የወያኔ በመፈክር ጨዋታ ውስጥ ገብቶ ነገርን እየረሱ ሕዝብን ማበሳጨት እና የጌታቸው ረዳ ዲስኩር (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የወያኔ በመፈክር ጨዋታ ውስጥ ገብቶ ነገርን እየረሱ ሕዝብን ማበሳጨት እና የጌታቸው ረዳ ዲስኩር (ምንሊክ ሳልሳዊ)
Minilik Salsawi – ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ከቃል አቀባይነት ይልቅ ለሕወሓቶች በወሬ አቀባይነት ያገለገለው ጌታቸው ረዳ ለሬድዋን ሁሴን ከስራ መባረር ሁነኛ ምቀኛ የሆነውና በግምገማው ይሁን በተለያዩ ስብሰባዎች እንዲሁም ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ሲገናኝ የሬድዋንን ስም በማጥፋት እና ሬድዋንን በማሳጣት ረዥም ጊዜያትን አሳልፎ በሬድዋን ወንበር ላይ ተቀምጧል::በዚህ ወሬኛ ሹልኩልክ እና ተንኮለኛ ጸባዩ በፈጠራ ሰውን መወንጀል ባሕሪው ከአማካሪነት ተነስቶ ወደ ሚኒስትርነት እና የማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተወትፏል::የነስብሃት ነጋ ወሬ አቀባይ እና ዋና ተሰላፊ ጌታቸው ረዳ ከመቀሌ ጫት ቤት አውጥቶ ለሹመት ላበቃችው ሕወሓት በል የተባለውን እንደሚል ለሕዝብ ያለውን ንቀት እና ወገን ለወገን ያለውን ፍቅር ትብብር እና አንድነት አራክሶ ሲናገር ተደምጠዋል::ሃገሪቱ በከፍተኛ የድርቅ እና ረሃብ አደጋ ውስጥ ሆና እነጌታቸው እንደለመዱት ሽምምጥ አድርገው ሲክዱ የድርቁን ጉዳይ ይከታተላሉ የተባሉት ጭፍራቸው ደመቀ መኮንንም የብኣዴን ድግስ በድርቁና ረሃቡ ላይ ያለውን አቅም ለመገንባት ይረዳል ሲሉ በሕዝብ ሰቆቃ ላይ ተዘባብተዋል::

ጫት ቃሚ ቢሄድ ጫት ቃሚ ይተካል ነው::ሬድዋን ይሁን ጌታቸው አብዛኛውን ጊዜ መግለጫ የሚሰጡት ቀልባቸውን ሳይሰበስቡ ሲሆን ሽመልስ ከማል ግን ነቄ ስለሆነ ቀልቡን ሰብስቦ ነው የሚከሰተው::ጌታቸው ረዳን የማውቀው ሽጉጤ ጫት ቤት ተወሽቆ ያለ ያሌለውን እየቀባጠረ ሲያደቅ ነው::ጌታቸው በራሱ አይተማመንም እንዳዘዝከው ጎንበስ ቀና ይልልሃል አንተ ሃሳብ አምጣ አንተ ተንኮል ጠንሥሥ እንጂ ለማስፋት ለማስፋፋት ጌታቸውን የሚያክል አካብዶ ውጥረት ለመፍጠር ጌታቸውን የሚያክል የለም::ጌታቸው ከመቀሌ መልስ በኮባ ጉያ በፌስታል እቅፍ በጫት አምባ አዲስ አበባ በደንብ ታውቀዋለች::ሱሰኛ ሰው በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ከባድ ይሁን ቀላል ሃላፊነትን መወጣት አይችልም::ሽመልስ ከማል ለዚህ ምስክር ነው::ሬድዋንም ተከታይ ምስክር ነው::ሌሎችንም እንዲሁ አሉ በተለይ የኦሮሚያ እና የሶማሊ ክልል ባለስልጣናት::ሬድዋን ሁሴን ከንፈሩን እያኘከ ስለ ጌታቸው ረዳ ሲናገር እልህ ይተናነቀዋል::
ወያኔ ባለፉት 25 አመታት በመፈክር ብቻ ሕዝብን እያታለለ የገባቸውን ቃሎች በመርሳት ሕዝብን እያበሳጫ ሲሆን አሁንም ውስጥ የተቆጣውን ሕዝብ ለማታለል ጥፋታችንን ልናርም ነው ካሁን በኋላ ያጠፋ ይሰቀላል በሚል ፌዝ በጌታቸው ረዳ አንደበት ማታለላቸውን ቀጥለዋል::በሃገሪቱ ያለው የፖለቲካ ጫና የኢኮኖሚ ሞት የማህበራዊ ዝቅጠት እንዲሁም ብሄራዊ ውርደት የወያኔ መንግስት ምእራባውያን ያስለመዱት የጂ20 ስብሰባ ላይ ሳይጋብዙት በመተዋአቸው እንደማይፈልጉት ስላረጋገጠ ከባድ ድንጋጤ ውስጥ ሲሆን አጣብቂኙ ከብዶበታል::
ከትራንስፎርሜሽኑ ደካማ ስራዎች አንዱ የሆነው የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን ማዋሀድና እንደገና በየአምስት ዓመቱ ማፍረሱ፣ እንደገና ማዋቀሩ፣ የአንድ ድርጅት የሥራ ባህል ከመፍጠርና ወጪን ከማብዛት በስተቀር ምንም እንዳልፈየደ በተግባር የታየ ጉዳይ ሲሆን የወያኔ መዋቅሮች ዘረፋን እንጂ ስራን መዋቅር ባለማድረጋቸው በሃገሪቱ የስራ ባህል ጠፍቶ የግለኝነት ባህል ተንሰራፍቷል::የስራ አመራ ዘይቤዎችን ለመጠቀም ፈቃደና ያልሆነ አገዛዝ የስራ ባህልን በመግደል ለሃገሪቷ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው::ሕዝብን ለማታለል ምህረት የለሽ ግምገማ አካሂደናል ያለው ጌታቸው ረዳ የሕወሓት ሹሞች የፈጠሩትን የዘረፋ እና የምንተፋ ኔትወርክ እንዴት እንደሚያጠፋ አልተናገረም::በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ግድያ የሚፈጽሙትን ባልደረቦቹን ላለማጋለጥ የሚንፈራገጠው ጌታቸው በወያኔ አገዛዝ መዘናጋት በተፈጥሮ አደጋ የመጣውን ድርቅ እና ረሃብ ወደ ሰው ሰራሽ አደጋ መለወጡን ለማመን አልፈለገም::ጌታቸውና አለቆቹ ወንጀለኛ መሆናቸውን መዘንጋት የለባቸውም::