የተባበሩት መንግስታት ሶሪያና ኢትዮጵያን በአንድ ምድብ አስቀምጧል : በሁለቱ አገራት ያለው ሁኔታ ለህፃናት አስፈሪ ሆኗል ::
የተባበሩት መንግስታት ሶሪያና ኢትዮጵያን በአንድ ምድብ አስቀምጧል : በሁለቱ አገራት ያለው ሁኔታ ለህፃናት አስፈሪ ሆኗል ::

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ የቅርብ ዓመታት ታሪክ ውስጥ እጅግ ከፍተኛው በመሆን የተመዘገበው ድርቅ 400.000 ህፃናትን ለአልሚ ምግብ እጦትና 10 ሚልዩን የሚደርሱ ሰዎችን ለምግብ እርዳታ ፈላጊነት ዳርጓቸዋል ብሏል ።
ድርጅቱ በሶስት አስርት ዓመታት ታሪኳ አስከፊው ድርቅ በመሆን የተመዘገበባት ኢትዮጵያ መጥፎውን ጊዜ እንድትቋቋም የ50 ሚልዮን ዶላር እርዳታ ከለጋሾች ጠይቄላታለሁ ማለቱን አልጀዚራ ዘግቧል ።
ሴቭ ዘ ችልድረን በመግለጫው በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ልክ በሶሪያ ያለው ጦርነት ለህፃናት ህይወት አስጊ እንደሆነው በአገሪቱ ለሚገኙ ህፃናትም ድርቁ በአስጊነቱ በተመሳሳይ ደረጃ የሚገለጽ ነው ብሏል ።
የህፃናት አድን ድርጅቱ ተወካይ ካሮሊን ሚልስ “በአለም ላይ ያሉን የአስቸኳይጊዜ እርዳታ ፈላጊዎች ምድብ ሁለት ናቸው ።ሶሪያ አንደኛዋ ስትሆን ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ናት።ለአስቸኳዩ ችግር መፍቻ 100 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ብለናል “ማለታቸው ተሰምቷል ።
አልጀዚራ በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ድርቅ ያናገረው የአስር ልጆች አባት ሙሐመድ ዱባለ ከድርቁ በፊት 53 ላሞች እንደነበሩት በማስታወስ አሁን የቀሩት አምስት ብቻ መሆናቸውን ይገልጻል ።
ሙሐመድ ለሁለት ጊዜያት ከመንግስት የምግብ እርዳታ ቢያገኝም ከድርቁ ስፋት የተነሳ በቂ አለመሆኑን ይናገራል ።
ሙሐመድ “ለህዝቡና ለልጆቻችን በጣም ሰግቻለሁ ምክንያቱም ዝናብ የለም ።ዝናብ ከሌለ ደግሞ ምግብ ና ወተት ስለማይኖር ሰዎች ይሞታሉ “ብሏል። ( Dawit S. Yemesgen)
