በሙስሊም ኮፍያ የተደበቀው የነበረው መንግስት ያስቀመጠው ወንጀለኛው የህገ-ወጡ መጅሊስ ጸሃፊ አራጋው አሊ ሲጋለጥ

ቢቢኤን የማፍያው ህገ-ወጡ አህባሽ መጅሊስ የሃጅ ዝርፊያ መረጃ ቁጥር 2

Abdurehim Ahmed's photo.

በሙስሊም ኮፍያ የተደበቀው የነበረው መንግስት ያስቀመጠው ወንጀለኛው የህገ-ወጡ መጅሊስ ጸሃፊ አራጋው አሊ ሲጋለጥ

ለሁለት አመታት ከሀጅ ጉዞ ታግዶ የቆየው በሌብነት የተሰማራ ሙስሊም ያልሆነ ሲሳይ ተስፉ ወልደ ጊዎርጊስ የተባለ ሀጅ እንዲሄድ ተደርግዋል
ይህ ግለሰብ በመጅሊሱ ውስጥ የፈጸማቸውን ወንጀሎች ህግና ስርአት ያለበት ሀገር ቢኖር በርካታ ክሶች ይቀርብበት ነበር፡፡ እኛም ግለሰቡ የያዘው የሚሊየኖች ኢትዪጲያዊያን
ሙስሊሞችን ውድ ቦታ ነውና በዘንድሮው ሃጅ የፈጸመውን ዝርፊያና ተያያዥ ስራዎቹን ከዚህ በታች እናቀርባለን
ወደ መጅሊስ በገባ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፈው አቶ አራጋው አሊ

የህገ-ወጡ ወጡ መጅሊስ ጸኃፊ አራጋው ሁለት መቶ ሰባ ሰባት ሺ ብር ሳያውቁ በስማቸው አበል የወሰደባቸው ሶስት ወንድምና እህቶች
ይህ ታሪክ እነዚህ ባለታሪኮች ራሳቸው ከጀርባ የተሰራውን አሻጥር አያውቁም ዝርዝሩን ያንብቡ
በጣም የሚገርማችሁ ነገር ቢኖር ይላሉ መረጃውን እና ማስረጃውን ያቀበሉን ምንጮቻችን ”በመጅሊስ ታሪክ ውስጥ እንደዚህ አይን ያወጣ ነገር ብዙም ተደርጎ አይታወቅም ”ለማለት የፈለኩት ነገር በአንድ ጊዜ ከአንድ ቤተሰብ ውስጥ ከአንድ በላይ ሰው ተጋብዞ አይታወቅም ነበር ፤ በዘንድሮው ሀጅ ግን በተግባር በይፋ አራጋው አሊ አድርጎታል ።
የነጻ የሃጅ ጉዞ ወጪና አበል ተሸፍኖላቸው መሄድ ያለባቸው ኡለማዎችና ዳኢዎች ቢሆኑም መጅሊሶች ግን ለቤተሰቦቻቸውም እንዲሁም ለግለሰቦች በመሸጥ የግል ጥቅማቸውን ያደልባሉ

ከላይ በፎቶ ላይ የሚታዩት ፈኪያ ሙሳ አህመድ ፣ ሐናን ሙሳ አህመድና ኤልያስ ሙሳ አህመድ የተባሉት በዘንድሮው ሀጅ ከአንድ ቤተሰብ በህዝበ ሙስሊሙ ገንዘብ ለሀጅ ከተጋበዙት ውስጥ ናቸው ፤ ይህ እንዴት ልሆን ቻለ ብለን ስናጣራ ግን ሰዎቹ የከፈሉ መሆናቸውን ነው የደረስንበት ። ጉዳዩ እንዲህ ነው ሙሰኛው አራጋው አሊ ሰዎቹን የሀጅ ሙሉ ክፊያ ከአስከፈላቸውና ራሱ ገንዘቡን ተቀብሎአቸው ወደ ራሱ ኪስ የ3 ሰው ሂሳብ ብር 177,300 ካስገባ በኋላ በዚህ ይህ ብቻ አይበቃኝም በማለት ተጋባዥ በማስመሰል ስማቸውን ወደ ፋይናንስ አስተላልፎ በእያንዳንዳቸው ስም የ20 የ20 ቀን አበል ብር 32,000 በማውጣት እነሱም በማያውቁት መንገድ በ3ቱ በስም በድጋሚ ወደ ብር 96,000 ገደማ ወደ ራሱ ኪስ አስገብቷል ፤ ይህ ነው እንግዲህ ጫወታው ከአንድ ቤተሰብ ውስጥ 3 ሰዎች የመጋበዛቸው ሚስጥር ።

Abdurehim Ahmed's photo.

ይህ አራጋው በህገ-ወጡ መጅሊስ ከዘረፋቸው ብሮች ጥቂቱ ነው ፡፡ የኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞች ታላቅ ተቋም በሆነው ቦታ ላይ የተቀመጠው አራጋው አሳፋሪ የሆነውን ምዝበራውን በዚሁ ይቀጥላል፡፡
በመጅሊስ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጾታዊ ጥቃት እንደተጠበቀ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ሃብት በመዝረፍ በኩል በአስደንጋጭ መልኩ በአጭር ጊዜ ሚሊየነር እስከ መሆን ደርሶ በቅርቡ መኖሪያ ቤት ሊገዛ መሆኑንም የቢቢኤን ምንጮች አጋልጠዋል ፡፡
በዘንድሮው ሃጅ ከፈጸማቸው ዝርፊያዎች በጥቂቱ
-አቶ አራጋው አሊ ከመጅሊሱ ሃጅና ኡምራና ዘርፍ ሃላፊ አህመድ የሱፍ ጋር በመሆን ከጉዞ ወኪሎች 750 ሺ ብር ኮሚሽን የወሰዱ ለጉዳይ አስፈጻሚያቸው 50 ሺ ብር በመስጠታቸው በተነሳ ቅሬታ ሚስጥሩ ሊሾልክ ችሏል

Abdurehim Ahmed's photo.

-የሳኡዲአረቢያ መንግስት ተጨማሪ ከሰጠው 2000 ሺ ሰው ኮታ ላይ ከ900 ሰዎች ከእያንዳንዳቸው አንዳንዱ ሺ ብር በመውሰድ ዘጠኝ መቶ ሺ ብር ወደ ኪሱ አስገብቷል
-ከጋምቤላ ክልል ለተገባዥ ኢማምና ለሃኪም የተሰጠውን ኮታ ዉህብያ ናቸው ብሎ በማስቀረት ሚስቱን ቀመሪያን በአስቸኳይ ከጋምቤላ በማስመጣት የአበል ብር ወስዶ ወደ ሃጅ ልኳታል
-ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችን ተጋባዥ ሀጅ ተጋዦች ናቸው በማለት ከነሱም ገንዘብ በመቀበል እንደገና በነሱም ስም የ20 ቀናት አበል ተቀብሎ ወስዷል

አቶ አራጋው አሊ በደርግ ጊዜ በአሁኑ የአፋር ክልላዊ መንግስት ተንዳሆ እርሻ ልማት ስራ አስኪያጅ የነበረ ሲሆን በቀይ ሽብር በርካታ ንጹሃንን አስጨፍጭፏል
የተከበራችሁ አንባቢያን አራጋውን በማስመለከት የደረሱን የወንጀል ዝርዝሮች በርካታ ሲሆን አንባቢያንን ላለማድከም ለዛሬ በዚሁ ገትተነዋል
በቀጣይ ደግሞ ሌሎች የመጅሊስ ሃላፊዎች የፈጸሙትን ወንጀል ለህዝብ እናደርሳለን
ማስታዎሻ ፤- ይህን መረጃ ለህዝብ የምናደርሰው በአሁኑ ጊዜ ኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞች በበደልና በጭቆና ላይ ባሉበት ሰአት ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ንጹኃን ሙስሊሞችን በግፍ ገድሎና አስሮ የሙስሊሙ መሪዎች ብሎ ያስቀመጣቸውን ሰዎች አውቆ ሙስሊሙ ለመብቱ እንዲታገል ነው
እናመሰግናለን

መረጃውን ሼር ፖስት በማድረግ በማስተላለፍ በሙስሊሙ ትከሻ ላይ የተቀመጡ ዘራፊዎችን እናጋልጥ