የድድ መድማት
የድድ መድማት
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
የድድ መድማት የድ ድ ላይ ችግርን እንዲሁም ከባድ ለሚባሉ የጤና እክሎች መዳረጋችንን ጠቋሚ ምልክት ሊሆን ይችላል።
✓ የድድ መድማትን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች
አንዱና ዋነኛ ምክንያት የድድ መቆጣት (inflamed gums) ወይንም ጅንጂቫይተስ (Gingivitis) ነው።
በድድ መካከል የሚጣበቅ ቆሻሻ (plaque) ካልተወገደ ጠጣር ይሆንና የዽ መድማተን ያስከትላል።
✓ ሌሎች ምክንያቶች ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል።
* የሚታወቅ የመድማት ህመም መኖር
* ጥርስን ሀይልን በመጠቀም ማጽዳት
* በእርግዝና ጊዜ የሚከሰቱ የሆርሞን ለውጦች
* የጥርስ ወይንም የዽ ኢንፌክሽን
* የደም ካንሰር
* ደም ማቅጠኛ መድሀኒቶችን መጠቀም
* የቫይታሚን ኬ እጥረት
* በአግባቡ ይልተደረጉ አርቴፊሻል ጥርሶች ናቸው።
✓ እርስዎ ምን ማድረግ ይችላሉ
* ጥርስዎን በሚፈቁ ጊዜ በዝግታ መሆን ይኖርበታል። በቀን 2 ጊዜ ቢያጸዱም ይመከራል።
* የድድ መድማት ካለዎት አልኮል ያላቸውን ጥርስ ማጠቢያዎች መጠቀም የለብዎትም ሁኔታውን ያባብሳልና።
* ጥርስዎን በአመት 1 ጊዜ በባለሙያ ይታጠቡ።
* ሲጋራ የሚያጤሱ ከሆነ ቢያቆሙ ይመከራል።
* ድድዎ በሚደማ ጊዜ በጎዝ ወይንም ጥጥ ቀዝቃዛ ውሃ ነክረው ይያዙበት።
✓ ሃኪምዎን ማማከር የሚገባው መቼ ነው።
* ለረዥም ጊዜ የድ ድ መድማት ካለብዎ
* ሌሎች ተያያዥ የህማም ስሜት ከተሰማዎ።
* ከህክምና በኋላ መድማቱ ከቀጥለ ናቸው።
ጤና ይስጥልኝ
ይህን በቪድዮ የታገዘ መረጃ ይከታተሉ
http://www.honeliat.com/what-causes-bleeding-gums/
