በአዲስ አበባ የተካሄደው ውይይት አነጋጋሪ ሆኗል

– «ሙስናን ለማጥፋት ምን ዕቅድ ተይዟል?» ተሰብሳቢዎች
– «የቀረቡትን ጥያቄዎች በፀጋ እንቀበላቸዋለን»  አቶ ግርማ ብሩ

(በውድነህ ዘነበ)

ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተጀመረው የአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት ላይ ተሰብሳቢዎች ትኩረት አድርገው የሚያነሱዋቸው ጉዳዮች በከተማው ውስጥ ባሉ ችግሮች ላይ ቢሆንም፣ የከተማው አስተዳደር የራሱን የአምስት ዓመት ዕቅድ ከአንድ ዓመት በፊት በማፅደቁ ምክንያት የውይይቱ ጠቀሜታ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡