ትግርኛ ተናጋሪው VOA ጋዜጠኛ ወሎ ድረስ ምን ኣስኬደው?~~

Abera Lucas ~~~ግርማይ ገብሩ ወይዘሮ ብርቱካን ለBBC የሰጡትን ቃለመጠይቅ ውሸት መሆኑን ለማረጋገጥ በፌደራል ህግ መሰረት ትግራይ ክልልን ተሻግሮ ኣማራ ክልል ድረስ ዘልቆ ወይዘሮ ብርቱካን ኣነጋግረዋል። ኣማራ ክልል ውስጥ ለምን ሄደ ?ማንስ ላከው? ትግራይ ክልል ውስጥ የሚጣራ ነገር ጠፍቶ ነው? ወይስ ሌላ ኣጀንዳ ኣለው? የሚለውን ማይቱ ሳይሻል ኣይቀርም፣

ከዛ በፊት ግን ግርማይ ገብሩ ይሕን ከመጻፉ በፊት እሁድ ጥዋት ገዛ ተጋሩ ፓልቶክ ሩም መጥቶ ምን ተናገረ? ግርማይ ገብሩ እሁድ እለታ ገዛ ተጋሩ ፓልቶክ ሩም መጥቶ ስለ መጽሃፉ፣ስለድርቁ፣ትግራይ ውስጥ ስላለው የትግርኛ ስነ ጽሁፍ ኣወራ፣ ውጭ ያሉትን የትግራይ ልጆች መጽሃፉን በመግዛት እና በመሸጥ እንደተባባሩትም ተናገረ፣ ግርማይ ገብሩ ኣንዲት የረሳት ነገር ግን ነበረች!!!! .

~~~ታሪኩ እንዲህ ነው፣ መቀሌ ውስጥ የተዘጋጀውን የትግራይ የዳያስፖራ ፌስቲቫል ላይ ግርማይ መጽሃፉን ሰማእታት ኣዳራሽ ውስጥ ለመሸጥ ሲሞክር ኣዳራሹን ለቆ እንዲወጣ በደህንነት ኣባል እንደተነገረው እና እሱ ካልወጣ ግን መጽሃፋቸውን ለመሸጥ የመጡ በሙሉ እንደሚያባርሩ ለሱ በግሉ ይነግሩታል(ይነገረዋል)፣ እሱም የደህንነት ኣባሉ ያለውን ተፈጻሚ ከማድረግ ሌላ ምርጫ እንደሌለው ስለሚያቅ ኣዲት መጽሃፍ ሳይሸጥ ኣዳራሹን ለቆ ወጣ፣ በተፈጸመበት ነገር ሁላችንም ኣዘንን!!!ግርማይ ገብሩ ገዛ ተጋሩ ፓልቶክ ሩም ላይ መጥቶ ይችን ቃል ኣልተናገረም፣ምክን ያቱ ደግሞ ገዛ ተጋሩ ፓልቶክ ሩም ውስጥ ህውሃትን መውቀስ ኣትችልም፣ እኛም ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን። . .

~~~በዚህ ብቻ ኣላበቃም ግርማይ ገብሩ መጽሃፉን ለማስተዋወቅ መቀሌ ላይ በተደረገው ምርቃት የትግራይ ክልል ሬድዮ እና ቲቪ ጥሪ ቢደረግላቸውም ኣልመጡም፣ ያልመጡበት ምክን ያት ግርማይ ራሱ ሲናገር እንዲህ ይላል፣ ሁለት ጊዜ መጽሃፌን ሳስመርቅ ለትግራይ መገናኛ ቡዙሃን ጥሪ ባደርግም ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ኣልመጡም፣ ይህቺን ነገር ማን እንዳደረጋት ከላይ ወደታች ራሴን ኣጣርቼ ደርሼበታለሁኝ ይላል፣እኛ ግን ማን እንደሆነ እስካሁን ግርማይ ራሱ ኣልነገረንም። የትግራይ ክልል ፕረዚዳንት ናቸው ወይስ የደህንነት ሃላፊዎች፣ይቀጥላል ግርማይ “እኔ በታገልኩለት እህት ወንድሞቼ በታገሉለት በተሰዉለት መብቴ በትግራይ ኣለመከበሩ ኣዝናለሁኝ ይላል”። በነገራችን ላይ ግርማይ ገብሩ የህውሃት ታጋይ ነበር። ለታጋይም መብት የሌላት ትግራይ እያለች ነው ወሎ ድረስ ሄዶ የውሸት የጋዜጠኝነቱን መብት ያከበረው።እኛም ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን። .

~~~እኔም እሁድ እለታ” ግርማይ ገብሩን የማያቅ የትግራይ ልጅ ቢያጋጥማቹ ብየ” በትግርኛ የጻፍኩት ያላንዳች ምክንያት ኣልነበረን። ፓልቶክ ሩም ውስጥ ግርማይ ገብሩ እንግዳ ሆኖ ሲመጣ ማን መሆኑን የማታቅ ኣድሚን ስለነበረች ነው፣ ኣስቡት እንግዲህ ስለትግራይ እቆሮቆራለሁኝ የምትል የህውሃት ደጋፊ ግርማይ ገብሩን ያወቀችው ያሁኑ እሁድ ነው ኣጃይብ ነው ኣለ ያጌሬ ሰው። ግርማይ ገብሩ ስለ ብርቱካን ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ገዛ ተጋሩ ሩም ውስጥ ነው፣ እኔ ዛሬ ኣይደለሁም የሰማሁት እሁድ ጥዋት ነው እናም ኣይገርመኝም። .

~~ግርማይ ወሎ ድረስ ምን ኣስኬደው?ትግራይ ውስጥ ስንት የሚጣራ ውሸት እያለ ከክልል ወደ ክልል ምን ያስኬዳል፣ እስኪ ትግራይ ውስጥ ያሉት ውሸቶች ሊጣሩ የሚችሉትን እንይ፣ . . .

~~ሃይለማርያም ደሳለኝ የትግራይ ገበሬ 100% ዘመናዊ ኣርሶ ኣደር ሆኖዋል ይላሉ፣ ኣሁንግን የትግራይ ገበሬ ርሃብ ላይ ይገኛል ከክልል ወደ ክልል ከመሮጥ እዛው ያለበት ክልል ውስጥ ይህንን ማጣራት ኣይቻልም ነበር ወይ? . .

~~ትግራይ ውስጥ የውሃ ኣቅርቦት 92% መድረሱን የትግራይ ክልል ይናገራል!!!ነገር ግን ትግራይ ውስጥ ውሃ በሳምንት ኣንዴ እንካን ከመጣች እልል ነው፣ ይህንን ነገር ውሸት መሆኑን ኣለመሆኑን ለማጣራት ለምን ከበደው? ዞሮ ዞሮ ትግራይ ውስጥ ብዙ የሚጣራ የውሸት ዳታ የመልካም ኣስተዳደር ችግር እያለ ለምን ወሎ ድረስ ኣስኬደው? ፍራቻ!!! ከሙያ እና ከህሊና ይልቅ ለደሞዝ መኖርን ስለሚሻ።እኛም ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን። . .

~~ሌላም ኣለ አቶ ዳዊት የተባሉ ኢንቨስተር፣ ኣሁን ኣቶ ዳዊት በህውሃት ባለስልጣናት 200 ሺ ብር በላይ ገንዘባቸው እንዳይንቀሳቀስ ተደርገዋል፣እኛም ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን። ኣቶ ዳዊት ኣድዋ ከተማ ውስጥ የተሰጣቸው መሬት በክልሉ ሃላፊዎች ተነጥቀዋል፣እኛም ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን።

~~ምርጫ በመጣ ቁጥር ለሚገደሉት የዓረና ኣባላት ማን እንደገደላቸው ለምን እንደተገደሉ ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን።

~~ኢፈርት የትግራይ ህዝብ ነው ለሚሉ የህውሃት ባለስልጣናት የትግራይ ህዝብ መሆንዋን ኣሁን ድርቅ በተከሰተበት ወቅት ለምን ሁሉም ከትርፍ ድርሻ እንዳልተሰጠው የሚያጣራልን የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን!!!!!

~~ህውሓት ጉባኤ ባካሄደበት ወቅት ጌታቸው ኣሰፋ ላቀረበው መከራከሪያ ነጥብ “ክራይ ሰብሳቢነት ሙስና” ለምን በ ኣብዛኛው የህውሃት ማእከላይ ኮሚቴ እንዳይታይ እንደተደረገ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን።

~~እናማ ግርማይ ገብሩ የፌደራሊዝም መብቱን ተጠቅሞ ከትግራይ ወሎ ድረስ ያስኬደው ትግራይ ውስጥ እንደዚህ ያለ ጥናት ቢያደርግ ላንዲትም ቀን እንደማይኖራት ስለሚያቅ ነው፣ ግርማይ ከመቀሌ ውጭ ወደ ተለያዩ የትግራይ ዞኖች ይሁን ወረዳዎች ለመንቀሳቀስ ከክልሉ ፍቃድ ያስፈልገዋል፣ ኣማራ ክልል ለመሄድ ግን መብት ኣለው፣ የአማራ ክልልም ትግራይ ውስጥ መብቱ ታፍኖ የውሸት የጋዜጠኝነት ስራውን በክልላቹ እንዲሰራ ስለፈቀዳቹለት እናመሰግናለን፣ ግ ርማይ ገብሩ ትግራይ ውስጥ ስንት የሚጣራ ነገር እያለ ውሎ ድረስ ምን ኣስኬደህ?  Abera Lucas

19 Comments on “ትግርኛ ተናጋሪው VOA ጋዜጠኛ ወሎ ድረስ ምን ኣስኬደው?~~”

  1. germay geberu kelel belo neger ayemchegnem wlo deres leyed yechalew beney gemet esu endegazetegnent muyaw gedeb yelsh yetem ager hedo lezgeb yegazetegnent mebetu new gen yenanet menged hule geze tebabun godana selyazachehu mekelakel sayenorebachehu berta yemegebachehu hul geze tensh maseb aywatam besefew godana hulunem bemelkam eyayachehu seru gazetegna germay ende gazetegnenteh bensu kelel becha mayet serahenem yatebewal sel sefewa agerh ethiopia ewnten yaregaget bechalekew zegeb lemenem atechenk ewnet wela adera tewtalech yezan geze bedel tewtaleh gera yemyagabuten leyachew mekery yehew new

  2. if girmay gebru not allowd to go amara land and you go back to your blessed land gondre from the great oromo land.no more power no more ethiopia is ortodox.viva the great oromia.

  3. You are a brilliant observer. I’ve been a VOA listener for short period of time (mostly the Tigrigna Program). I decided not to waste my time recently because of this ‘VOA Reporter’ name Girmay Gebru. My reason was that he always sounds a copy/cat (copy and paste) specialist of the Dimtsi Woyane’s cheap PR. You don’t need to be an expert to figure out he is a recruited PR’ist cadre. He obviously is a low profile ‘Limatawi Cadre’ who cowardly annoy the world that Ethiopia is about to become world’s second biggest economy next to China by next spring (forget the US, Europe and others since they will be history, according to Girmay and his masters).
    Honestly, if I were Girmay, I become a World Class reporter by using the opportunity that is on his hand, as a reporter for a well-known international news media VOA, destined to report from an oppressed society, where a free and independent media is equals to zero, he should take the chance even for one and his last time to use the opportunity. Remember, world class reporters and journalists take a risk then become popular by exposing and sharing the untold stories.
    One wonders why while there are millions of social, economic and political issues in Tigray? Well, Girmay and his surroundings are bunch of POWs of the Zenawi doctrine, that is lie lie and lie then lie.
    As an American Tax payer myself, I feel betrayed and sad to see the American Tax payer money being misused for a wrong purpose to oppress a freedom of speech and killing a true journalism in Ethiopia. It may be time to write a complaint to the State Department not only about Girmay but also for the entire Tigrigna Program management, for knowingly cooperate and allow to broadcasting a brutal and totalitarian regime’s propaganda on a daily basis.

  4. come on wodi tegaru ! ! ! its a good start,but more is expected of wodi tegaru as the venom of tplf is made out of the tegaru.its never too late to speak out.for now it a good beginning.girmai is of course cadre.

  5. ትግርኛ ተናጋሪው ጋዜጠኛ ለምን ወደ ሰሜን ወሎ ተጉዞ ዘገበ፣ የሚለው አባባል ለኔ ብዙም አልተመችኝም። ምክንያቱም እኛ የምንፈልገው እቦታው ድረስ ተገኝቶ ተገቢውን ዘገባ አድርጓል ነው ወይስ አይደለም መሆን ሲገባው ማለቴ ነው።
    እንደሰማሁትና እንደተረዳሁት ከሆነ ጥሩ ዘገባ አቅርቧል ሊመሰገንም ይገባዋል እያልኩ፣ ነገር ግን ለምን ሩቅ መንገድ ተጓዘ እቅርቡ ትግራይ ውስጥ ብዙ የሚባል እያለ መሆኑ ነው የተቺው ሀሳብ።
    ስለዚህ ትግራይ ያለችበትን አስተዳደር ከሌላው ወገኑ ኢትዮጵያዊ ጋር ማነጻጸሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል ባይ ነኝ።
    አስተዳዳሪዎቹ ትግርኛ የሚናገሩ የጎረቤት አገር ሰዎች መሆናቸውን አትርሱ።
    መልካም ጊዜ።

  6. ተናገርኩ ብለህ ሙተሃል ! ! ! ትግራይ የራስዋን አምባሳደር የምትወክል፥በመለስ እቅድ መሰረትም ለሌሎቹ ክልሎች የኢንዳስትሪ ማዕከል የሆነች •••የኤፈርት ብቸኛ ባለቤት ሌሎቹን ክልሎች ልክ አሜርካ አጋር የአውሮጳን አገሮች በማርሻል ፕላን እንደረዳች ሁሉ ትግራይም ሌሎቹን ክልሎች በሞግዚት የምታስተዳድር ••ወዘተ ወደ ሌሎቹ ክልሎች እንዳፈተታት ገብታ የምትወጣት ሲያሻትም ላለመውጣት መብቱዋ የተጠበቀ የራስዋን ዘጋቢ ያለቪዛ ወደ ሌሎቹ ክልሎች መላክ አምትችል ሌሎቹ ክልሎች ግን ወደ ትግራይ መግባት ቢፈልጉ ቪዛ የመስጠት ወይም ያለመስጠት ልዩ ሃይልና መብት ያላት ናት።እስቲ ከወሎ ወይም ከአማራው ክልል ትግራይ ይሂድና አንዲት ነገር ትንፍሽ በል። በመጨረሻም ሆዳም አማራ ወይስ የወያኔ ስናር አህያ ልበልህ ? ወይስ ሁሉም ይስማማሃል? ? ዴዴቭ ! ! !

  7. ተናገርኩ ብለህ ሙተሃል ! ! ! ትግራይ የራስዋን አምባሳደር የምትወክል፥በመለስ እቅድ መሰረትም ለሌሎቹ ክልሎች የኢንዳስትሪ ማዕከል የሆነች •••የኤፈርት ብቸኛ ባለቤት ሌሎቹን ክልሎች ልክ አሜርካ አጋር የአውሮጳን አገሮችን በማርሻል ፕላን እንደረዳች ሁሉ ትግራይም ሌሎቹን ክልሎች በሞግዚት የምታስተዳድር ••ወዘተ ወደ ሌሎቹ ክልሎች እንዳፈተታት ገብታ የምትወጣ ሲያሻትም ላለመውጣት መብቱዋ የተጠበቀ የራስዋን ዘጋቢ ያለቪዛ ወደ ሌሎቹ ክልሎች መላክ አምትችል ሌሎቹ ክልሎች ግን ወደ ትግራይ መግባት ቢፈልጉ ቪዛ የመስጠት ወይም ያለመስጠት ልዩ ሃይልና መብት ያላት ናት።እስቲ ከወሎ ወይም ከአማራው ክልል ትግራይ ይሂድና አንዲት ነገር ትንፍሽ በል። ትግርኛ ተናገረ ኦሮምኛ ተናገረ አይደለም ቁምነገሩ። በመጨረሻም ሆዳም አማራ ወይስ የወያኔ ስናር አህያ ልበልህ ? ወይስ ሁሉም ይስማማሃል ? ? ዴዴቭ ! !

  8. መቼም ስልጡን አነጋገር ከኛ እንዳይወጣ የተገዘተ እስኪመስል ድረስ ከኣፋችን ጥሩ አልወጣ እያለ፣ የሰዉን ክብር ማንኳሰስና አላስፈላጊ ዘለፋን ምን ይሉታል፤
    ወደ ቁም ነገሬ ልግባና፣ ወደድንም ጠላንም አንድ ማወቅ የሚገባን ነገር ቢኖር፣ ትግርኛ እየተናገረ የሚያስተዳድርህ ያለው የጎረቤት አገር ሰዎች መሆናቸውን ተረዱ በሁለቱም ጎራ ተሰልፋችሁ የትግራይ ሰው እንዳለፈለት፣ ወዘተ የምትልፍፉ ሁሉ።
    የትግራይ ህዝብን ልክ የመሞከሪያ ማሳ እየተጠቀሙበት እንደሆነ የምናውቀው ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተቀጠረ ድርጅት ነውና የተለያዩ ሰዎችን ቢያስቀምጥ ለጥቅሙ ስለሆነ ሊያስደንቀን አይገባም ባይ ነኝ።
    አዎ እያወቃችሁ ልታደናቁሩ የምትፈልጉ ተላላኪዎች እንዳላችሁ ግልጽ ነው። እስኪ አሁን ለምንድን ነው ኢትዮጵያ ከ፱፱ ሚሊዮን ህዝብ በላይ እያላት፣ አንዲት ትንሽ አገር ሁለት ወደብ ተሰጥቷት ያውም የራሷ የነበረ፣ እኛ እናውቅልሃለን ዝም በል ተብሎ ወደ ሌሎች አገሮች መጎናበስ የተገባው፣ ታዲያ እነዚህን ሰዎች ነው የትግራይ ናቸው ተብለን እንድንቀበል የምንወተወተው፤ እውን ኢትዮጵያውያን ከሆኑና ከተቆረቆሩና ለሃገራቸው አሳቢ ከሆኑ ያለምንም መሸፋፈን ኢትዮጵያ አንድ ወደብ ያዉም የራሷ የሆነዉን አሰብ ማግኘት አለባት ብለው በዓለም ፍርድ ቤት ለምን ክስ አቅርበው አይጠይቁም? ምክንያቱም ቅጥረኞች ናቸውና።
    ስለዚህ የትግራይ ሕዝብን በዚህም በዚያ ሆነን መከራ ባናበዛበት ይሻላል።
    ልብ ብላችሁ አዳምጣችሁት ከነበረ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ንግግር፣ ኢትዮጵያዊነትኮ…ፌዝ ነበር።
    ኤርትራዊ እዉን ለኢትዮጵያ ሊያስብ ነው? ሂዱና አገራችሁን አስተዳድሩ! በቃ።

  9. Please, Please say what you want to say freely. But if you are calling names and insulting individuals, you are not free for yourself. You are a prisoner of hate and partiality. Anyone who wants to comment please comment on ideas and deeds of people than personalities. We care for what Girmai Gebru reports and informs us and examine his reports if we are suspicious. But saying Girmay is tall,short Tagay Adhari .. will do nothing good. He has the right to go to wollo and report but he is also responsible for what he is reporting. We can ask Girmay to report for us from Tigray by giving him clues of issues necessary and timely to report. If he ignores that we ask him why. If he still ignores reporting important issues and events there, then we question his neutrality and journalistic ethics and tell him that if we can with more evidences. If we say woyanie, hodam amara, Timkihtegna…… I think we are not appropriate persons to make comments and we are hate mongers. If we behave properly, we will be able to know the truth which can never be hidden by any power.

  10. የvOA ጋዜጠኞች የትግርኛ ፕሮግራም ኤርትራዊ ላለመሆናቸው የሚያጣራልን የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን!!!

  11. ዋይ አይትፈልጥዶ እዚ ግርማይ ዝብሀል ሠብ ናይ ወዲ ተቆናኒት አዜብ መሥፍን ወላድ እዩ

  12. ሲጀመር አንተ እንደ ጋዜጠኛ ጭብጥ ነገር የምታቅ አይመስለኝም።ምን እንኳን በትግራይ ውስጥ ብዙ ሚጣሩ ነገሮች አሉ የሚለው ሐሳብህ ቢያስማማኝ ነገር ግን ቢቢሲ ወ/ሮ ብርትኳንን እንደ ናሙና መውሰዱ ግርማይ ደግሞ እንደ ገለልተኛ ጋዜጠኛ ወ/ሮ ብርትኳንን መጠየቁ አግባብ ያለው ነው።
    እንጂ አንተ እንዳሰብከው የትግራይ ህዝብ በድርቅ ሰለ ተጎዳ ገበናውን በአማራ ህዝብ ለመሸፈን አይደለም አራት ነጥብ።

  13. አበራ እንድ ትክክል የሆንከውንና የተሳሳትከውን ልንገርህ ትግራይ ውስጥ ያለውን ችግር ይፈትሽ ትክክል ለምን ወሎ ሄደ እንካን ከትግራይ BBC ከየት ነው እንዴ የመጣው በናትህ ለአገር ገፅታ ጡሩ የስራ ጎበዝ ማለት እንልመድ ለምሳሌ BBC የዘገበውን ዘገባ ልጅዋን በመንግስት ተቃዋሚ ሃይሎች ተገደለ ብሎ ቢሆን ኑሮ እና እዛ ሂዶ አጣርቶ ውሽት መሆኑን ቢዘግብ ንሮ ባንተ ቤት እንደ ጀግና ትፅፍለት ነበርክ እሱ የዘገበው ግን የመንግስትም የተቃዋሚም ሳይሆን የአገር ገፅታ ነው ለኛ ሳይሆን ለተረካቢ ልጆቻችን ሃቀኛ ዘገባ ሌላ ልጨምርልክ ለግርማይ ለምን ይህ ይህ አታደርግም ያልከው አንተ ራስህ ታደርገዋለክ ??? የጋሮ ጀግና አትሁን

  14. Bua , bejaha gidefeni. Girmai is Agame. What do you expect from an Agame trush. All Agames are Melese Zenawis used condoms.

  15. Sanitation for all! AAWSA congrats residents of AA on the inauguration of 100s of new restrooms worth 148m br. on world toilet day 19/11/15. Aweke H/mariam, GM

    ወገን ተርቦ ሽንትቤት ምረቃ?

  16. ante nonsense, ende and ethiopiawi enasib sitilen alneberem ende. ahun Amhara tigray kilil eyalk mitkebatirew. girmay gebru malet eko yegazetegn sinemigbar gebtot mizanawi mereja yemiset new. esti yenanten mereja eyut hule metfo never bicha. almost all our information being white lie.

  17. አማርኛ ተናጋሪዎች የኢሳት ጋዜጦኞች ኤርትራ ድረስ ሂደው የለም እንዴ፤ ደግሞስ ሰሜን ወሎ ቀርቶ ኢዮጵያ ሙሉ ሄዶ ስለ ኢትዮጵያ ብዘግብ ምን አስጨነቃሁህ፤ ደግሞስ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ወሎ ሄዶ ዘግቦ የለም እንዴ፤ ምድረ ዘረኛ ሁላ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*