በሸዋ ወለጋ ባሌ ሃረርጌ ክፍለሃገራት የህዝቡ ጥያቄ ወደ ሕዝባዊ አመጽ እየተለወጠ ስለሆነ ለአብዮቱ እያንዳንዳችን በተጠንቀቅ ዝግጁ እንሁን::
የህዝቡ ጥያቄ ወደ ሕዝባዊ አመጽ እየተለወጠ ስለሆነ ለአብዮቱ እያንዳንዳችን በተጠንቀቅ ዝግጁ እንሁን::
#Ethiopia #Ethiopianuprising #Oromoprotests #Miniliksalsawi #Change
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሕዝቡ ጥያቄውን አደባባይ ይዞ መውጣቱን ቀጥሏል::የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን የሚቃወመው ሕዝብ በየአከባቢው ከተማሪው ጋር በጋራ በመቆም የፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎቹን ይዞ ድምጹን ማሰማቱን ቀጥሏል::ይህ ወሳኝ የሆነ ለለውጥ የተዘጋጀውን አብዮት እያንዳንዳችን በንቃት ልንሳተፍበት እና ወደ ሕዝባዊ አመጽ በመቀየር አምባገነኑን የወያኔ ስርዓት ልናወርደው ይገባናል::
በሮቤ ኡኬ ወሊሶ በዶዶላ በጊንዶ በሃዋሳ ዩንቨርስቲ እና በሸዋ ወለጋ ባሌ ሃረርጌ ክፍለሃገራት የተነሱ ተቃውሞዎች ቀጥልው የዋሉ ሲሆን ሕዝቡ ለውጥ እንደሚፈልግ በአንድነት በተግባር ያስመሰከረባቸው ሰልፎች ተካሂደዋል::ተከታታይ ሰልፎች እንደሚካሄዱም ከየአከባቢው የሚገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ ሁላችንም ለለውጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፏችን እንድንቀጥ እና በማስተባበር እና በመቀስቀሱ የያዝነውን ተግባራዊ ስራ አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል:: #ምንሊክሳልሳዊ
