በሕወሓት የበላይነት የብአዴን አስረሽ ምችው – ፈንጠዝያ ባርነት እስከመቼ ?

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃ ትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት ታላቋን ትግራይን እፈጥራለሁ ያለውን ሕወሓት የትግሉ ስኬት ሲከሽፍበት ኢሕዴንን እና ኦሆዴድን በመንተራስ ተረማምዶ ለስልጣን ከበቃ 25 ድፍን አመታትን አስቆተረ::

Minilik Salsawi's photo.

በ25 አመት የስልጣን ቆይታው የኢሕዴንን እና የኦሕዴድን የትግል አስታውጾ ላማኮላሸት እና ከታሪክ ሂደት መስመር ለማሳት የተጠቀመባቸው ዘዴዎች እና ወታደራዊውን እና የደህንነቱን ተቋም በአንድ ብሄር በማጠር አባል ድርጅቶቹ እና አባላቱ መላወሻ እንዲያጡ ሲሰራ በአደባባይ ታይቷል::ከአቶ ታምራት ላይኔ የፖለቲካ ጠለፋ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባሉ የኢሕዴን ታጋዮች እና ካድሬዎች በተለያዩ የወንጀል ልጣፎች ከያሉበት ተጠልፈው ወደ ሞት እስር እና ስደት ተግዘዋል:: የኦህዼድ አባላትንም እንዲሁ በመጥለፍ በፖለቲካዊ የኦነግ ታርጋ በማሰር በመግደል እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በማሸት አንደበታቸውን አሽጎታል:: ይህ የሕወሓት ስራ ማንም የሚያውቀው እና ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው:: ቢተነተን የማያልቀው የሕወሓት የውስጥ እና የውጭ ሽብር የሚጋለጥበት ቀን መድረሱ የብኣዴን እና የኦህዴድ አባላት ተግተው በመስራት ላይ መሆናቸውን ሌሎችንም ካድሬዎች እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል::

በገዛ ሃገራቸው በድርቅ እና በረሃብ እያለቁ እየተሰደዱ ያሉት የኦሮሞ እና የአማራ ህዝቦች ኦሕዴድ እና ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪካቸው ተጋርጠውባቸው አሊያም ባንዳ ሆነው አስፈጅተዋቸው አያውቁም። በጣሊያን ወረራ ጊዜ ለቅኝ ገዢዎች ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ኦሕዴዾችና ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። ከዛሬዎቹም በተሻለ የድሮ ባንዶች በጌቶቻቸው ጣሊያኖች የሚሉት ይደመጥ ነበር። ኦሕዴድ እና ብአዴን ግን ራሳቸውን ከባንዳነትም አውርደው ባርነት ደረጃ ላይ የጣሉ ከመሆንም አልፎ ባሪያ ሆነው ተለጎመው በመነዳታቸው የሚደሰቱ ሆዳም ሰዎችን የሰበሰቡ ድርጅቶች ናቸው። ኦሕደዽ እና ብአዴን አለቃቸው ሕወሓት ያዘዘውን በመፈጸም የሚረኩ ጥርቅሞች ናቸው። አጉርሱኝ ሲላቸው ያጎርሳሉ፤ጉረሱ ሲላቸው በደስታና በችኮላ ተስገብግበው ይጎርሳሉ።

የብኣዴን እና የኦህዴድ አመራሮች እና ካድሬዎቻቸው ራሳቸውን ከሕወሓት የበላይነት የማላቀቅ ግዴታ አለባቸው::የሕወሓት የበላይነት ከምን የመጣ ነው? ትግል ከሆነ ሁሉን እኩል ድርሻ ያለውን ትግል በጋር ታግለው ነው ወታደራዊውን ስርኣት ያስወገዱት ለሕወሓት ብቻ ማን ይህን እድል ሰጠው? ሕወሓት ብቻውን አልታገለም ብኣዴንም የራሱ ድርሻ ኦሕዴድም የራሱ ድርሻ አለው:; የአማራውና የኦሮሞው ህዝብ ኢሕዴን/ብኣዴንን አይተው ኦሕዴድን አይተው እንጂ ለሕወሓት ሲሉ የእትዮጵያን መሬት በመምራት አልተባበሩም ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ አመራሮች እና ካድሬዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ትግሉ ሕወሓት ብቻ የመራው ያደራጀው ያሸነፈው አለመሆን እና የድርጅቶቹም ድርሻ እኩል መሆኑን ነው::
በመከላከያው እና በደህንነቱ ዘርፍ ከፍተኛውን ቦታ በመቆጣጠር ሌላውን የእንጀራ ልጅ ያደረጉት ሕወሓቶች የበረሃውን ዳገት እና ቁልቁለት እነሱ ብቻ የተወጡት አድርገው በማቅረብ የቀሪውን ታጋይ ደም እና ድካም ጥላሸት እየቀቡት ነው::የሕወሓት የበላይነት እንዲያበቃ በመከላከያው እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ያሉ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ታጋዮች የራሳቸውን አስታውጾ ሊያበረክቱ ይገባል::የፖለቲካ ባርነት እንዲቆም ትግሉን የማቀጣጠል ሃላፊነት አለባቸው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

12 Comments on “በሕወሓት የበላይነት የብአዴን አስረሽ ምችው – ፈንጠዝያ ባርነት እስከመቼ ?”

  1. To be honest these Eprdf guys are all retatded
    bunches . Why they sit and see the terrorist
    right behind their back like media that
    disseminate false information MINILIK SALSAWI
    UNLESS YOU TAKE ACTION ON THIS SOURCE believe me it would be bad to all of us l.

  2. @Sammy

    አንተ ሌባ የወያኔ ተላላኪ ውሻ ካራ ይዞ ሾተል መላሥ ኬክ ቆረሣ ወገን ተርቦ ይህ ነው የአሸባሪ መንግሥት ሢገለፅ ባክህ ልንገርህ

    “እጅ እግርን አጣምሮ ራሥን ተንተርሦ የበሉት እንጀራ ይወጣል ደም ጎርሶ”

    ለናተ ለወያኔዎች ነው አንብቡት ከድርጅት ሥሪያ ተላቀቁ

  3. ብአዴን ኦህዴድ ደህዴን ለወያኔ ባለቤት የሌለው አህዬች ናችሁ ድምር ውጤቱ እንዴት ኢትዬጵያን ለመገነጣጠል አሠባችሁ? አ.አ ከገባችሁ በሀላ የትግል ማንነት መጣ ኢትዬጵያ ተረሣች በትውልድ ሥፍራ ተወሠነ የሀገር ፍቅር ሥሜቱ ተረሣ በየፊናችሁ መገዝገዝ ተያያዛችሁ እውነት ተርባችሁ አቆፋዳው ባዶ ሆኖ ነበር ብረት ያነሣችሁት? ወይሥ ከፋፍሎ ለመግዛት የትግራይ ነፃ ላውጣ ያለውም ፍየል ዛሬ 80ው አልፋል ግንጠላው አልተሣካም ድርቅ የምትባለዋ አንቀፅን ማምለጥ አትችሉም ወዴት?… ትላላችሁ

    አሁን 35 አመት ሙሉ ወገን ከረሀብና ሞት አልተላቀቀም ይቀጥላል ወያኔ እሥካልጠፋ ድረሥ….

  4. ሰይጣን ብዙ ስም አለው ብ አዴን ወያኔ እረስንቱ ጎበዝ እንደቀልድ ማየቱ ይብቃ እጓዳቺን ውስጥ ነው ያሉት

  5. እንደኔ እንደኔ እነዚህ ተለጣፊ ፈንጂ ረጋጭ ድርጅቶች ልደታቸውን ማክበር የጅመሩት 5 አመት እንኳን አይሞላም ሥንገመግመው ታዲያ ወያኔ አጥሯ በጅብ መቀደድ ሢጀምር በድርጅቶቹ ድጋፍን ፈለገች መጣፊያ አደረጓቸው ያሣዝናል እቺ ወያኔ ተንኳሏ የጉድ ነው በውጊያው በርካታ ቁጥር ያለቀው ሀገር ወዳድ ድርጅቶች ነበር ብልጦቹ ተሀገሥ ኮፍ በል እያሉ ወንበር ያዙ ምንም ማረግ አይቻልም ቁጥራቸው አ.አ ሢደርሥ 1 ሻለቃም አልሞሉም ድምፅ ማሠማት አይችሉም ታድያ ያች መላጣ ” አንቀፂ 39 ቁፅሪ ፅቡቅ እዩ ንብ ከሎም ተጋዳላያት” ብሎ መላ ፈየደ የህዝብ ሪፍረንደም ሣይጠየቅ መገንጠል ፀደቀ ታድያ ብረት ያነሡለት አላማ በምግብ ራሥን ለመቻል ሣይሆን በብሄር ራሥን መቻልን ተማሩ አንድነታችን ተቀበረ ትውልድ ግን አንድ ቀን ቆፍሮ ያወጣዋል አጆሀ።

  6. Dimtsachin yisema ye Ethiopian
    Telat neaw manenetschun
    betedegagami asayetachoal .
    Kehadi yinat tute nekash
    nachehu.

  7. ሳልሳዊ ምኒልክ ወገን!! ምኞትሕ በጣም ጥሩ ነው። ነገርግን ብአዲን እኮ ለወያኔ የተሸጠ ዘላለማዊ ባሪያ ነው የሰላሳ አምስት አመት ጭፈራው ወደልቅሶነት የሚመለስበት ቀን እሩቅ አይደለም ምክንያቱም የሕዝባችን ብሶት ገንፍሎ ብአዴንን አንቅሮ ከተፋው ይኸውና 25ዓመታትን አስቆጥሮ ከመጨረሻው ደረጃው ላይ ደረሶልና። ስለዚሕ ሳልሳዊ ምኒልክ ለብአዲን የለገስከው ምክር “ከሞቱ በሑላ መንፈራገጥ መላላጥ ነው “የምትባለው ቅኔ ተመችታኛለች ስለዚ ዘይትና ውሐን አታቀላቅል ይለቁንም ለወሳኙ ሕዝባዊ የነፃት ተጋድሎ እራስሕን አዘጋጅ አንተም እራስሕ ሹም ባሺ እንዳትሆን ተጠንቀቅ።

  8. ሻዕቢያዎች፣ ስግብግቦች፣ ከኢትዮጵያ ወገናችሁ ተነጥላችሁ ባንዴ እንደነ ሲንጋፖርና እስራኤል ልትሆኑ ቋምጣችሁ፣ ሃብታሞች ሆናችሁ ድሃ ኢትዮጵያዊዉን አሻግራችሁ ልታዩ፣ ኢትዮጵያ ለናንተ የጥሬ ዕቃ አቅራቢ፣ እናንተ ፋብሪካ ተክላችሁ እኛ የናንተን ምርት ገዢዎች ልንሆን ወዘተ ኢትዮጵያ ግን ፋብሪካ መትከል አትችልም ወይም ችሎታው የላትም በቃ፣

    አቤት እንዴት ዓይነት ድንቁርና ነው ከቶ? ያ ሁሉ ህልም እንደ ጉም በኖ ሲጠፋ፣ የ፴ ዓመት ዉጊያ ተመኩሮ አለን ብላችሁ ሞከራችሁ። ወዘተ የናንተ ጉድ ተዘርዝሮ አያልቅም። አሁን ደግሞ ኢትዮጵያን እኮ እንወዳለን፣ ጥላችን እኮ ከወያኔ ጋር ነው። አንጀቴ! ለኢትዮጵያ በጎ ኣሳቢዎች፣ “ጽድቁ ቀርቶ በዉል በኮነነኝ” ይባል የለ!

    የናንተ መውደድ ቀርቶብን ቤታችሁን ዘግታችሁ ብትቀመጡልን ትልቅ ነገር ነው። ኑራችሁ የማትረኩ፣ ሄዳችሁ አታርፉ፤ የቅናት ዛር አልለቅ ብሎኣችሁ እንዲሁ እንደባዘናችሁ አላችሁ።
    ወንድም ሕዝባችንን ልቀቁና ወደ መሄጃችሁ ሂዱልን።

  9. This party of the Amhara is a strong party
    who liberate the poor Amhara from the dark
    age . they should be respected and honored .
    those who oppose this are the sons and daughters of
    the killer dergue and the Shabea slaves and
    some komata neftegnas .

  10. ቅማቶችና ብአድኖች
    እንኳን ደስ አላችሁ! አንቀጽ 39 ለቅማት ሊተገበር ነው
    ሰሜን ጎንድር 46 ቀበሌ ለቅንማት ተሰጠ ጉድ ጉድ ስኬት በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!
    የኢትዮጵያ ጠላቶች ኢትዮጵያዊያን የረደታ፣ተመጽች ፣እንድትሆን/እንድንሆን/በሃገሩ፣በወንዙ፣በሰፈሩ፣ስደተኛ ድሃ በማድረግ ስራቸውን ሰርተዋል!
    ቅማንት ሆይ የኢትዮጵያ አንድነት መሰረት የሆነችውን የጎንድር ክፍለ ሃገር ከወያኔ ጋር በመተባበር ለሱዳን፣ ለሸቢያ፣ለወያኔ፣ለግብጽ፣ለአረብ አሳልፋችሁ ሰጥታችሁ እናንተ ዛሬ ኢትዮጵያ አይደላችሁም ብትባሉ አይድነቃች እውነት ነገሩማ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ ሁሉ የእጅን ያገኛታል ነገ ቅማነት ፈላሻ ሞራ ናችሁ እንምትባሉ አትዘንጉ
    የኢትዮጵያ አላህ/ፈጣሪ/ ይጠብቃላል እናንተም ድሃ እንደሆናችሁ ትቀጥላላችሁ!
    ሳተናው አሊ

  11. አዎ ብአዴን እሥከመቼ ነው በአማራው ሥም የሚነግደው? እሥከመቼ ነው እንደአህያ ፈንጂ ሥናመላልሥ የምንኖረው ኦህዴድም ደህዴንም አንድ ነው ሥራችሁ የጎሣ ፌድራሊዝም መዘዙ ብዙ ነው ብትበተኑ ይሻላል በግዜ ወያኔ መገንጠል እንደማይችል በቂ ምልክቶችን በተፈጥሮ ክሥተት እያየው ነው ከቻላችሁ ሞክሩት ውጡልን ከሀገራችን

  12. አዎ ብአዴን እሥከመቼ ነው በአማራው ሥም የሚነግደው? እሥከመቼ ነው እንደአህያ ፈንጂ ሥናመላልሥ የምንኖረው ኦህዴድም ደህዴንም አንድ ነው ሥራችሁ የጎሣ ፌድራሊዝም መዘዙ ብዙ ነው ብትበተኑ ይሻላል በግዜ ወያኔ መገንጠል እንደማይችል በቂ ምልክቶችን በተፈጥሮ ክሥተት እያየው ነው ከቻላችሁ ሞክሩት ውጡልን ከሀገራችን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*