ለተራቡት ዜጎች እርዳታ ባለመድረሱ በርካቶች ወደ ከተሞች እየተሰደዱ ነው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በያዝነው አመት አጋማሽ 15 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ መንግስት በበኩሉ 8.2 ሚሊዮን ህዝብ እንደተራበ አምኗል፡፡ ሰሞኑን ቢቢሲ በሰራው ዘገባ በርሃቡ ምክንያት በየቀኑ 2 ህፃናት እየሞቱ እንደሆነ ገልፆአል፡፡ ለተራቡት ዜጎች እርዳታ ባለመድረሱ በርካቶች ወደ ከተሞች እየተሰደዱ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ መንግስት እንርዳታ እያደረሰ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡ መንግስትም ርሃቡን ግልፅ በማድረግ ለዜጎች ከመድረስ ይልቅ መደበቁን መሸፋፉኑን መርጧል፡፡
