ህገወጡ ሲኖዶስ የቴሌቭዥን አገልግሎቱን የ24 ሰዓት የሳተላይት ሥርጭት ለማስጀመር ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፳፬፤ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

Holy Synod2008Tikmit

ከጥቅምት 12 ጀምሮ የዓመቱን የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በማካሔድ ላይ የሚገኘው ሲኖዶስ፣ የቴሌቪዥን አገልግሎቱን ለማስጀመር የሚያስችል የብር 12 ሚሊዮን 22 ሺሕ ዓመታዊ በጀት ከትላንት በስቲያ ማጽደቁ ታውቋል፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብዙኃን መገናኛ ድርጅት በሚል ተዋቅሮ ሥራ አስኪያጅ በመሠየምና እስከ 22 ሠራተኞችን በመቅጠር የሚጀምረው አገልግሎቱ፤ ዝግጅቱንና ቀረጻውን በሀገር ውስጥ በማከናወን በሳተላይት እንደሚሠራጭ ተገልጧል፡፡