሳትህ በፊት ስለ መብት ልታውቅ ይገባል እያሉ መብቱን የማያውቅ ተላላኪ መሆኑን አስደረድተውታል ።

የኮሚቴዎቻችን ቤተሰቦች ከኮሚቴዎቻችን ጋር ሳይገናኙ ምግቡን ብቻ ሰጥተው መመለሳቸው ታውቋል ።

በተያያዘ ዜናም ባለፈው ሳምንት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የእስር ቤቱ ሃላፊዎች መልካም አስተዳደርን በሚመለከት እስረኞችን ሰብሰበው ባነጋገሩበት ወቅት : በእስር ቤቱ ሁሉ ነገር የተሟላ ይመስል ምን ችግር አለ ብለው ሲጠይቁ :ጀግኖች ኮሚቴዎቻችንም በእስር ቤቱ ምንም አይነት መልካም አስተዳደር የሚባል ነገር እንደሌለ መግለፃቸው ተውቋል ።

በስብሰባው ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ኮሚቴዎቻችን መልካም አስተዳደር እንደሌለ ካስረዱባቸው መገለጫዎች መካከል ሌላው ቀርቶ በእስር ቤቱ ህገ መንግስቱ ያስቀመጠው ሁሉም ሃይማኖት እኩል ነው የሚለው እንደማይከበር ገልፀው ።

በእስር ቤቱ በቆዩባቸው አመታት ብዙ የሙስሊም አመታዊ በአላት ቢያልፋም እንደ ሌላው እምነት በዓላት አንድም ቀን ለሙስሊሙ እስረኛ በሬ ታርዶ አለማየታቸውን ገልፀዋል ።

ይህ ማለት ግን ለሌሎች እምነት ተከታዮች ለምን ተደረገ ማለታቸው እንዳልሆነ በግልፅ ቋንቋ ነግረዋቸዋል ።

ከዚህ በተጨማሪም ኮሚቴዎቻችን ሌሎች በእስር ቤቱ አየተፈፀሙ ያሉ ህገ ወጥ ተግባሮችን እያነሱ መልካም አስተዳደር የሚባለው ነገር በግቢው ውስጥ ፍፁም እንደሌለለ በግልፅ ቋንቋ አስቀምጠውላቸዋል ።

ኮሚቴዎቻችን በተገኘው አጋጣሚ የአምባገነኖችን ህገ ወጥ ስራ ማጋለጣቸውና ወኔያቸው እንዳለ መሆኑ እንቅልፍ የነሳቸው የአምባገነኑ ስርዓት ደህንነቶች በእነርሱ ላይ እያደረሱ ያሉትን በደል አጠናክረው ቀጥለዋል ።

ኮሚቴዎቻችን በግፈኞች እጅ ሆነው አሁንም አምባገነኖችን ይጋፈጣሉ አሁንም ለመብታቸው ይታገላሉ ።

እኛስ ትላንት ኮሚቴዎቻችንን መርጠን የላክናቸው ሙስሊሞች ምን እየሰራን ነው ?
ለትግሉስ ምን እያበረክትን ነው? እኛ ብንተኛም እነርሱ እንደማይተኙልን እያሳዩን ነውና : ሁላችንም ትግሉ ግቡን እንዲመታ የአቅማችንን እናበርክት ።

Ayda Fuad Ayda Fuad's photo.