ከልደታ ፍርድ ቤት በርካታ እስረኞች አመለጡ፤ አካባቢው በተኩስ ተናወጠ


የአይን እማኞች እንደሚገልጹት እስረኞች አምልጠዋል በሚል ከሃያ በላይ የጥይት ድምጾችን ሰምተዋል፡፡ በተለይም በዛሬው ዕለት በዚሁ ፍርድ ቤት መምህር ግርማ ቀጠሮ ስለነበራቸው በርካታ ሕዝብ በአካባቢው ይገኝ እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸው ተኩሱ በተሰማበት ወቅት ፖሊስ ዛሬ በዳኛ አለመኖር ወደ ነገ ቀጠሯቸው የተሻገረው መምህር ግርማን በአስቸኳይ ይዞ ወደ ማረፊያ ቤት ይዟቸው ሄዷል