ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ

የሕዝቦችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች በመጣስ የሚከናወኑ የኢህአዴግ ሕገወጥ እርምጃዎች ሕዝባችንን ለከፍተኛ ችግር፣ ሀገራችንንም ለአሳሳቢ ሁኔታ እየዳረጉ ስለሆነ በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል!!
(ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ)
የኢህአዴግ አገዛዝ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በተግባር ሊያውላቸው ያልተዘጋጀባቸውን ድንጋጌዎች ከሀገሪቱ ሕገመንግሥት ጀምሮ ሲያውጅ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ያወጃቸውን ድንጋጌዎች በማፍረስና በተግባር እንዳይውሉ በማድረግ የዜጎችንና የሕዝቡን መብቶች የሚጥሱ ተግባራትን እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ይህ ሁኔታ ከአንድ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት በጉልበትና በማጭበርበር ቀምቶ መንግሥት ነኝ ከሚል አምባገነን ቡድን የሚጠበቅ ቢሆንም፣ መዘዙ የሀገራችንን ደህንነትና የሕዝቦቻችንን እኩልነትና አንድነት ለማይሹ ኃይሎች አፍራሽ እንቅስቃሴ ቀዳዳ እየሰጣቸው መሆኑ መድረክን በእጅጉ ያሳስበዋል፡፡
ከእነዚህ ሕገመንገሥታዊ ድንጋጌዎች ጥሰት መነሻነት ከተፈጠሩት ውስብስብ ችግሮች ውስጥ አንዱ የአዲስ አበባ ከተማንና የኦሮሚያን ክልላዊ መንግሥት ግንኙነት በሚመለከት፣ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 “የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሐል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል” የሚለውን በማንአለብኝነት ከመጣስ የመነጨ ችግር ነው፡፡ በዚህ ረገድ የኢህአዴግ ሥርዓተ-አልበኝነት መገለጫ ሆኖ የቆየው በሕገመንግሥቱ የሰፈረው ዝርዝር የአፈጻጸም ሕግ ሳይወጣ ከ21 ዓመታት በላይ መቆየቱ ተጠቃሽ ነው፡፡ እንዲሁም በአዲስ አበባ አከበቢ የሚሠሩ የልማት ሥራዎችንም በሚመለከት ሕዝቡን በአግባቡ ሳያወያዩ ጥቂት እበላ ባይ ካድሬዎችን በአስፈጻሚነት በማሰማራት የእርሻ መሬታቸውን እየነጠቁ ወደ አዲስ አበባ ከተማ የማካለል እንቅስቃሴ ላይ መሠማራቱ በተከታታይ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችንና ውዝግቦችን ከማስነሳቱም በላይ ለብዙ ዜጎች ሕይወት በኢህአዴግ መንግሥት አርመኔአዊ እርምጃ መቀጠፍ ምክንያት ሆኖአል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአዲስ አበባ ከተማን ከሕግ አግባብ ውጪ ማማስፋት ጋር በተያያዘ በሕዝቡ ዘንድ ካደረው ስጋት በመነሳት የተቀሰቀሰውን ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞን በኃይል ለማስቆም የኢህአዴግ መንግሥት በወሰደው እርምጃም በርካታ ተማሪዎችና ሌሎች ዜጎች መገደላቸውን መድረክ በእጀጉ ይኮንነዋል፡፡

የተገደሉት ዜጎችም 1ኛ፡- ተማሪ ካረሳ ጫላ ምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ፣ 2ኛ፡- ተማሪ ጉቱ አበራ ምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ፣ 3ኛ፡- ተማሪ ሚፍታህ ጁንዲ በምዕራብ ሐረርጌ በደኖ ወረዳ፣ 4ኛ፡- ተማሪ ገዘሃኝ ኦልሂቃ የሀራማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪ፣ 5ኛ፡- ተማሪ ደጀኔ ሰርቤሳ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ቶሌ ወረዳ፣ 6ኛ፡- ተማሪ በቀለ ሰቦቃ አዳበርጋ ወረዳ ሙገር፣ 7ኛ፡- ተማሪ በቀለ ሰይፉ አዳበርጋ ወረዳ ሙገር፣ 8ኛ፡- ተማሪ ሙራዲ አብዱ የሀራማያ 2ኛ ደረጃ ተማሪ፣ 9ኛ፡- አቶ ጫላ ተሾሜ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ባቢቻ ከተማ፣ 10ኛ፡- ተማሪ አብደታ ባይሳ ምዕራብ ሸዋ ጫለያ ወረዳ ባብቻ ከተማ፣ 11ኛ፡- ተማሪ ዱሌ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣ 12ኛ፡- አቶ ታመነ ጸጋዬ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣ 13ኛ፡-ተማሪ ደረጀ ጋዲሰ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣ 14ኛ፡- ተማሪ ፈቃዱ ግርማ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣ 15ኛ፡-ተማሪ ሉጫ ገማቹ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ፣ 16ኛ ተማሪ አያና ባንቲ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ፣ 17ኛ፡- ተማሪ አላዛር ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ ነዋሪ 18ኛ አቶ ኤብሰ ቱጆ ሆሮ ጉዱሩ ፍንጫ፣ 19ኛ፡- አቶ ደበላ ጣፋ ጫንጮ ላይ ተገድሎ ተጥሎ የተገኘ፣ 20ኛ ወ/ሮ ዲሶ ሚሊኬሳ ሕልፈታ ወረዳ 21ኛ፡- አቶ አበበ ቡሎ ወሊሶ ከተማ፣ 22ኛ፡- አቶ ታዴ ሰፈራ አመያ ከተማ፣ 23ኛ፡- አቶ ሌንጮ ሁንዴራ ወሊሶ ከተማ፣ 24ኛ፡- አቶ ሰለሞን ሞገስ አማያ ከተማ፣25ኛ፡- አቶ ታዴ አንዲሳ ወንጪ ከተማ፣ 26ኛ፡- አቶ እናውጋው ኃይሉ ግንደበረት ወረዳ፣ 27ኛ፡- ተማሪ አብደታ ለታ ግንደበረት ወረዳ 28ኛ፡-አቶ ባይኢሳ ገደፋ አቡና ግንደበረት ወረዳ 29ኛ፡- ተማሪ አስቻለው ወርቁ ግንጪ ወረዳ፣ 30ኛ፡- ተማሪ ሰይፉ ቱራ ግንጪ ወረዳ፣ 31ኛ፡- ተማሪ አሸናፊ ግንጪ ወረዳ፣ 32ኛ፡- አቶ ገላና ባቃና ጪቱ ከተማ ነዋሪ የነበሩ ስለመሆናቸው የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ከዚህም ሌላ ከመቶ ባለይ ዜጎች ቆስለዋል፣ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእስራት ተዳርገዋል፡፡ ሰላማዊና ሕጋዊ ተቃውሞን ለማፈን በመንግሥት እየተወሰደ ያለው የኃይል እርምጃ እስከ አሁንም እንደቀጠለ በመሆኑ፣ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት መድረክን በእጅጉ እያሳሰበው ይገኛል፡፡ እንደዚሁም በቅርቡ በጎንደር ከተማ በሚገኘው ወሕኒ ቤት በእስረኞች ላይ የተፈጸመው ግዲያ መድረክን አሳስቦታል፡፡
ከዚህም ሌላ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ “የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው” የሚለውንና በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ የሚጠቀሙበት መሬት በነፃ የማግኘት፣ የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው” ተብሎ የተደነገገውን በመተላለፍ፣ በከተሞችና በእንቨስትመንት ማስፋፋት ስም የአርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን መሬት እየቀሙ በማፈናቀል ለከፍተኛ የኑሮ ችግሮች እየዳረጉዋቸው ይገኛሉ፡፡ መድረክ ይህንን የኢህአዴግ መንግሥት የመሬት ቅሚያ እርምጃ ደጋግሞ ሲያጋልጥ የቆየ ሲሆን በእርምጃው ምክንያት በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው የጉዳት መጠን ከጊዜ ወደጊዜ በአሁኑ ወቅት እየሰፋ ስለመገኘቱ መረጃዎች ያሳያሉ፡፤
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አገዛዙ በርካታ የሀገሪቱን ከተሞች ለማስፋፋትና መሬቱንም በፌዴራል መንግሥት ቁጥጥር ሥር በመሬት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ለማስተዳደር፣ የማስተር ፕላንና የሪፎርም ከተሞች ብሎ በመሰየም፣ በየከተሞቹ አከባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች ይዞታዎች አርሶ አደሩን ሳያማክሩና ተገቢውን ካሳ ሳይከፍሉ ወደ ከተማ ለማካለል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ነዋሪውን ሕዝብ ለከፍተኛ ስጋትና ጭንቀት እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡ ስለሆነም የኢህአዴግ አገዛዝ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በማንአለብኝነት አምባገነናዊ ስሜት እየተመራ ፌዴራላዊ ሥርዓቱንና የዜጎችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች በመጣስ እየፈጸመ ከሚገኘው ሕገወጥ ተግባር እንዲቆጠብ እንጠይቃለን፡፡ በተለይም፡-
1ኛ፡- ከአዲስ አበባ ከተማና ከኦሮሚያ ክልል ግንኙነት ጋር በተያያዘ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮች ሕገመንግሥቱን ተግባራዊ ባለማድረግ ምክንያት እየተከሰቱ ስለሆኑ የሕገመንግሥቱን አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 ተግባራዊ የሚያድርግ ሕግ በአስቸኳይ ወጥቶ ተግባራዊ እንዲደረግና ለችግሩ ዘላቂ እልባት እንዲሰጥ፣ ለከተማዋ ልማት የሚወጡ እቅዶችም የሕገመንገሥቱን ድንጋጌ የሚያከብሩ ሆነው የአከባቢውን አርሶ አደሮች መብትና ጥቅም በሚገባ የሚያስጠብቅ እንዲሆኑ፣
2ኛ፡- በቅርቡም መንግሥት ሕገወጥ እርምጃ ለመውሰድ በተንቀሳቀሰበት ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ባደረጉና በሌሎችም ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም፣
3ኛ፡- እስከአሁን የዜጎችን ሕይወት በሕገወጥነት ያጠፉና ሌሎች ጉዳቶችን ያደረሱ የመንግሥት አካላትም ለሕግ እንዲቀርቡና ለሟቾቹ ቤተሰቦችም ተገቢው ካሳ እነዲከፈላቸው እንዲደረግ፣
4ኛ፡- በመላ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ሕገመንግሥቱ ያረጋገጠላቸው ከመሬታቸው የያለመፈናቀል መብታቸው ተከብሮ፣ በየአከባቢያቸው በልማት ሥራዎች ሰበብ ኑሮአቸው እየተናጋ ለችግር የሚዳረጉበት ሁኔታ በአስቸኳይ ተወግዶ፣ የሚከናወኑት የልማት ሥራዎችም ቢሆኑ የአከባቢውን ሕዝብ ይሁንታ ያገኘና መብታቸውን የጠበቀ እንዲሆን እንዲደረግ፤
5ኛ፡- በተለይም በአሁኑ ወቅት ከተሞችን በማስፋፋት ስም የአርሶ አደሩን መሬቶች ወደ ከተማ ለማካለልና በከፍተኛ ዋጋ በሊዝ ለመሸጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ፣ አርሶ አደሩን በስጋት ውስጥ እየከተተው ስለሚገኝ፣ ኑሮአቸውን ለማሻሻል የሚበቃ በቂ ካሳ ሳይከፈል ይዞታቸውን ለመንጠቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዲቆም እንዲደረግ፣
6ኛ፡- በቅርቡ በጎንደር ከተማ በሚገኘው ወሕኒ ቤት የተገደሉ በርካታ ዜጎች ጉዳይ በአስቸኳይ ተጣርቶ የሰላማዊ ዜጎችን ሕይወት ያጠፉና ጉዳት ያደረሱ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡና ለሟቾቹ ቤተሰቦችም ተገቢው ካሳ እንዲከፈላቸው እንዲደረግ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
በመጨረሻም መድረክ በንጽሐን ዜጎቻችን ላይ በኢህአዴግ መንግሥት የተወሰደውንና እየተወሰደ ያለውን ኢሰብአዊ ግዲያ በጥበቅ እያወገዘ ለሟቾቹ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡ መላው ሕዝባችንም በኢህአዴግ በጉልበትና በማጭበርበር በተካሄዱት ምርጫዎች የተቀማውን ሕገመንግሥታዊ መብቶቹን ለማስከበር ሰላማዊ ትግሉን እንዲያጠናክር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ጥሪ ያቀርባል፡፡
ድል ለሕዝባዊ ትግላችን !!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ
ታህሳስ 5 ቀን 2008 ዓ ም
አዲስ አበባ

 

6 Comments on “ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ”

  1. መቶ በመቶ ያሸነፈው ወያኔ ሕዝብ እጨረሰ ነው ከተመረጠ ታድያ ለምን እመራዋለሁ የሚለው ሕዝብ በርሃብ፣በጥይት ይቆላል? አይደንቅም ጉድ ነው ነገሩ!
    በአማራና በኦሮሞ መካከል ያስነሳውስ ግጭት መቼ ይብዳል ትላላችሁ? አቅጣጫ ለማስለወጥ ጎሳን ከጎሳ ማጋደል፣መግደል ስራው የሆነው ወያኔ ጋር ያሉ ምሁር ተብየዎች እባከችሁ ሳይማር ራቁቱን እየሄደ ያስተማራችሁን ወገናችሁን አታጥፋ/አትጉዲት/!ጥፋት ይቁም
    ተው እንደሰው አስቡ?

    ሳተናው አሊ

  2. “Ye hagerachin deninetina ye hizbochachinin ekulinetina andinet lemaishu hailoch afrash enkiskase” malet lemin izih meglecha wust tetekese ?

    What does that mean ? Is it really from medirek or from other group? This is the usual tplf/wuyane statement. Before we go furthere we need more explanation. Talking about unity in a positive way ok. I am for unity. But attacking one group of people and employing the usual scare tactic is completely different. It looks like scrumbbiling for the power. We are not yet there. Think before you write.

  3. በ15 ቀን ባልሞላ የህዝብ አመፅ 32 ሠው ሞት እኮ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ነው ይህ ከቀይ ሽብር ምን ለየው ወገን በጣም አሣዛኝ ጭፍጨፋ ነው የተፈፀመው በኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ላይ ይህ አንድ ብሄርን ያተኮረ መሥሎን ከሆነ ተቃሥተናል በሌላም አጎራባች ክልልሎች ጎንደርንም ልንረሣ አይገባንም የቅማንት ህዝብ የመገንጠል ጥያቄ በሚል ሤራ ወያኔና ለራሡና ከፊሉን ለሡዳን የአባይን ግድብ ካሣ መሠጠቱ እጅጉን ከግንባራቸው ላይ ካለችው የሀዲድ ጠባሣ በከፋ ሠፊ የዝርፊያ ክሥተቶችን እንቢ ላገሬ ያለውን ቆራጥ ጀግና ህዝብን ርሸናውን ተያይዞታል ግን የት ሆኖ መኖር እንደፈለገ የሁላችንም እንቆቅልሽ ነው ትግራይን ገንጥሎ ለመኖር ድርቅ አሥቸግሮታል ታድያሥ እያናከሡ በእጃዙር የክልሎችን መሬት በሊዝና በልማት ሥም መውረሥ ከሆነ ከዚህ ከያሥነው የነፃነት ትግል የሞት ፅዋውን እንዲጎነጭ የየበኩላችንን ድርሻ እንወጣ።

    ሞት ለወያኔ!!!

    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

  4. “በኢህአዴግ በጉልበትና በማጭበርበር በተካሄዱት ምርጫዎች የተቀማውን ሕገመንግሥታዊ መብቶቹን ለማስከበር ሰላማዊ ትግሉን እንድናጠናክር”

    ወያኔ ሊወገድ ግድ ይላል!

  5. የተከበራችሁት እድምተኞ የወያኔው ኢንሣ አሁን በደረሠን መረጃ መሠረት mereja.com/amharic ብሎክ መደረጉን በ አ.አ ያሉ ተከታታዬቻችን ነግረውናል እናም ነፃ የVPN አገልግሎት ዳውን ሎድ አድትጋችሁ እንድትጠቀሙ ሞያዊ እገዛዬን ለግሣለሁ።

    ሞት ለወያኔ

  6. We know that from long tome that Wayne is the fascist anti unity of the country and organized systematic tribal conflict among tribes, enmity and hatrat among peace loving people who lived together for over tens of thousands of years.
    They sold our country 1600 km to Sudan along from north Of the country to Gambela and 60 km of land to deep into the country.they don’t care for the rest of people except few Fascist Tigray people who live like donkey never one day think of their country and their people .On the contrary there are millions of peace loving Tigray people who are victims of this regime because speaking out oppositin their evil and ruining the country, massacring all people regardless of what.
    The Killing of hundreds of Oromo student, thousands of Oromo people dislocation of their land and become watch man for those snatched the land made them homeless on their door steps where their ancestors’ land.moreover about 50,000 innocent intellectual Oromo and the most productive and well educated and skilled person put behind bars and some are taken from home and never seen the rising Sun,even their bodies have not discovered yet.
    Because of WAYNE ETHIOPIA become grave yards for her children. How many Amhara people were displaced for jut being Amhara, some are being buried alive in Harar and some are rolled down from the top of THE HIGHEST mountain being tie up of rope in the region, How many Amhara were killed in Ariba Minchi by the order of Meles Zenawi and implement by Shiferawu Shigute the EPRDF killing machin or the slave of Wayne.
    How many Gambela our brothers were murdered just because of their fertile land just to give to Tigray people who are cooperating in killing innocent fellow Ethiopian for the sake of their evil political agenda.

    This is message to all peace loving Ethiopian Wayne is A CANCER who kills and destroy the nation for generations to come.Therefore for us to live peacefull in unity and harmony. We should united as one and remove this CANCER CELL. No matter which tribe we are at the end of the day Ethiopianism is more colour full than single out.

    To the soldiers of WAYNE Ethiopian is your country because of benefits which can’t stay for while and worthless fleeing, do not kill your own father, mother, brother and sister moreover your country then you will be judged by history and God
    Long life for Ethiopian Peace loving PEOPLE
    Tekily

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*