የጂቡቲ የጸጥታ ሃይሎች ዛሬ በአንድ ሀይማኖታዊ ኩነት ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች ሞተዋል – VOA
የጂቡቲ የጸጥታ ሃይሎች ዛሬ በአንድ ሀይማኖታዊ ኩነት ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሶማልኛ አገልግሎት ተናግረዋል።
የጸጥታ ሃይሎቹ ሃይማኖታዊው ኩነት እንዳይካሄድ ያስጠነቀቁ ቢሆንም አዘጋጆቹ ችላ እንዳሉትና ሟቹ ሃይማኖታዊ መሪ ሼኽ ዮኒስ ሙሴን ለማሰብ እንደተሰባሰቡ ምንጮች ጠቁመዋል።
የጸጥታ ሃይሎቹ የተሰባሰቡትን ሰዎች ለመበተን ሞክረው እንደነበር ጂቡቲ ያሉት ጋዜጠኞችና እማኞች ተናግረዋል። በሀገሪቱ ያለ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ቢያንስ ሁለት ሰዎች እንደተገድሉ ዘግቧል። ሌሎች ምንጮች ደግሞ ከዛ የበዛ ነው ይላሉ። የዜና ዘገባውን ያዳምጡ → listen