በሕገመንግስቱ አንቀጽ 39 መብት ነው ብሎ ወያኔ ያጸደቀውን የራሱን ሕግ በተግባር ሊተረጉሙ ተንቀሳቅሰዋል ያላቸውን ከሰሰ::

በሕገመንግስቱ አንቀጽ 39 መብት ነው ብሎ ወያኔ ያጸደቀውን የራሱን ሕግ በተግባር ሊተረጉሙ ተንቀሳቅሰዋል ያላቸውን በሃሰት ውንጀላ ከሰሰ::

ማስረጃ አልባ ከባባድ የሃስት ክሶች ቀርበውባቸዋል ::

=============================================================

ባለሥልጣናት አየር መንገድና ኤምባሲዎች ዒላማዎቻቸው ነበሩ ተብሏል :: የኦሮሞን ሕዝብ ነፃ ለማውጣትና ክልሉን ከፌዴሬሽኑ ለመገንጠል፣ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል የተባሉ 29 ተጠርጣሪዎች፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ እና 19ኛ ወንጀል ችሎቶች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላት ሆነው፣ ከድርጅቱ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበልና ዓላማውን ለማስፈጸም በአገሪቱ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር፣ ኅብረተሰቡን ለማስፈራራት፣ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሽብር ተግባር ወንጀል ለመፈጸም ሲዘጋጁ ሲንቀሳቀሱ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፣ የተመሠረተባቸው ክስ ያስረዳል፡፡

በኤምባሲዎችና በአየር መንገዱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከሦስት ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ሞጆ ከተማ ውስጥ በ2005 ዓ.ም. ቤት ተከራይቶ ለሦስት ወራት ሲንቀሳቀስ ነበር የተባለው ተከሳሽ፣ በቅጽል ስሙ ጫላ ኢብራሂም የሚባለው ቦሰት በቀለ ሮባ፣ ከኦነግ አመራሮች የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ ሰኔ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አካባቢ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን የዓቃቤ ሕግ ክስ ይገልጻል፡፡

ነዋሪነቱ ኬንያ ናይሮቢ የሆነውና አብደላ መሐመድ የተባለው ሌላው ተከሳሽ ደግሞ፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትን እንዲገድልና በመንግሥት ተቋማት ላይ ጥቃት እንዲፈጽም ከኦነግ አመራሮች የተሰጠውን ትዕዛዝ ለመፈጸም፣ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ወደ አዳማ ለመሄድ በጉዞ ላይ እያለ፣ ሞጆ ከተማ በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም. በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን ክሱ ያስረዳል፡፡

ራሳቸውን በሴል በማደራጀትና የሥራ ክፍፍል በማድረግ ምዕራብ ሸዋ ዞን አደአ በርጋ ወረዳ ኦሎንኮሚ አካባቢ በሚገኘው ጫካ ውስጥ ለሚገኘው የኦነግ ቡድን፣ የስንቅና ትጥቅ ድጋፍ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ፣ የመንግሥት ሠራተኞችን ለመግደል ሲያሴሩና ለግድያ በተመረጡ ሠራተኞች መኖሪያ ቤትም ሲመላለሱ ነበር ከተባሉት ውስጥ በቅጽል ስሙ ማሞ የሚባለው ኦላና ከበደ ደምሴ፣ መገርሳ ፈቃዱ፣ አርገሞሲሳ ሌንዲሳ፣ ምክትል ሳጅን መሠረት ኦቡማ፣ አብዲሳ ኢፋና ዋርደር ተመስገን ፀጋዬ የተባሉትን ተከሳሾች ዓቃቤ ሕግ በቀደምትነት ጠቅሷል፡፡

ተከሳሾቹ በኬንያና በተለያዩ አካባቢዎች ሥልጠና በመውሰድ የጦር መሣሪያ አፈታትና አገጣጠም፣ ቦምብ ውርወራና ዒላማ ተኩስ በመሠልጠን፣ ሌሎችን በመመልመል፣ ሰላማዊ ሰው በመምሰልና ለሕዝቡ ተቆርቋሪ በመሆን፣ ኅብረተሰቡ አምስት አምስት ብር መዋጮ እንዲከፍል በመቀስቀስ፣ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመገርሰስ፣ በሴል በመደራጀት እየተንቀሳቀሱ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

የኦነግን ተልዕኮ በመቀበል የአገሪቱን ሕዝቦች አንድነት ለማፈራረስ፣ የኦሮሞን ሕዝብ ነፃ ለማውጣትና ክልሉን ከፌዴሬሽን ለመገንጠል በሚል ዓላማ፣ የሽብር ተግባር ወንጀል ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በ2007 ዓ.ም. በተለያየ ጊዜና ቦታ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው፣ ጥቅምት 24 እና 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ክስ የተመሠረተባቸው 29 ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡ ተጠርጣሪ ተከሳሾች ቦሰት በቀለ ሮባ፣ አብደላ መሐመድ፣ አብዲ ዋቆ፣ ፋንታሌ ሮባ፣ ቦሩ ሀዌ፣ ጄሎ ፈንታሌ፣ ሁሴን አዲ፣ ሻሾ አድማሱ፣ ኦላና ከበደ፣ ወልዴ ሞቱማ፣ መገርሳ ፈቃዱ፣ አርገሞ ሲሳ ሌንጂሳ፣ ምክትል ሳጅን መሠረት ኦቡማ፣ አብዲሳ ኢፋ፣ ዋርደር ተመስገን ፀጋዬ፣ ተመስገን ወርዶፋ፣ ቦኪ እሸቱ፣ ብርሃኑ ቦኪ፣ ማሙሽ ቦኪ፣ ፍቃዱ አዱኛ፣ መኮንን ዘውዴ፣ ወርቁ ጉርሙ፣ ገረሙ አዱኛ፣ ደረጄ ታዬ፣ ጃለታ ሰንዳፋ፣ ላቀው ሮቤ፣ እንግዳ ቁሲ፣ ቶሽሌ ተስፋና ታደሰ ዓለሙ መሆናቸውን የዓቃቤ ክስ ይዘረዝራል፡፡

11 Comments on “በሕገመንግስቱ አንቀጽ 39 መብት ነው ብሎ ወያኔ ያጸደቀውን የራሱን ሕግ በተግባር ሊተረጉሙ ተንቀሳቅሰዋል ያላቸውን ከሰሰ::”

  1. ይህ ሊያሥገርመን አይችልም አንቀፅ 39 ሆን ተብሎ በወረበላው የወያኔ አገዛዝ እንዲፀድቅ ያረጉት ሀገሪቷን ለመበታተን አልመውና አቅደው በዚህ ሽፋን ሥር የሚደራጅ ድርጅትን አሸባሪ የሚል ታርጋ በመለጠፍ ለእሥር መዳረግ ተግባራቸው ነው እውነት ይህ ድርጅት ምን ያህል እውነት ነው ከመልክአ ምድር አቀማመጥ ጀምሮ የቱ ተገንሥትሎ የቱ ሊቀር ማን ባንዳ ሊሆን? ወይሥ በተገላቢጦሹ ወያኔ ትግራይን ሊገነሥትል የሚያሥችለው ደረጃ ላይ ደርሷል ቢባልም ቅሉ ተገንጥሎ በምግብ ራሡን ሥለማይችል በሌላው ላይ ጥገኛ ህዋሥ በመሆኑ መሥኖም የህልም እንጅራው ነውና ይህን ሀሣብ አዘግይቶታል ምላሹን ይህው ኦሮምያ ነው እኔ አላልኩም የሚል የሀሠት ማሥተባበያ ቅንብር እንደሆነ መገመት ይቻላል።

    አንቀፅ 39 የራሥን እድል በእሥር መወሠን ላለመገንጠል ተብሎ በ547 ጉልቻዎች ብታሻሽሉት ይሻላችሀል

    **********************************************

  2. ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት እንታገላለም እያላችሁ የኦሮሞ ደም በከንቱ ስፈስ ልዩነታችሁ ምን እንደሆነ ሳትረዱ ለማን እንደምትታገሉ ሳትለዩ የኦሮሞ ሕዝብ ተረሽነ ተሰደደ እናንተ ገና አምሳ ቦታ ተበታትናችሁ ኦሮሞንአሳሰራችሁ አስጨፈጭፋችሁ ለዚህም ተጠያቂዎቹ በመጀመርያ እናንተ በሁለተኛ ደረጃ ወያኔ ነው አምሳ ቦታ ተበታትናችሁ እንደትነው ኦሮሞን ነፃነት የምታጎናፅፉት ለራሳችን የስልጣልን ማማ ላይ የመፈናጠጥ አባዘ ተፀናውቶን ነው ብትሉ ይሻላችኃል በዚያውም ከወያኔ ፍርፋር ይጣልላችኃል ካለበለዝያ ግን አንዲት እናታችሁን ተበታትናችሁ ነፃ አታወጧትም እናንተም ነፃ አትወጡም

  3. ኢህአዴግ ራሱን ቆም ብሎ በማየት ጅቦችን ቢከላከል መልካም ነዉ!!!ያልያ ግን ethiopia will be….

  4. አንተም ከጅቦቹ አነዱ ትሆናለህ ኢትዪጵያ ምንም አትሆንም ይህቺ ረሃብ ትለፍ እንጂ እናያለን ገና……… ገዢ ሆነ ተቃዋሚ ለ አንድ ኢትዮጵያ እንስራ፡፡

  5. አንተም ከጅቦቹ አነዱ ትሆናለህ ኢትዪጵያ ምንም አትሆንም ይህቺ ረሃብ ትለፍ እንጂ እናያለን ገና……… ገዢ ሆነ ተቃዋሚ ለ አንድ ኢትዮጵያ እንስራ፡፡

  6. ቆንጂት የምን ይልክ ሳልሳዊ የመንፈስ እህት=ምነው በውሸት ማስተርሽን ሰራሽ?

  7. ye oromo tegentayna weyani yetgri tegentay liba siserk ysmamana sikafel ytalal new negeru dros bihon yezer kll yefeterut huletum bebltabltnet sltan enageNalen bemalet amharan katefan ethiopiyan enkefafelalen bemil zer atften zer asdten ager kemten lezerochachn nesanet enametalen silu lemehonu yetnaw zemen lay endalu erestewtal adis ager adis tarik lemesaf ye ethiopiya telatoch enkan be 21Naw kflezemen beyetnawm zemen yemeta altesakaletm ethiopiyan yefelege ethiopiya astenagdalech enji ageranna mannetan asalfa seta atawkm ethiopiyawinet wrs new weyani banda yefashisht ashker bemehon ye ekonomi balebit lemehon ena keriwn ethiopiyawi yebey temelkach lemadreg betaktik ethiopiyan yegl habtu adrgo lemetekem yababelachu enji oromon wedo amharan sletela aydelem weyani yetgri banda oromo sle ethiopiyawinet aychenekm wedeb ayteykm bemil astesaseb kll kesetenachew amharawn lematfat hayl yhonunal bemil estratiji enji sle ethiopiya ende ager mekomna etiopiya oromiya yemtbal agern endalwererech oromo erasu tenkko yawkewal mot lekefafayoch lezer atfiwoch ager afrashoch

  8. lerasish endetemechesh negerochin lemasked sitmokiri wishet ena sihitet new. mikniyatum ankets 39 behail yefelegnewin enadrig silemayil. yerasish zena gin yemilew “behail” new. silezi tinish amezazigni ehitachin. nonsense remains nonsense if it is written by any one.

  9. ከ29ኙ ኦሮሞዎች በተጨማሪ 25ሺህ ኦሮሞዎች በቃሊቲ; ቂሊንጦ; ዝዋይና ሌሎች እስር ቤቶች የታጎሩት ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ነው:: እስር ቤቱም ኦሮምኛ ይናገራል ከተባለ እኮ ቆየ!! ይህንን ያህል ኦሮሞ ወገኖቻችን በእስር ላይ እያሉ ዘወትር አርብና ሰኞ ኢትዮ-አማሮች የለንደንንና የዋሺንግተንን ጎዳናዎች የሚያጣብቡት ለአንድ አንዳርጋቸው ፅጌ መሆኑ ያስተዛዝባል!! ኦሮሞ በቁመቱ ልክ የሃገሩ ባለቤት ካልሆነ ቢገነጠል አይሻልም ትላላችሁ? ኦሮሞ መብቱ; ጥቅሙ; ባህሉና ቃንቃው ከተከበረለት ሃገሪቱ የኔ ናት የማይልበት ምክንያትስ ይኖራል? የተዳፈነው የኦሮሞ ፖለቲካ ግሃድ የወጣ ቀን ከመተራመስ አሁኑኑ የኦሮሞን ጥያቄ መመለስ ያሻል!! የቁቤ Generation መጥቶ ከፊታችሁ እየቆመ ነው:: አባካችሁ ኢትዮ-አማሮች ንቁ ከ130 አመት እንቅልፋችሁ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*