አቶ አላሙዲና የዘረፋ ግብረአበሮቹ በአሜሪካ ፍርድቤት ሽንፈትና ቅሌት ተከናነቡ::
የወያኔ አገዛዝ ዋና ደጋፊ የሆኑት ቢሊየነሩ መሃመድ አላሙዲን በአሜሪካን አትላንታ በኢትዮጵያ ሪቭው አዘጋጅ በጋዜጠኛ ኤሊያስ ክፍሌ ላይ የከፈቱት ክስ ውድቅ መሆኑ ታወቀ::

በአትላንታ የሚገኘው ፍርድ ቤት አላሙዲን እና ግብረ አበሮቹ እነ ጀማል አህመድ ከነሃሴ 2012 ጀምሮ በጠበቃቸው ዲኤልኤ በኩል በኢትዮጵያ ሪቭው ድህረገጽ ላይ እኔን እና ቤቴሰቤን የሚጎዱ ጽሁፎች ወጥተዋል በሚል በጋዜጠኛ ኤሊያስ ክፍሌ ላይ የመሰረቱት ክስ ሽንፈት እንዳከናነባቸው ታውቋል::ከ2010 ጀምሮ በጋዜተኛ እሊያስ ክፍሌ ላይ በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች ክስ ሲመሰርቱ የነበረው መሃመድ አላሙዲ በአትላንታ ዲስትሪክት ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ያቀረቡት ክስ ለክስ የሚያበቃ ሕጋዊ መሰረት የለውም በሚል ተቀባይነት ማጣታቸው ታውቋል::እንዲሁም ለኤሊያስ ክፍል ያወጣውን ወጪ አላሙዲን እንዲከፍሉት አዘዋል::
በየካቲት 2015 ጋዜጠኛ ኤሊያስ ክፍሌ አላሙዲን ላይ በጻፋቸው ጽሁፎች መረጃዎቹን /ምንጮቹን እንዲናገር ቢወሰንም ጋዜጠኛ እሊያስ ክፍሌ በኢትዮጵያ ያሉ ምንጮቼ ለሕይወታቸው አደጋ ስለሆነ ምንጮቹን ለመናገር ፈቃደኛ አይደለሁም በማለት ይግባኝ የጠየቀ መሆኑ ሲታወስ ይግባኙን የተቀበለው ፍርድ ቤት በሕጉ መሰረት ከሕግ ውጪ የሆነ ምንጮቹን እንዲናገር ማስገደድ እደማይቻል ወስኗል::በአሜሪካን አገር የመናገር ነጻነት እና የፕሬስ ነጻነት የተከበረበት መሆኑን የዘነጉት ከጀርባቸው ወያኔ ታዝሎ ጋዜጠኛ ኤሊያስ ክፍሌን ለማጥቃት አላቡዲን እና ተባባሪዎቹ እነ ጀማል አሕመድ በአሜሪካን ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ እፍረትን ተከናንበዋል::
